Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሙሴ በእምነት ኃይል የተሞላው ሰው

    በህፃንነት ከሞቀች የድሀ ቤቱ ሲወጣ ሙሴ ዕድሜው ከዮሴፍ ወይም ከዳንኤል በጣም ያነሰ ነበር፡፡ ይሁነና እነኛ የእነሱን ሕይወት ያስተካከሉላቸው የእግዚአብሔር ሕጐች የእርሱንም ገርተውለት ነበር፡፡ ከዕብራዊያን የህፃንነት ጓደኞቹ ጋር የቆየው አሥራ ሁለት ዓመታት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን የእርሱ የታላቅነት መሠረት የተጣለው በእነኝህ ዓመታት ውስጥ ነበር፡፡ እነኝህ መሠረቶች የተጣሉትም ምንም ያክል ዝነኛ ባልሆነ ሰው አማካኝነት ነበር፡፡EDA 65.1

    ዮካቤድ የምትባል አንድ ባሪያ ሴት ነበረች፡፡ በሕይወቷ ያጋጠማት ዕድል የተቀደሰ ሆኖ ሳለ የወደቀባት ሸክም ግን እጅግ ከባድ ነበር፡፡ ግን በማንም ሌላ ሴት አማካይነት የናዝሬቷ ማርያም አለዳነችመ ዓለምም እጅግ ታላቅ በረከት አላገኘም፡፡ ልጅዋ ባስቸኳይ ከእሷ አጅ ወጥቶ እንድትሆን ፈጥና ከልቧ ጥረት አደረገች፡፡በልጅዋ ልብ ውስጥም እግዚአብሔርን ማፍቅርና ለእግዚአብሔር ታማኝ የመሆን ስሜት እንዲያድግበት ተመኘች፡፡ ይህም በታማኝነት ወዲያውኑ በተግባር ተፈፀመ፡፡ እናቱ እሱን ለማስተማር በተሸከመችው ኃላፊነት በትምርቱ ውስጥ የተካተቱ የእውነት መሠረተ ሐሳቦች በእሷም ትምህርት ሆነዋት የነበሩ ሲሆን ሙሴንም በኋላ የመጡ ማራኪ ነገሮች ሊያስለውጡት አልቻሉም፡፡EDA 65.2

    በጐሽን ከነበረው አነስተኛ ቤት የዮካቤድ ልጅ ወደፊረኦን ቤተመንግሥት ገባ፡፡ ከዚያም በግብጽ ልዕልት ዘንድ የሚወደድና የሚፈቀር ልጅ ሆነ፡፡ በግብጽ ውስጥ በነበሩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙሴ ከፍተኛ መህበራዊና ወታደራዊ ሥልጠና አገኘ፡፡ በታላቅ የግል ማራኪነቱ በቅርፁ እና በባህሪይው በሚገባ የተኮተኮተው አእምሮና ልኡላዊ ይዘቱ እውቅ ወታደራዊ መሪ በመሆኑም የወገኖቹ መመኪያና ኩራት ሆነ፡፡ የግብጽ ንጉሥ ጭምር የካህናት ጉባኤው አባል ነበር፡፡ ሙሴ ደግሞ ምንም እንኳን ከአረመኔዎች አምልኮ ጋር ለመሳተፍ ፈቃደኛ ሳይሆን ቢቆይም በግብጻዊያን የሃይማኖት ሚስጥሮች ሁሉ እንዲገባ የጐተጉቱት ነበር፡፡ በዚህ ግብጽ እጅግ ኃይለኛ እንደሆነች ባለችበት ጊዜና እጅግ በከፍተኛ ደረጃ ከሌሎች ሕዝቦች በበለጠ ሥልጣ ላይ ባለችበት በዚሁ ዘመን ሙሴ ይህች ዓለም ልትሰጥ የምትችለውን እጅግ ከፍተኛ ታሳቢ ወራሽ ልዑለ በሚሆንበት ማዕረግ ላይ ነበር፡፡ ለእግዚአብሔር ክብር ለተጣሉና ለተረሱ ወገኖቹ እድገት ሙሴ በግብጽ መንግሥት ያገኘውን ክብር በመስዋዕተነት ከፈለ፡፡ ከዚያ በኋላ ፍፁም ልዩ በሆነ መንገድ እግዚአበሔር እርሱ የሚሰለጥንበትን ሁኔታ አዘጋጀ፡፡EDA 65.3

    ሙሴ አሁንም ቢሆን ለሕይወቱ ለሚሆን ሥራ ገና አልተዘጋጀም ነበር፡፡ በመለኮታዊ ኃይል ላይ የመመካትን ትመህርት ገና መውሰድ ነበረበት፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማ መን እንደነበር አላወቀም ነበርና ተሳሳተ፡፡ እስራኤልን በጦር ኃይል ነፃ ማውጣት እንዳለበት አድርጐ ያስብ ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል ቆርጦ ተነሳ፡፡ ሞከረም፡፡ ነገር ግን በሁሉም ሙከራዎቹ ወደቀ፡፡ በውድቀቱም ተስፋ ቆርጦ በስደት ወደሌላ አገር ሄደ፡፡EDA 66.1

    በሚዲያን በረሃ ሙሴ በግ ጠባቂ ሆኖ አርባ ዓመታትን አሳለፈ፡፡ ሕይወቱ በነበራት ተልዕኮ ለዘላለም ተቆርጣ ተለይታ የነበረችው ትሟላ ዘንድ የሚያስችላትን ትምህርት መከታተል ነበረበት፡፡ ያልተማረና ሥርዓት የሌለውን ሐብረተሰብ ለመምራት መጀመሪያ ራስን መቆጣጠር መቻል ያስፈልጋል፡፡ ለበጐች እና ለየዋህ ግልገሎች እንከብካቤ በማድረግ ታማኘና ታጋሽ የእስራኤል ሕዝብ እረኛ መሆንን እየተለማመደ መማረ ነበረበት፡፡ የእግዚአብሔር ተወካይ ይሆን ዘንድ ከእርሱ መማር አስፈለገው፡፡EDA 66.2

    በግብጽ ውስጥ በነበረ ጊዜ ዙሪያውን የከበበው የሚስብ ነገር፤ የውድ እናቱ ፍቅር የንጉሡ የልጅ ልጅ በመሆን የነበረው ደረጃ በአስር ሽህ ዓይነት ሁኔታ የከበበው የምቾትና የክፉ ሥራ፣ እጅግ የረቀቀ የሃሰት ሃይማኖት ተንኮልና ሚስጥር በአእምሮውና በባህሪው ላይ ተጽዕኖ አሳድሮበታል፡፡ ቀላል በነበረው የበረሃው ኑሮው ውስጥ ይህ ሁሉ ተወግዶለታል፡፡EDA 67.1

    ግርማ ሞገስ በተላበሱ ተራራዎች ብቸኝነት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ብቻውን ነበር፡፡ በየቦታውም የእግዚአብሐር ስመ ተጽፎ ነበር፡፡ ሙሴ ጌታ ባለበት አካባቢ የተቀመጠና በርሱ ኃይልም የተከበበ ይመስል ነበር፡፡ የራሱ መጋቢ ብቻ መሆኑ እዚህ ላይ አበቃ፡፡ ወሰን የሌለው አምላክ ባለበት ሥፍራ ሰው ምን ያክል ደካማ ምን ያክል ለራሱ የማይበቃ፣ ምን ያክል አርቆ መመልከት የማይችል እንደሆነ ተገነዘበ፡፡EDA 67.2

    እዚህ ላይ ሙሴ ባሳለፋቸው ዘመናት አድካሚና ለሰው ተጨናቂ በነበረው ሕይወቱ ውስጥ መለኮታዊ የሆነው ኃይል ባጠገቡ እንደነበረ ተረዳ፡፡ ክርስቶስ በስጋ የሚገለጥበትን ጊዜ በጉጉት መናፈቅ ብቻ ሳይሆን ክርስቶስ እስራኤላዊያን በሚጓዙበት ሁሉ ከሚያስተናግዳቸው ጋር አብሮ እንዳለ ተመለከተ፡፡ ሰዎች በማይረዱለትና ውክልናው በተዛባበት ጊዜ ቅሬታና ስድባቸውን እንዲሰማላቸው በሚጠይቁት ሰዓት አደጋና ሞትን ለመጋፈጥ በተጋለጠ ጊዜ መታገስ ተችሎት ነበር፡፡ «የማይታየውን እርሱን እንዳየ ያክል ይሆን ነበር፡፡» አብ 11፡27EDA 67.3

    ሙሴ እግዚአብሔርን ማሰብ ብቻ ሳይሆን ተመለከተው እግዚአብሔር በራዕይ እፊቱ ይቀርብ ነበር፡፡ የእርሱ ፊት ለሙሴ ተሰውሮበት አያውቅም ነበር፡፡ እምነት ለሙሴ በግምት የሚከናወን ሙከራ አልነበረም፡፡ እውን ነበረ እንጅ፡፡ እግዚአብሔር በተለይ የእርሱን ሕይወት እንደገዛ ያምን ነበር፡፡ እናም ለሁሉም ዝርዝር ሥራዎች ሁሉ እርሱን ያመሰግን ነበር፡፡ እያንዳንዱን ፈተና ለመቋቋም በእርሱ ይተማመን ነበር፡፡EDA 68.1

    በእርሱ የተመደበውንና የተጣለበትን ኃላፊነትም እጅግ ድንቅ በሆነ መልኩ ስኬታማ እንዲሆን ለማድረግ አሰበ፡፡ ስለሆነም እምነቱን በሙሉ በመለኮት ኃይል ላይ አኖረ፡፡ እርዳታ እንደሚያስፈልገውም ተገነዘበ፡፡ እንዲሰጠውም ጠየቀ፡፡ በእምነትም አገኘ፡፡ የማያቋርጥና የማይወድቅ ኃይል ስለ ተረጋገጠለት እርምጃውን ወደፊት ቀጠለ፡፡EDA 68.2

    በበረሃ የአርባ ዓመት ቆይታ የሥልጠና ጊዜው ውስጥ ሙሴ ያካበተው ልምድ ይኸን ይመስል ነበር፡፡ እንዲህ ዓይነት ልምድ ለማካበት ማለቂያ የሌለው ጥበብ በረዥም ዓመታትም ሆነ በውድ ዋጋ የሚገኝ አይደለም፡፡EDA 68.3

    እዚያ በተሰጠው ሥልጣና የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም በዚያ የተሰጡ ትመህርቶች ከአስራኤል ታሪክ ጋር መያያዛቸው ብቻ ሳይሆን ከዚያ ቀን አንስቶ እስከአሁን ድረስ ያለውን የዓለምን ዕድገት መናገራቸው ነው፡፡ ለሙሴ ታላከነት ከፍተኛው ምስክር በሕይወቱ ላይ በመንፈስ የተላለፈው ቃል ነው፡፡ «እግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል ዘንድ አልተነሳም፡፡» ዘዳ 34፡10EDA 68.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents