Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  የሕይወት ሥነ-ሥርዓትን መጋጠም

  ከቤትና ከትምህርት ቤት ሥነ-ሥርዓት ባሻገር ከሕይወት ሥርዓት ጋር መገናኘት አለበት፡፡ ለእያንዳንዱ ልጅና ለእያንዳንዱ ወጣት ይኽንን እንዴት በጥበብ መያዝ እንዳለበት ግልጽ ሊደረግለት ይገባል፡፡ እርግጥ ነው እግዚአብሔር ሁላችን ይወደናል፡፡ ደስ የሚያሰኘንን ነገር ሁሉ ያደርግልናል፡፡ ትዕዛዙን ደግሞ ሁልጊዜ ብናከብር ስቃይEDA 332.3

  የሚባለውን ነገር ባለወቅነውም ነበር፡፡ እናም በዚህ ዓለም ውስጥ በኃጢአት ምክንያት ሥቃይ መከራ ሸክም ወደ እያንዳንዱ ሰው ሕይወት መምጣቱ ያንኑ ያክል እውነት ነው፡፡ ልጆች ወጣቶች የዚህን ዓለም ችግሮችና ሸክሞች በጀግንነት እንዲጋጠሙአቸው አድርገን በማስተማር ለእድሜልካቸው ጥሩ ትምህርት ልንሰጣቸው እንችላለን፡፡ ርህራሄ ስናደርግላቸው የግል ኃዘንን መግለጽ ማለት ፈጽሞ መሆን የለበትም፡፡ የሚያስፈልጋቸው ነገር ቢኖር ከሚያዳክማቸው ይልቅ የሚያነቀቃና የሚያበረታታቸው ምክር ብቻ ነው፡፡EDA 333.1

  ይህ ዓለም የጦርነት ሜዳ እንጅ የሰልፍ ትርኢት የሚታይበት አደባባይ አለመሆኑን ይማሩ፡፡ ሁሉም የተጠሩት እንደ ጥሩ ወታደሮች ችግርን እንዲቋቋሙ ነው፡፡ ጠንካራና በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች መሆን አለባቸው፡፡ እውነተኛው የባህሪ ፈተና ሸክሞችን ለመቻል ፈቃደኛ በመሆንና ምድራዊ ዕውቅናም ሆነ ሽልማት ባያስገኝም ከባዱን ቦታ በመሸፈን መደረግ ያለበትን ሥራ መሥራት እንደሚገባቸው ይማሩ፡፡EDA 333.2

  ፈተናን መጋፈጥ ማለት ሁኔታውን ተጋጥሞ መለወጥ መቻል እንጅ ከፈተናው ለማምለጥ መሞከር ማለት አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ ለቀድሞውም ለኋለኛውም ሥርዓት ሁሉ የሚሠራ ነው፡፡EDA 333.3

  አንድ ልጅ በሕፃንነቱ ማግኘት ያለበትን ትምህርት ወይም ሥልጠና ችላ ማለት ወይም በንቀት መመልከት እና ያላቋረጠ ወደ ጥፋት የማዘንበል ሥራውን ዝም ብሎ ማየት የወደ ኋላ ትምህርቱን አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ሥነ-ሥርዓትን ራሱን የሚቆጠቁጥ መራራ ዓይነት ነገር ያስመስለዋል፡፡ ለትንንሽ ልጆች በእርግጥም መራራ መሆን አለበት፡፡ የተፈጥሮ ፍላጎቶችንና አዝማሚያዎችን የሚፃረር እንደመሆኑ ሥቃይ ያለበት መሆኑ አይቀርም፡፡ ነገር ግን ሥቃይ በከፍተኛ ደስታ መተካት አለበት፡፡EDA 333.4

  ልጆችና ወጣቶች እያንዳንዷን ስህተት እያንዳንዷ ጥፋትና ችግር ድል ስትደረግ ለተሻሉ ከፍተኛ ነገሮች የመንገድ ምልክት ድንጋዮች እንደሚሆኑ ይማሩ፡፡ በሕይወት ውስጥ የተሳካላቸው ሰዎች ሁሉ በእንዲህ ዓይነት ገጠመኝ ውስጥ አልፈው ነው፡፡EDA 334.1

  ‹‹ታላላቅ ሰዎች የደረሱበትና ያስመዘገቡት ውጤት፣
  በድንገት በርረው ያረፉበት አይደለም
  ነገር ግን ጓደኞቻቸው በተኙ ጊዜ
  በምሽት ሁሉ ይሠሩ ነበር፡፡››

  ‹‹ እጫማችን ሥር ባሉ ነገሮች ጀምረን በሚገባ
  ባወቅናቸውና በሰለጠንባቸው ጉዳዮች
  ኩራትንም ጥለን ቀልባችንንም አጥተን
  በየሰዓቱ ያጋጠሙንን ነገሮች ድል አደረግን፡፡››

  ‹‹ በየዕለቱ የሚያጋጥሙ የተለመዱ ድርጊቶች
  በአንድ ሰዓት ላይ ታይተው ወዲያውኑ የሚጠፉ
  ደስታችንና ቅሬታዎቻችን ሁሉ
  ወደላይ የምንወጣባቸው ዙሮች ናቸው፡፡››
  EDA 334.2

  ማየት ያለብን ‹‹የማይታየውን እንጅ የሚታየውን ባንመለከት ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን - - - የሚታየው የጊዜው ነውና የማይታየው ግን የዘለዓለም ነውና፡፡›› 2ኛ ቆሮ 4፡18 የራስ ወዳድነት ስሜትና አዝማሚያዎችን ወዲያ በመጣል በለወጡ የከበረውንና ዘለዓለማዊውን ለማግኘት ዋጋ የለሽ የሆነውን ጊዜያዊውን መጣል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ወሰን የሌለው ትርፍ እንጂ መስዋዕትነት አይደለም፡፡EDA 334.3

  ‹‹አንድ የተሻለ ነገር›› የሚለውን አነጋገር በትምህርት ውስጥ የማስጠንቀቂያ ቃል ነው፡፡ የእውነተኛ ሕይወት ሕግ ነው፡፡ ክርስቶስ እንድንሠራ ለሚጠይቀን ነገር ሁሉ በምትኩ አንድ የተሻለ ነገር አስቀምጦልናል፡፡ ወጣቶች ብዙ ጊዜ ክፉ የማይመስሉ ነገር ግን ከፍተኛውን መልካም ነገር የሚጎዱ ቁሳቁሶችን ዝንባሌዎችንና የደስታ ጨዋታዎችን ይወድዳሉ፡፡ ሕይወትን ቅዱስ ከሆነው የዓላማ መንገድ ያመጣታል፡፡ የኃይል እርምጃዎች ወይም ቀጥተኛ ውግዘት ወጣቶችን ጥሩ ነው ብለው ከያዙት ነገር አይመልሳቸውም፡፡ ለእይታ ከሚደረጉ ነገሮች ከጉጉት ወይም መጥፎውን ነገር ሁሉ አብዝቶ ከመውደድ ይልቅ ወደተሻለው መልካም ነገር ያምሩ፡፡ ወደ በለጠውና ውብ ወደሆነው፣ እጅግ ከፍተኛ ከሆኑ መሠረታዊ ሐሳቦች ጋር ቅዱስ ከሆኑ ሕይወቶች ጋር እንዲገናኙ አድርጓቸው፡፡ አጠቃላይ ‹‹እጅግ ግሩም ድንቅ›› በሆነው እንዲያዙ ወደ እርሱ ምሯቸው፡፡ አንድ ጊዜ በርሱ ላይ ሲያተኩሩ ሕይወት ማዕከሏን ታገኛለች፡፡ ንቃት፤ ከልብ መመሰጥ የወጣቱ የፍቅር ከበሬታ፣ እውነተኛ ግብ ይኖራቸዋል፡፡ ተግባር፤ ደስታ፣ መስዋዕትነት ደግሞ ፍስሃ ትሆናለች፡፡ ክርስቶስን ለማክበር እንደ እርሱም ለመሆን፤ ታላቁ የሕይወት ዓላማና ትልቁ ደስታዋም ለርሱ ለመሥራት ነው፡፡EDA 335.1

  ‹‹የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል፡፡›› 2ኛ ቆሮ 5፡14EDA 335.2

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents