Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 35—ከዚያ በኋላ የሚኖረው ትምህርት ቤት

  ‹‹ፊቱን ያያሉ፣ ስሙም በግንባሮቻቸው ላይ ይሆናል››EDA 336.1

  ሰማይ፤ ፍጥረተ ዓለማት የጥናት መስክ የሚሆኑባትና ዘለዓለማዊዩ አምላክም መምህር የሚሆንበት ትምህርት ቤት ነው፡፡ የዚህ ትምህርት ቤት ቅርንጫፍ በኤደን ተቋቁሞ ነበር፡፡ የቤዛነትና የማዳን ዕቅድም ተፈጽሞአል፡፡ ትምህርትም በኤደን ትምህርት ቤት ውስጥ እንደገና ይጀምራል፡፡ ‹‹ዐይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰው ልብም ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው፡፡›› 1ኛ ቆሮ 2፡9 ስለ እነዚህ ነገሮች ዕውቀት ማወቅ የሚቻለው በርሱ ቃል አማካይነት ብቻ ነው፡፡ ያውም እንኳ በከፊል የሚገለጥ ብቻ ነው፡፡EDA 336.2

  ‹‹አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛው ምድር አልፏልና ባህርም ወደፊት የለም፡፡ ቅድስቲቱ ከተማ አዲሲቱም እየሩሳሌም ለባልዋ እንደተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ፡፡›› ራዕ ዮሐ 21፡1፣2EDA 336.3

  ‹‹ለከተማይቱ የእግዚአብሄር ክብር ስለሚያበራላት - - - ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበራላት አያስፈልጋትም ነበር፡፡›› ራዕ ዮሐ 21፡23EDA 336.4

  በመጀመሪያ በኤደን በተቋቋመው ትምህርት ቤትና በእንግዲህ በኋላ በሚኖረው ትምህርት ቤት መካከል የዚች ዓለም አጠቃላይ የታሪክ ሂደት ይታያል፡፡ የሰው ልጅ የተላለፋቸው ስህተቶችና ያሳለፈው የሥቃይ ታሪክ፤ የመለኮት መስዋዕትና በሞትና በኃጢአት ላይ ድል የመንሳቱ ታሪክም በዚያ ውስጥ ይቀመጣል፡፡ በዚያ የመጀመሪያ የኤደን ትምህርት ቤት ውስጥ ሁኔታዎች ሁሉ በወደፊቱ የሕይወት ትምህርት ቤት ውስጥ አይኖርም፡፡ ለፈተና ዕድል የሚከፍት በጎውንና ክፉውን የሚያሳውቅ ዛፍ አትኖርም፡፡ ፈታኝም የለም፡፡ ስህተት የመሥራት ዕድልም የለም፡፡ እያንዳንዱ ባህሪይ የክፉን ፈተና ተቋቁሞ አልፏል፡፡ ካሁን በኋላ ማንኛውም በቀላሉ በርሷ ኃይል የሚሳብ አይሆንም፡፡EDA 336.5

  ‹‹ድል ለነሳው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ አንዲበላ እሰጠዋለሁ፡፡›› ይላል ክርስቶስ ራዕ ዮሐ 2፡7 በኤደን ውስጥ የተሰጠችው የሕይወት ዛፍ ቅድመ ሁኔታ ያለባት ነበረች እሷም መተላለፍ ተፈፀመባት የወደፊቱ ሕይወት ስጦታ ግን ምንም የሌለበት ፍፁምና ዘለዓለማዊ ነው፡፡EDA 337.1

  ነብዩ እነሆ እንዲህ ይላል ‹‹እንደ ብርሌ የሚያንፀባርቀውን የሕይወትን ውሃ ወንዝ አሳየኝ›› ‹‹በወንዙም ወዲያና ወዲህ - - - የሕይወት ዛፍ ነበር›› ‹‹ሞትም ከእንግዲህ ወዲያ አይሆንም ኃዘንም ቢሆን ወይም ጩኽት ወይም ስቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና›› ራዕይ ዮሐ 22፡1 ፣ 22፡2፣ 21፡4EDA 337.2

  ‹‹ ሕዝብሽም ሁሉ ፃዲቃን ይሆናሉ፡፡
  እኔም እከብር ዘንድ የአታክልቴን ቡቃያ
  የእጄ ሥራ የምትሆን ምድሪቱንም
  ለዘለዓለም ይወርሳሉ፡፡›› ኢሳ 60፡21
  EDA 337.3

  የሰው ልጅ እንደገና በርሱ ፊት ተመልሶ እንደ ቀድሞው በእግዚአብሔር እጅ ይማራል፡፡ እንደዚህ ይላል ‹‹ስለዚህ ወገኔ ስሜን ያውቃል ስለዚህም የምናገር እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያውቃሉ እነሆ እኔ ነኝ፡፡›› ኢሳ 52፡6EDA 337.4

  ‹‹እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፡፡ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፡፡ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፡፡ ራዕ ዮሐ 21፡3EDA 337.5

  ‹‹እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነፁ ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፡፡ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልክታል በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው በነርሱ ላይ ያድርባቸዋል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፡፡ ከእንግዲህም ወዲህ አይጠሙም ፀሐይም ትኩሳትም ሁሉ ከቶ አይወርድባቸውም በዙፋኑ መካከል ያለው በጎ እረኛቸው ይሆናልና ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋልና፡፡›› ራዕ 7፡14-17EDA 338.1

  ‹‹ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፡፡ ዛሬስ ከእውቀት ከፍየ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ፡፡›› 1ኛ ቆሮ 13፡12EDA 338.2

  ‹‹ፊቱንም ያያሉ ስሙም በግንባሮቻቸው ይሆናል፡፡›› ራዕ ዮሐ 22፡4 EDA 338.3

  በዚያ ስፍራ እንዳናይ የሚከልለን መጋረጃ ሲወገድልን፣ ዐይናችንም በዚያ የውበት ዓለም ላይ ሲያርፍ አሁን አጉልቶ በሚያሳይ መነጽር እንኳ ገና ጭላንጭሉ ብቻ እናያለን፡፡ የሰማይን ክብር ስንመለከት፣ በቴሌስኮ እንደዚያ ተስተካክለው የምናያቸው ዓለማት የኃጢአት ክፉ ስበት ሲወገድልን መላው ዓለም ‹‹በጌታችንና በአምላካችን ውበት›› ሲገለጽ ምን ዓይነት የጥናት መስክ ነው የሚከፈትልን! በዚያ ስፍራ የሣይንስ ተማሪ የተፈጥሮን መዝገቦች አንብቦ ሲመረምር የክፉ ሕግ ርዝራዦችን ፈልጎ አያገኝም፡፡ የተፈጠሮን ድምጽ እንደ ሙዚቃ ሊሰማ ይችላል፡፡ ነገር ግን አንዳችም የጩኽት ወይም የሐዘን እንጉርጉሮ የለበትም፡፡ በተፈጠሩ ነገሮች ውስጥ ሁሉ ላይ አንድ አይነት የእጅ ጽሁፍ ብቻ ያገኛል፡፡ በሰፊው ይቀዳል፡፡›› እናም በመሬትም ሆነ በባህር ወይም በሰማይ በየትኛውም ቦታ አንዲት የበሽታ ምልክት እንኳ አትኖርም፡፡EDA 338.4

  በዚያ የኤደን ሕይወት ይኖራል፡፡ በዚያ የአትክልት ስፍራና ገነት ሜዳ ላይ፡፡ ‹‹ቤቶችንም ይሠራሉ ይጠቀሙባቸውማል፡፡ ወይንም ይተክላሉ ፍሬውንም ይበላሉ፡፡ ሌላ እንዲጠቀምበት አይሠሩም ሌላም እንዲበላው አይተክሉም፡፡ የሕዝቤ እድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና እኔ የመረጥኳቸው በእጃቸው ሥራ ረዥም ዘመን ደስ ይላቸዋልና፡፡›› ኢሳ 65፡21፣22EDA 339.1

  ‹‹በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉም›› አንዳችም ዓይነት ጉዳት ‹‹አይጎዱም›› ይላል ኢሳ 65፡25 በዚያ ቦታ ሰው ወደ ቀድሞው ንጉሥነቱ ይመለሳል፡፡ ታናናሽ ፍጥረታትም የእርሱን አመራር ይረዳሉ ኃይለኛው ለስላሳ፤ ፈሪውም ልበሙሉ ይሆናሉ፡፡EDA 339.2

  ለተማሪው ዳርቻ ወሰን የሌለው ታሪክና ሊገለጽ የማይችል ሐብት ይከፈትለታል፡፡ በዚህ ቦታ ምቹ ከሆነው ከእግዚአብሔር ቃል መሠረተ በመነሳት ተማሪው ሰፊ የታሪክ መስክና የሰው ልጅ ድርጊቶችን ውጣ ውረድ በሚገዙ መሠረታዊ ሐሳቦች ዕውቀት ያገኛል፡፡ ከዘለዓለማዊዩ ብርሃን ፊት እስከሚቆም ድረስ ሁሉንም ነገር በግልጽ ማየት አይችልም፡፡EDA 339.3

  ከዚያ በኋላ ዘመን ከመጀመሩ አንስቶ እስከ ዘመን መጨረሻ ድረስ ያለው የታላቁ ጦርነት ታሪክ ሂደት እፊቱ ላይ ይከፈትለታል፡፡ የኃጢአት ሐሳብ ታሪክ፤ ጠማማ የሆነው የውሸት ሥራ እጣ፤ ያ ከራሱ ትክክለኛ መስመር ሣይሆን ራስ ሣይሆን ከዚያ በኋላ የተጣመመው እውነት ስህተትን ጥፋትን ድል እንዳደረገ ሁሉም ነገሮች ግልጽ ይደረጋሉ፡፡ በሚታየውና በማይታየው ዓለም መካከል ያለው መጋረጃ ወደ ጎን ይሰባል አስገራሚ ነገሮችም ይገለጣሉ፡፡EDA 339.4

  የእግዚአብሔር ቸርነት በዘለዓለማዊ ብርሃን እስከሚታዩ ድረስ የርሱ መላዕክት የሚያደርጉልንን እንክብካቤና ጥንቃቄ ልናስተውለው አንችልም፡፡ የሰማይ ኃይሎች በሰው ልጅ ጉዳዮች ውስጥ ሁሉ ቀልጣፋ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡ እንደ መብረቅ የሚያበራ ልብስ አዘጋጅተዋል፣ መንገደኞች ሲነጠቁ እንደ ሰው ሆነው መጥተዋል፡፡ በሰዎች ቤት ውስጥ የተደረገላቸውን መስተንግዶ ተቀብለዋል፡፡ ለመሸባቸው እንግዶች በጨለማ ውስጥ እንደ መሪ ሆነው ረድተዋቸዋል፡፡ የጥፋተኛውን ሐሳብ አስለውጠዋል፤ አጥፊው የሰነዘረውንም አቅጣጫውን አስቀይረዋል፡፡EDA 340.1

  ምንም እንኳን የዚህ ዓለም ገዥ ባያውቀውም መላዕክት በምክራቸው ስለ እኛ ተናግረውልናል፡፡ በሰዎች ዐይን ታይተዋል፡፡ የሰዎች ጆሮ የእነሱን ምክር ሰምተዋል፡፡ በምክር ቤት አዳራሾችና በፍርድ አደባባዮች የሰማይ መልዕክተኞች ለተሰደዱና ለተጨቆኑ ሰዎችን መንገድ ተማጽነዋል፡፡ በእግዚአብሔር ልጆች ላይ ስህተትና ስቃይ ሊያመጡ ይችሉ የነበሩትን ሐሳባቸውን ድል አድርገው ክፋታቸውንም አስቀርተዋል፡፡ በሰማዩ ትምህርት ቤት ለሚገኙ ተማሪዎች ይህ ሁሉ ይገለጥላቸዋል፡፡EDA 340.2

  እያንዳንዱ በርሱ መታደግ ደህንነት ያገኘ ሰው ሁሉ በራሱ ሕይወት ውስጥ የመላዕክትን አገልግሎት ያስተውላል፡፡ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ይጠብቀው የነበረው የርሱ መልአክ፤ እርምጃዎቹን ሁሉ ይከታተል የነበረው መልአክ፣ በጥፋት ቀንም ራሱን የሸፈነለት የማረፊያ ቦታውን ያዘጋጀለት፣ በትንሳኤ ጧትም መጀመሪያ ሰላም የሚለው መለአክ፣ ከርሱ ጋር መነጋገር ማለት ምን ዓይነት ይሆን! መለኮት በግለሰቡ ሕይወት ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ስለ ማዳኑ፤ ስለሰማያዊው ትብብር ለሰው ልጅ ስላደረገው እያንዳንዱ መልካም ሥራ ታሪክ መማር እንዴት ድንቅ ይሆን!EDA 340.3

  በሕይወት ውስጥ የነበሩ ውስብስብ ገጠመኞች ሁሉ በዚያ ጊዜ ግልጽ ይደረጋሉ፡፡ ለእኛ ምስቅልቅልና ተስፋ የሚያስቆርጡ መስለው ይታዩን የነበሩ ሐሳቦችና እቅዶች እጅግ ትልቅ፣ የሁሉ የበላይ ድል አድራጊ ሐሳቦችና መለኮት የተዋሐዳቸው ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡EDA 341.1

  በዚያ ስፍራ ራስን ባለመውደድ መንፈስ የታገሉ ሁሉ የሥራቸውን ፍሬ ያገኛሉ፡፡ የእያንዳንዱ ትክክለኛ መሠረተ ሐሳብና ክቡር ተግባር ውጤት ይታያል፡፡ አንዳንድ ነገር በዚህም ዓለም እንደምናየው ዓይነት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ለበጎ አድራጊው በዚህ በአሁኑ ሕይወቱ ለሚሠራው ክቡር ነገር በዚህ ዓለም የሚያገኘው ዋጋ እጅግ በጣም ትንሽ ኢምንት ነው፡፡ ከአቅማቸው በላይ እና ከእውቀታቸው በላይ ለሆነባቸው ሰዎች ራስን ባለመውደድና ያለመሰልቸት የሠሩ ስንቶች ናቸው ወላጆችና መምህራን በመጨረሻው እንቅልፍ ያርፋሉ፡፡ እድሜ ልካቸውን የደከሙበትም ሁሉ በከንቱ ተደፍኖ የቀረ ይመስላል፡፡ ታማኝነታቸው የበረከት ምንጮችን ከፍቶ ምን ጊዜም ያለማቋረጥ እንደሚፈስ አያውቁ ይሆናል፡፡ ያሰለጠኗቸው ልጆቻቸው ለወገኖቻቸው በረከቶችና የመንፈስ ማነቃቂያ እንደሚሆኑና ፍቅራቸውም አንድ ሺህ ጊዜ አጥፍ ሆኖ ለብዙዎች እንደሚዳረስ የሚያዩት ግን በእምነት ብቻ ነው፡፡ የብርታት፣ የተስፋና የድፍረት መልዕክቶችን ለማዳረስ ወደ ዓለም የተላኩ፤ የበረከት ቃሎችን በየሃገሩ ለሚገኙ ልቦች ተሸክመው የሚጓዙ አንዳንድ ሠራተኞች አሉ፡፡ ነገር ግን እንደዚያ በብቸኝነትና በጭለማ መከራቸውን ያዩ ቢሆንም ስለ ውጤቱ የሚያውቁት ጥቂት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ችሎታዎችን መታደል፣ ሸክሞችን መቻል ሥራንም መሥራት ያለ ነው፡፡ ሰዎች ዘርን ይዘራሉ ከመቃብራቸውም ላይ ሌሎች በረከትን ያጭዳሉ ይሰበስባሉ፡፡ ፍሬውን ሌሎች የሚበሉት ዛፍ ይተክላሉ፡፡ በችሎታዎቻቸው ለዘለቄታው ሥራዎችን ማያያዛቸውን አሁን አያውቁም፡፡ ከዚህ በኋላ በሚኖረው ሕይወት የእነኝህ ሥራዎችና ዐፀፋዊ ምላሻቸው ሁሉ ይታያሉ፡፡EDA 341.2

  እግዚአብሔር ስላደለን እያንዳንዱ ስጦታዎች ሰዎችን ራስ ወዳድ ወደአልሆነ ጥረት የሚመሩ ስጦታዎች ታሪካቸው በሰማይ ይመዘገባል፡፡ ይህ ደግሞ ሰፊ እንደመሆኑ ለመከታተል፣ በእኛ ጥረት ልባቸው የተነሳሳና የተከበረላቸውን ሰዎች ለማየት የእውነተኛ መሠረተ ሐሳቦችን ሥራ የማዳረስ ታሪካቸው፣ ይህ ከሰማዩ ትምህርት ቤት ጥናቶች አንደኛውና ሽልማትም ነው፡፡EDA 342.1

  በዚያ ስፍራ እኛ እንደ ታወቅን ሁሉ እናውቃለን፡፡ በዚያ እግዚአብሔር ነፍስ ውስጥ የተከላቸው ፍቅርና ርህራሄዎች ፍፁም እውነትና እጅግ ጣፋጭ የሆነ ቦታቸውን ያገኛሉ፡፡ ቅዱሳን ከሆኑ ፍጡሮች ጋር የሚኖረው ንፁህ ግንኙነት፣ ከተባረኩ ማለዕክትና በዘመናቱ ሁሉ ከነበሩ ታማኞች ጋር የሚኖረው የተዋሃደ ማኅበራዊ ሕይወት፤ ‹‹በሰማይና በምድር ውስጥ ሁሉ ያሉት ቅዱሳን ቤተሰቦች›› ሁሉ ጋር የሚኖረው የተቀደሰ ግንኙነትና ትስስር፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከዚህ በኋላ በሚኖረው ሕይወት የሚገኑ ናቸው፡፡EDA 342.2

  በዚያም ሙዚቃ ይኖራል፡፡ መዝሙርም ጭምር፡፡ እንዲህ ዓይነት ሙዚቃና መዝሙሮች፣ በእግዚአብሔር ዐይን ብቻ የሚጠበቁና ማንም መዋቲ ያልሰማቸውና በአእምሮውም አስተውሎአቸው የማያውቅ ናቸው፡፡EDA 342.3

  ‹‹በዚያ ሥፍራ የሚዘምሩና በመሣሪያዎቹ የሚጫወቱ ይኖራሉ፡፡›› መዝ 87፡7 እነዚህ ድምፃቸውን ያነሳሉ እልልም ይላሉ ስለ እግዚአብሔር ክብርም ከባህር ይጣራሉ፡፡›› ኢሳ 24፡14EDA 342.4

  ‹‹እግዚአብሔርም ጽዮንን ያጽናናል፡፡ በርሷም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፡፡ ምድረ በዳዋን እንደ ኤደን በረሃዋንም እንደ እግዚአብሔር ገነት ያደርጋል ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምጽ ይገኝበታል፡፡›› ኢሳ 51፡3EDA 343.1

  በዚያ ቦታ ኃይል ሁሉ ይዳብራል እያንዳንዱ ችሎታም ይጨምራል፡፡ እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነው የሥራ ድርጅት ይካሄዳል፣ በልብ የተቀመጠው እጅግ ያለቀው ምኞት ይደረስበታል፣ እጅግ ከፍተኛ ዓላማም ይጨበጣል ይታያል፡፡ አሁንም እንደገና ከፍተኛ መወጣት የሚኖርበት ሐሳብ ያጋጥማል፡፡ አዲስ አስደናቂ የሆኑ ነገሮች፤ የምናስተውላቸው አዲስ እውነታዎች የአካል፣ የአእምሮና የመንፈስ ኃይሎችን የሚጠይቁ አዲስ አላማዎች ይኖራሉ፡፡EDA 343.2

  የዩኒቨርስ መዝገቦች ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ያጠኗቸው ዘንድ ክፍት ይሆናሉ፡፡ ሊነገር በማይቻል ደስታ ያልወደቁ ፍጡራን ወደያዙት ደስታና ጥበብ ውስጥ እንገባለን፡፡ በእግዚአብሄር የእጅ ሥራዎች ላይ ልብን አሰባስቦ ከዘመን እስከ ዘመናት በተደረገው ትኩረት ከተገኙት መዝገቦች እንካፈላለን፡፡ የዘለዓለም ዓመታትም ባለፉ ቁጥር የበለጠ ክብር ያለው ራዕይ ማምጣታቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ‹‹ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ፡፡›› ኤፌ 3፡20 እግዚአብሔር የሚያካፍለን ስጦታዎች ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የሚቀጥሉ ናቸው፡፡EDA 343.3

  ‹‹አገልጋዮቹ ያመልኩታል፡፡›› ራዕ ዮሐ 22፡3 በሰማይ ላይ የሚኖረው ሕይወት በምድር በሚኖረው ሕይወት ይጀምራል፡፡ በምድር ላይ የሚኖረው ትምህርት፤ በሰማይ ለሚገኙ መሠረታዊ ሐሳቦች መነሻ ነው፡፡ በዚህ ዓለም ያለው የሕይወት ሥራ በዚያ ለሚኖረው የሕይወት ሥራ የሥልጠና ጊዜ ነው፡፡ አሁን በባህሪይ፤ እና በቅድስና አገልግሎት ላይ በመሆን ላይ ያለነው ወደፊት ለምንሆነው እርግጠኛ ምሳሌ ነው፡፡EDA 343.4

  ‹‹የሰው ልጅ ሊያገለግል እንጅ - - - - ሊያገለግሉት አልመጣም፡፡›› ማቴ 20፡28 ክርስቶስ በዚህ በምድር የሠራው ባላይኛው የሚሠራውን ነው፡፡ በዚህ ዓለም ከርሱ ጋር በመሥራታችን ለሚኖረን ዋጋም በሚመጣው ዓለም ከርሱ ጋር ለመሥራት ታላቅ ኃይልና ጥቅሙም ሰፊ ይሆናል፡፡EDA 344.1

  ‹‹ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል እግዚአብሔር እኔም አምላክ ነኝ፡፡›› ኢሳ 43፡12 በዘለዓለም ቤትም እንደዚሁ ነው የምንሆነው፡፡EDA 344.2

  ታላቁ ተጋድሎ በዘመናት ሁሉ እንዲቀጥል ተደርጎ የነበረው ለምንድን ነው? ሰይጣን በአመጽ እንደመጣ ወዲያውኑ በአጭሩ እንዲቀጭ ከማድረግ ይልቅ በሕልውናው እንዲቀጥል የተደረገው ለምን ነበር? የእግዚአብሔር ፍርድ በክፉ ላይ ምን እንደሚመስል መላው ዩኒቨርስ ያምንበት ዘንድ ኃጢአትም ዘለዓለማዊ ውግዘት ይደርስበት ዘንድ ነው፡፡ በደሙ የመዋዤት ዕቅድ ውስጥ፤ ዘለዓለማዊነት ራሷ ጨርሳ ፈጽሞ ልትደርስበት የማትችለው ከፍታዎችና ጥልቀቶች መላዕክትም ሊመለከቱዋቸው የሚወድዱት ድንቅ ነገሮች ሞልተዋል፡፡ ከፍጡራን ሁሉ የዳኑት ብቻ በራሳቸው ኑሮ ውስጥ ከኃጢአት የተደረገውን ጦርነት አውቀውታል፡፡ ከክርስቶስ ጋር ተቀጥቅጠው ተቀርፀዋል፡፡ መላዕክት እንኳ ሊያደርጉት እድሉ ያልነበራቸውን እነርሱ ከእርሱ ጋር ስቃዩን ተጋርተዋል፡፡ ታዲያ በኅጢአት ያልወደቁ ፍጡራን የማያገኑትን ስለቤዛነት የመታደግ ጥበብ (ሣይንስ) ምስክርነት አይሰጡበትምን?EDA 344.3

  አሁንም ቢሆን ‹‹በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ›› ‹‹ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ በቤተክርስቲያን በኩል›› ተገለጠ እና እርሱም ‹‹በክርስቶስ የሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የፀጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ከርሱ ጋር አስነሳን በክርስቶስ የሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከርሱ ጋር አስቀመጠን፡፡›› ኤፌ 3፡10፣ 2፡6፣7EDA 345.1

  ‹‹ሁሉም በመቅደሱ ምስጋና ይላል፡፡›› መዝ 29፡9 ነፃ የወጡት ሰዎች የሚዘምሩት መዝሙር በሕይወታቸው ያጋጠማቸውን ያሳለፉትን ኑሮ የሚመለከት ሆኖ የእግዚአብሔርን ክብር ይገልፃሉ፡፡ ‹‹ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፣ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ በመንገድህ ፃድቅ ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና የጽድቅም ሥራህ ስለተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፡፡ በፊትህም ይሰግዳሉ፡፡ እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ፡፡›› ራዕ 15፡3 EDA 345.2

  በዚህ ምድራዊ ሕይወታችን ምንም እንኳ በኃጢአት የተገደበ ቢሆንም እጅግ ታላቁ ደስታቸውና ከፍተኛው ትምህርታቸው አገልግሎት ላይ ይውላል፡፡ በወደፊቱ ሁኔታም ኃጢአት በተሞላው ሰብዓዊነት ውሱን መሆን ቢደናቀፍም ታላቁ ደስታችንና ከፍተኛው ዕውቀታችን ሊገኝ የሚችለውና የምንመሰክረውም፤ በአዲስ መልክ እየተማርን ‹‹የዚህ ምስጢር ክብረ - - - ምስጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው፡፡›› ቆላ 1፡27EDA 345.3

  ‹‹ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም፡፡ ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እሱን እንድንመስል እናውቃለን፡፡›› 1ኛ ዮሐ 3፡2EDA 345.4

  ከዚያም በርሱ ሥራዎች ውጤት ውስጥ፤ ክርስቶስ ካሳውን አስቀምጦ በዚያ ማንም ሰው ሊቆጥረው በማይችል ሕዝብ ፊት ‹‹በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው፡፡›› ይሁዳ 24 በደሙ የዋዣንና ሕይወቱም ለትምህርታችን የሆነ እርሱ ‹‹ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፡፡›› ኢሳ 53፡11EDA 346.1

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents