Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ከድካም ወደብርታት

  የክርስቶስን የማሰለጠኛ ዘዴ እንደ ጴጥሮስ ታሪክ በጥሩ ሁኔታ የሚገልፀው ሌላ የለም፡፡ ደፋር ቁጡ ልበሙሉ ለማስተዋልና ለተግባር ፈጣን በግንኙነቱ ቁጥብ ሆኖ ሳለ ለጋስ የነበረው ጴጥሮስ ለስህተት የሚፈጥን ወዲያውኑ መልሶ ለመታረምም እጅግ ቀልጣፋ ነበር፡፡ ከጋለ ልቦና የመነጨው ታማኝነቱና በክርስቶስ የነበረው ተመስጽኦ አነስተኛ እውቅናና ዝቅተኛ ግምት የሚሰጣቸው አልነበሩም፡፡ በትዕግሥትና ለየት ባለ ፍቅር አዳኞችን ይኸንን ትዕግት የሌለውን ተማሪውን በራሱ የሚተማመን እንዲሆንና ሰብዓዊነትን ታዛዥነትንና እምነትን ይማር ዘንድ ለብቻው ወሰደ አነጋገረው፡፡EDA 95.3

  የተሰጠው ትምህርት ግን በከፊል ነበር፡፡ ምክንያቱም ገና ራስን አሳልፎ በመስጠት አልተረጋገጠምና፡፡EDA 96.1

  በራሱ ልብ ላይ ከባድ ሸክም የነበረበት የሱስ የርሱን መከራና ስቃይ ደቀመዛሙርት አሻግረው ያዩት ዘንድ መንገዱን ሊከፍትላቸው ፈለገ፡፡ ዐይኖቻቸው ግን እንደተያዙ ነበሩ፡፡ ጥበቡ ገና አልታወቀም ነበርና ማየት አልቻሉም፡፡ ክርስቶስ እንደዚያ በስቃይ በማንገላታበት ጊዜ ለማየት ያልፈለገውና የተሳቀቀው ጴጥሮስ በልብ ንጽህና «አይሁንብህ ጌታ ሆይ ይህ ከቶ አየድረስብህ» አለው (ማቴ 16፡22) በበ የእሰ ቃላት የአሥራ ሁለቱን ደቀመዛሙርት ሀሳብና ፍላጐት የገልፃል፡፡EDA 96.2

  እንደዚህ እያሉ ቀጠሉ፡፡ ቀውሱም እየተቃረበ መጣ፡፡ የመስቀሉን ጉዳይ ሳያስቡ፤ እንዲሁ በጉራ ይገባኛል ብለው ያሰቡትን ክብር ለየራሳቸው የቤተ መንግሥት ሥልጣን ቦታ እየመረጡ እያደላደሉ የመድቡ ጀመር፡፡EDA 96.3

  ከሁሉም የጴጥሮስ ሕይወትና ያጋጠሙ ነገሮች ትምህርት የሚሰጡ ነበሩ፡፡ በራስ እምነት መሞከር ውድቀትን ያመጣል፡፡ ሆን ተብሎ የሚደረግ የክፋት ሥራ ይቅርታ የለውም፡፡ ክርስቶስም ጴጥሮስን ከማድረግ አላገደውም ወይም አልከለከለውም፡፡ ነገር ግን ጴጥሮስን ከማድረግ አላገደውም ወይም አልከለከለውም፡፡ ነገር ግን ጴጥሮስ በባህሩ ላይ መሄድ ሲጀምር የውሃው ሞገድ በላዩ ላይ ሊፈስበት ሲል የየሱስ እጆች እንደደረሱለት ሁሉ ጥልቅ የክፋት ውሃ በነፍሱ ላይ ሊወጣበት ሲል የርሱ ፍቅር ደርሶ አዳነው፡፡ በተደጋጋሚ ለበርካታ ጊዜ ጴጥሮስ ከጥፋት አፋፍ ላይ እያደረሱት የጉራ ቃላቶችም ይበልጥ ወደ ገደል እያቃረቡት ነበር፡፡ በተደጋጋሚ ያስጠቀቀው ቢሆንም «ትክለኛለህ» ሉቃ 22-34 በደቀ መዛሙርቱ ፊት በስቃይ ላይ እያለ እንኳ ፍቅር የተሞላበት የእምነት ቃለ ተናገረ፡፡ «ጌታ ሆይ ከአንተ ጋር ወደእርስ ቤትና ወደሞትም ቢሆን እሄዳለሁ፡፡» ሉቃ 22-23 ያ ልብን ማንበብ የሚችለው ጌታ ደግሞ ለጴጥሮስ ይኸንን መልዕክት ሰጠው ያን ጊዜ ዝክተኛ ግምት ተሰጥቷቸው የነበረ ነገር ግን በዚያ ውድቅት ሌሊት የተስፋ ጨረር ፈነጠቁ፡፡ «ጌታም ስምኦን ስምኦን ሆይ እነሆ ሰይጣን እንደስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስላንተ አማለድሁ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ፡፡» ሉቃ 22፡31-32EDA 96.4

  በፍርድ ቤቱ አደራሽ ውስጥ እነኝህ የክህደት ቃላት ሲነገሩ የጴጥሮስ ፍቅርና ታማኝነት በዓለም መድህን የትካዜ የፍቅርና የሐዘን ዐይን አገላለጥ ሲነቃቃ ክርስቶስ ወደአለቀሰበትና የፀለየበት የአትክልት ስፍራ በዚያ የእሱ እንባ በፀፀት በጣር የደም ነጠብጣብ ባራሰው መሬት የሆነውን በትዝታ አስታወሰና ከዚያም የአዳኙ ቃል «እኔ ፀለይሁላችሁ በእምነት በተለወጣችሁ ጊዜ፡፡ ልባችሁ ብርታት ያገኝ ዘንድ» በማለት ያደረገው ፀሎት ታወሰው፡፡ ክርስቶስ የጴጥሮስን ኃጢአት አስቀድሞ አውቋል፡፡ ያን ከመፈፀም ግን አላገደውም፡፡EDA 97.1

  ክርስቶስ በጴጥሮስ ላይ ዐይኑን ሲያሳርፍ የነበረው አስተያየት በሀኔታ ፋንታ የሚያወግዝ ቢሆን ሆኖ ሀጢአቱን አስቀድሞ በመተንበይ በመናገር የተስፋ ቃሉን ሳይናገር ቢቀር ኖሮ ጴጥሮስን የከበበው ጨለማ ምን ያክል ይበልጥ ድቅድቅ በሆነ ነበር? የዚያች ክፉኛ የተገረፈች ነፍሱ ስቃይም ምን ያክል ድንገተኛ የቁጣ ፍርድ በሆነ ነበር፡፡ በዚያ የስቃይ እና ራሱን ከቡድን ጋር የሚያደረግበት ሰዓት ይሁዳ በተወረወረበት መንገድ ቁልቁል ከመውረድ የሚያግደው ምን ነገር ይኖር ነበር?EDA 97.2

  የእርሱን ተከታይ ደቀ መዝሙር ለመከራ ያልተወው ጌታ በከባድ ስቃይ ላይ እያለ ብቻውን አለተወውም፡፡ እሱ የማይወድቅ የማይለወጥ ፍቅር ነው፡፡EDA 98.1

  በክፋት ውስጥ ያሉ ሰብዓዊ ፍጡሮች እየተፈተኑ የሚሳሳቱ ሰዎችን ለፍቅር ወደማነጋገር ያዘነብላሉ፡፡ ልብን ማንበብ አይችሉም፡፡ ልብ ያለበትን ትግልና ስቃይም አያውቁም፡፡ ከፍቅር ተግሳጽ ቁስልን ከሚያድን፣ ተስፋን ከሚያናግረው ማስጠንቀቂያ ገና መማር አለባቸው፡፡EDA 98.2

  በፍርድ ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ከርሱ ጋር የቆየው ዮሐንስ አልነበረም፡፡ ከመስቀሉ ጐን የቆመው ካሥራ ሁለቱ ሁሉ ቀደም በአንደኝነት በመቃብር ቤት በር የተገኘው ጴጥሮስ እንጅ ዮሐንስ አልነበረም፡፡ ከእርገቱ በኋላ በክርስቶስ ስሙ የተወሳውም ‹ለደቀመዛሙርቱ ለጴጥሮስ ተናገራቸው፡፡› አለ መልአኩ «ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀመዛሙርቱ ለጴጥሮስም ወደገሊላ ይቀድማችኋል እደነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ፡፡» ማር 16፡7EDA 98.3

  ክርስቶስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር በባህር ዳርቻ ባደረገው የመጨረሻ ስብሰባ ላይ ጴጥሮስ «ትወደኛለህን?» በሚለው ሦስት ጊዜ ተደጋግሞ በተነሳው ጥያቄ ተፈተነ፡፡ ሥራው አስመረጠው፡፡ የጌታን መንጋ እንደመግብ ተደረገ፡፡ በኋላ በመጨረሻ ላይ በእርሱ የግል አመራር የሱስ እንደህ ተናገረው፡፡ «ተከተለኝ፡፡» ዮሐ 121፡17-22EDA 98.4

  አሁን እነኛ ቃላቶች ሊያደንቃቸው ይችላል፡፡ ክርስቶስ አንድ ሕፃን ልጅ በደቀመዛሙርቱ መካከል አስቀምጦ እንደእሱ እንዲሆኑ እየነገረው በሰጠው ትምህርት የተገሰፀውን አሁን ጴጥሮስ በተሻለ መንገድ ሳያስተውለው አይቀርም፡፡ የርሱን ደካማ ጐንና የክርስቶስን ኃይል ይበልጥ በተሟላ መልኩ እያወቀው በመጣ ቁጥር ለማመንና ለመታዘዝ ዝግጁ ሆነ፡፡EDA 99.1

  በሥራ ልምዱና መሰዋዕትነቱ መጨረሻ መዝጊያ ላይ ይህ ደቀ መዝሙር ባንድ ወቅት መስቀሉን በሚገባ ለይቶ ለማስተዋል ሳይዘጋጁ፤ ጌታን የካደ እንደሱ ዓይነት ሰው ጌታው በተሰቀለበት ሁኔታ መስቀል ላይ መሞት ለከሃዲ ሰው ትልቅ ክብር ነው ብሎ በማሰብ ብቻ ሕይወቱን ወደ ወንጌል ሠራ ማዘንበል አንደደስታ ቆጠረው፡፡EDA 99.2

  የጴጥሮስ ፍፁም መለወጥ የመለኮት ፍቅር ልዩ ተዓምር ነበር፡፡ የሊቀካህኑን መንገድ ለመከተል ለሚፈልጉ ሁሉም የሕይወት ትምህርት ነው፡፡EDA 99.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents