Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  የእምነት ትምህርት

  «እንስሶችን ጠይቅ ያስተምሩህማል የሰማይን ወፎች ጠይቅ ይነግሩህማል፡፡ … የባህርም አሶች ይነግሩሃል፡፡» «ወደ ገብረጉንዳን ሂድ መንገዷንም ተመልከት» «ወደሰማይ ወፎች ተመልከቱ» «ቁራዎችን ተመልከቱ» ኢዮ 12፡78 ምሳ 6፡6 ማቴ 6፡26 ሉቃ 12፡24EDA 128.1

  ስለእነኝህ የእግዚአብሔር ፍጥረቶች ለልጆቻችን መንገር ብቻ በቂ አይደለም፡፡ እንስሶቹ ራሳቸው የእሱ አስተማሪዎች መሆናቸው ነው፡፡ ትዕግሥት የተሞላበትን የኢንዱስትሪ ግንባታ ሥራ መሰናክልን ዘለቶ የመውጣት ትምህርት ለወደፊቱ የእግዚአብሔርን ፈቃድና ስጦታ ትምህርት የሚሰጡን ጉንዳኖች ናቸው፡፡ ወፎች ደግሞ ጣፋጭ የሆነውን የእምነት ትምህርት እንዲያስምሩ ነው፡፡ ምግብ የሚያቀርብላቸው የሰማዩ አባታችን ነው፡፡ ነገር ግን የግድ ምግቡን መሰብሰብ አለባቸው፡፡ ጐጆአቸውን መሥራትና ልጆቻቸውን ማሳደግ አለባቸው፡፡ በየጊዜው እነሱን ሊያጠፏቸው ለሚሹ ጠላቶቻቸው የተጋለጡ ናቸው፡፡ ነገር ግን ወደዕለት ሥራቸው ሲወጡ ደስተኞች ናቸው የዝማሬ ፉጨቶቻቸው ሁሉ በደስታ የተሞሉ ናቸው፡፡EDA 128.2

  በመዝሙረኛው ዳዊት ለእነዚህ የጫካ የእግዚአብሔር ፍጥረቶች የተሰጠው መግለጫ እንዴት ግሩም ነው፡፡ «ረጃጅም ተፈራሮች ለዋላዎች ድነጋዮችም ለእሽኮኮዎች መሸሻ ናቸው፡፡» መዝ 104፡18 ምንጮች የሰማይ ወፎች የሚኖሩበት «የሚዘምሩበት» ጫካ አካባቢ መካከል በየኮረብታው ሽንተረር ላይ እንዲወርዱ አደረገ፡፡ በደኑ ውስጥ ያሉ ፍጥረታት ሁሉ የእርሱ ትልቅ ቤተሰብ አንድ አካል ናቸው፡፡ «ሕያው ለሆኑ ነገሮች ሁሉ የሚሹትን ሁሉ» ያገኙ ዘንድ እጁን ይዘረጋላቸዋል፡፡ መዝ 145፡1EDA 128.3

  ተራራ ላይ ያለችው ንሥር አንዳንድ ጊዜ በጠላቷ ተመትታ ወደ ተራራው ስንጥቅ ውስጥ መግባት ይኖርባታል፡፡ የዳመና ማዕበል ያችን ግዙፍ የጫካ ወፍ ይዘጋባትና ጥቅጥቅ ጨለማዎች ይለያትና ይሸፍንባታል፡፡ ቤቷን ከሠራችበት ገደል ወጥታ ለማምለጥ የምታደርገው ሙከራ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡ አየሩን በጠነከሩ ክንፎቿ እየመታች ወደፊተና ወደኋላ ትሄዳለች፡፡ ጩኸቷም ከተራራው የገደል ማሚቶዎች ጋር ያስተጋባል፡፡ በመጨረሻም በድል አድራጊነት ወደላይ ከፍ ብላ በመውጣት ዳመሃዋችን ሰንጥቃ በማለፍ ትመጥቅና ግልጽ የፀሐይ ብርሃን የምታገኝበት ቦታ ላይ ትደርሳለች፡፡ ኃይለኛ ውሽንፍርና ድፍን ያለው የጨለማ ዝናብ ዘልቃ ወደታች በርቀት ቁልቁል የምተይበት ስፍራ ላይ ትደርሳለች፡፡ እኛም እንደዚሁ በብዙ ችግሮች ተስፋ በመቁረጥሃ በጨለማ ውስጥ ዙሪያውን የምንከበብበት ጊዜ ይኖራል፡፡ የሐሰት ሥራ ጭንቀት የሞላበትና ፍትህ በሌለበት ሁኔታ ዙሪያውን ዝቅ ሊሆንብን ይችላል፡፡ ልንገፍፈው ወይም ልንበትነው የማንችለው ዳመና ያጋጥመናል፡፡ ከሆኔታዎች ጋር በኃይል እንድታገላለን፡፡ ነገር ግን ልናመልጥ የምንችልበት አንድና አንድ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ጭጋጉና ጉሙ ከመሬት ጋር እንደተያያዙ ናቸው፡፡ ከዳመናው በላይ ግን የእግዚአብሔር ብርሃን ያበራል፡፡ በዕምነት ክንፎች እርሱ ወደ አለበት ብርሃን መነሳት አለብን፡፡EDA 129.1

  መማር ያለብን ትምህርቶች ብዙ ናቸው፡፡ በሜዳው ወይም በተራራው ላይ ብቻውን የቆመው ዛፍ ሥሮቹን ወደመሬት በጥልቀት በመስደድ መሬቱን በጥብቅ ጠፍንጐ በመያዝ ኃይለኛውን ነፋስ መቋቋም ይችላል፡፡ በልጅነት የሰበት ኃይል አንድ ቅርንጫፍ ተጠማዞ ቅርጹ እንደተበላሸና የጐበጠ ለጋ አትክልት በኋላ ቆይቶ ሊመልሰውና ሊያስተካክለው የሚችል ምድራዊ ኃይል የለም፡፡ የቅድስና ሕይወት ሚስጥር ከውሃ ላይ በበቀለች አበባ ይመስላል፡፡ ከትንሿ ኩሬ ዳርቻ በአረምና በቆሻሻ የተከበበች ሆና ሳለ ሥሯን ወደታች ዘርግታ ወደአሸዋማው አፈር በመዝለቅ ለሕይወቷ የሚሆን ውሃ እየሳበች ግሩም ሽታ ያላቸውን የአበባ ላቫዎቿን ነጥብ የምታክል ስህተት ወደሌለበት ፍፁማዊ ብርሃን ታቀናለች፡፡EDA 129.2

  ስለዚህ ልጆችና ወጣቶች ከመምህሮቻቸውና ከትምህርት መጽሐፎች የእውነትን እውቀት እያገኙ እያሉ ትምህርትን መቀበለና እውነቱን ለራሳቸው መለየትን ይማሩ፡፡ በአትክልት ቦታ ውስጥ እያሉ ለራሳቸው የግል አትክልት በሚያደርጉት እንክብካቤ ምን እንደተረዱ ጠይቋቸው፡፡ የመሬቱን ቆንጆ አቀማመጥ ሲመለቱ እግዚአብሔር ሜዳውን እንደዚያ በሚያስደስትና ውብ በሆኑ የተለዩ ዕጽዋት ለምን እንዳለበሰው ጠይቋቸው ለምንድን ነው ሁሉም ደማቅ ቡኒ ያልሆነው? አበባዎችን ሲሰበስቡ ይኸን የመሰሉ ድንቅ ነገሮችን ከኤደን ገነት ላይ ለምን እንዳስተረፈልን እንዲያስቡ አድርጓቸው፡፡ በየቦታው በተፈጥሮ ነገሮች ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ለእኛ በማሰብ ላዘጋጀልን ለፍላጐታችንና ለደስታችን የሚሆኑትን ነገሮች ሁሉ በአስገራሚ ሁኔታ ለእኛ ስለማሳደጉ ማስረጃ እንዲሰበስቡ አስተምሯቸው፡፡EDA 130.1

  በተፈጥሮ ውስጥ ያለውን የአብን የእጅ ሥራ የሚያውቀው በመሬት ሐብትና ውበት በኩል የእሱን የእጅ ጽሁፍ የሚያነበው ከተፈጥሮ ጥልቅ ትምህርቶች መማር የሚችለውና የማሰጡትን ከፍተኛውን ግልጋሎት መቀበል የሚችለው እርሱ ብቻ ነው፡፡ የኮረብታዎችን የወንዝና የሀይቅን ከፍተኛ ጠቀሜታ አውቆ በአድናቆት በክብርና በምስጋና የሚቀበል የእግዚአብሔርን ሐሳብ መግለጫዎች እንደሆኑ አድርጐ የሚያይ የፈጣሪ መግለጫዎች እንደሆኑ የሚመለከት እርሱ ብቻ ነው፡፡EDA 130.2

  ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ፀሐፊዎች ከተፈጥሮ ብዙ መግለጫዎችን በመውሰድ ተጠቅመዋል፡፡ እኛም በዓለም ላይ የተፈጥሮ ነገሮችን በመመርመር ስንከታተል በመንፈስ ቅዱስ አመራር የእግዚአብሔርን ቃል ትምህርቶች ሙሉ በሙሉ ለማስተዋል ብቃት እናገኛለን፡፡ ስለዚህም ተፈጥሮ የቃሉ የግምጃ ቤት ቁለፍ ይሆንልናል፡፡EDA 131.1

  ልጆች የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርቶች የሚገልፁ በተፈጥሮ ውስጥ ያሉ ተጨባጭ ነገሮችን እንዲፈልጉና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተፈጥሮ የተወሰዱ ተመሳሳይ ቁምነገሮችን ተከታትለው እንዲመራመሩ መበረታታት አለባቸው፡፡ ክርስቶስን የሚወክሉ ማናቸውንም ነገሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከተፈጥሮ ውስጥ ፈልገው እንዲያገኙና እርሱ እውነትን ለመግለጽ የተጠቀመባቸውን ነገሮች መርምረው ማግኘት አለባቸው፡፡ በዚህም መንገድ በዛፉ በወይኑ በአበባው እና በየጽጌረዳው በፀሐይና በከዋክብትም እርሱን ማየትን መማር አለባቸው፡፡ በወፎች ዝማሬ፣ በዛፎች ውዝዋዜ፣ በሚጮኸው መብረቅ፣ በባህሩ ሙዚቃ አማካይነት የርሱን ድምጽ መስማት ይማሩ ዘንድ እናም እያንዳንዱ ተጨባጭ የተፈጥሮ አካል የርሱን ግሩም ድንቅ ትምህርት ይደግምላቸዋል፡፡EDA 131.2

  በመሆኑም ራሳቸውን በዚህ ዓይነት ከክርስቶስ ጋር ለሚያስተዋውቁ ሰዎች ምድር ብቸኛ የግዞትና የተገለለ ሥፍራ አይሆንባቸውም፡፡ በአንድ ወቅት ከሰዎች ጋር የነበረው እርሱ በመካከላቸው በመገኘቱ የተሞላች የአባታቸው ቤት ትሆንላቸዋለች እንጂ፡፡EDA 131.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents