ኤልሳዕ በትንንሽ ነገሮች ሁሉ ታማኝ የነበረው ሰው
ነብዩ ኤልሳዕ በዚያ ፀጥ ባለና በተረጋጋ ያገር ቤት ኑሮው የመጀመሪያ አመታቱን ያሳለፈው ከእግዚአብሐርና ከተፈጥሮ በሚያገኘው ትምህርት ሥር እና ጠቃሚ በሆነ ሥራ ላይ ነበር፡፡ ሀገሬው በመሉ እግዚአብሔርን ትቶ ሃይማኖቱን በለወጠበት ጊዜ የአባቱ ቤተሰቦች በጉልበታቸው ተንበርክከው ለባአል ካልሰገዱት ሰዎች ውስጥ ጥቀቶቹ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር የሚከበርበትና በየቀኑ የተግባር እምነት ሕግ የሆበት አንድ ቤተሰብ ነበር፡፡EDA 61.3
የአንድ ሀብታም ገበሬ ልጅ የነበረው ኤልሳዕ በቅርበ ያገኘውን ይህን ሥራ ያዘ፡፡ በሰዎች መካከል መሪ የመሆን ችሎታ ያለው ሲሆን በሕይወት በተለመዱት ተግባሮች አማካኝነት ሥልጠናውን አግኘቷል፡፡ በጥበብ ለመምራት ይችል ዘንድ መጀመሪያ መታዘዝን መማር ነበረበት፡፡ በትንንሽ ነገሮች ታማኝ በመሆን ክብደት ያላቸውን እምነቶች ለመሸከም ተዘጋጀ፡፡EDA 61.4
የዋህና ደግ በሆነ መንፈስ ውስጥ ኤልሳዕ ኃይልና ጽናት ያለውመ ሰው ነበረ፡፡ እግዚአብሔርን ማፍቀርና መፍራትን እጅግ ይወድ ነበር፡፡ በየቁኑ ትህትና በተሞላው ተግባሩ ሁሉ የዓላማ ብርታትን ፣ በባህሪ ጌታ መሆንን፤ በመለኮት ፀጋና እውቀት ማደግን የተለያዩ ልማዶቹ አድርጐ ነበር፡፡ በቤት ውስጥ ሥራዎች አባቱን ይረዳ የነበረ ሲሆን በዚህም ከእግዚአብሔር ጋር መተባበርን ይማር ነበር፡፡EDA 62.1
የነብይነት ጥሪው ከአባቱ ሠራተኞች ጋር በአባቱ ማሳ እያረሰ በነበረበት ሰዓት መጣለት፡፡ ኤልያስ በመለኮት መመሪያ የሚተካው ሰው እንዲፈልግ በታዘዘ ጊዜ በርኖሱን በወጣቱ ትካሻ ላይ ጣለ፡፡ ኤልሳዕም ጥሪውን ተገነዘበና ታዘዘ፡፡ ‹ተነስቶ ኤሊያስን ተከትሎ ሄደ፡፡› 1ኛ ነገ 19፡21 መጀመሪያ ከኤልሳዕ ይፈለግ የነበረው ታላቅ ሥራ አልነበረም፡፡ ሥነ-ምግባሩን የሚገሩለት የተለመዱት የሥራ ቦታዎች ነበሩ፡፡ ለአለቃው ለኤልያስ እጅ እንዲያስታጥብ ነበር የታዘዘው፡ የነብዩ የግል አገልጋይ እንደመሆኑ በትንንሽ ነገሮች ታማኝ መሆንን ቀጠለበት፡፡ አስመሰከረም፡፡ በየቀኑ ብርታት ለማሰጠው ዓላማው ከሚያከናውነው ተግባር ጋር እግዚአብሔር ለመረጠው ተልዕኮውም ከልቡ በተመስጦ ይዘጋጅ ነበር፡፡EDA 62.2
መጀመሪያ በተጠራ ጊዜ ቁርጠኛነቱ በቅድሚያ ተፈትኖ ነበር፡፡ ኤልያስን ለመከተል ሲነሳ ነቢዩ ተው ወደቤትህ ተመለስ ብሎት ነበር፡፡ ያን ጊዜ ወደፊት ሊገጥመው የሚችለውን ፈተናና የሚጠይቀውን መስዋዕትነት በማገናዘብ ጥሪውን እምቢ ማለት ወይም መቀበል ነበረበት፡፡ ኤልሳዕ ግነ ያጋጠመውን እድል ጠቃጢነት አገንዝቦ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ መሆንን ወይም ከእርሱ አገልጋይ ጋር መሥራትን ለሌላ ዓለማዊ ጥቅሞች አሳልፎ የሚለውጥ አልሆነም፡፡EDA 62.3
ጊዜ እያለፈ በሄደ መጠን ኤልሳዕ ተርጓሚ ለመሆን ተዘጋጀ፡፡ ተከታይና ተተኪ ለመሆን ተሰናዳ፡፡ አሁንም እምነቱና ቁርጠኝነቱ በድጋሚ ተፈተነ፡፡ ኤልያስ እየዞረ አገልግሎት በሚሰጥበት ቦታ ሁሉ አብሮ ሲሄድ በቅርቡ አንድ ለውጥ እንደሚከተል በማወቅ አሁንም ወደቤቱ እንዲመለስ በነቢዩ ይጠየቅ ነበር፡፡‹ኤልያስም ኤልሳዕን እግዚአብሔር ወደቤቴል ልኮኛልና አነተ በዚህ ቆይ አለው፡፡ ኤልሳዕም ሕያው እግዚአብሔርን በሕያው ነፍስህም አመናለሁ አልለይህም፡፡ አለ› ድሮ በእርሻ ሥራ ላይ መሪ የነበረው ኤልሳዕ ተስፋ መቁረጥና መውደቅ እንደሌለበት ተምሮ ስለነበር አሁን እጅን ወደሌላ የሥራ መስክ አዙሮ ሲሠራ ከዓላማው ዝንፍ የሚል አልነበረም፡፡ ሁልጊዜ ወደቤቱ እንዲመለስ በተጠየቀ ቁጥር የሚሰጠው መልስ «ሕያው እግዚአብሔርን በሕያው ነፍስህ አምናለሁ፡፡ አልለይህም፡፡» የሚል ነበር፡፡ 2ኛ ነገ 2፡2EDA 63.1
«እግዚአብሔር ወደ ዮርደኖስ ልኮኛልና አንተ አዚህ ቆይ አለው፡፡ እርሱም ሕያው እግዚአብሔርን ሕያው ነፍስህንም አምናለሁ አልለይህም አለ፡፡ ሁለቱም ሄዱ፡፡ ከብያትም ልጆች ሃምሳ ሰዎች ሄዱ፡፡ በፊታቸውም ርቀው ቆሙ እነዚህ ሁለቱ በዮርዳኖስ ዳር ቆመው ነበር፡፡ ኤልያስም መጐናፀፊያውን ወስዶ ጠቀለለው ውኃውንም መታ ወዲህና ወዲያም ተከፈለ፡፡ ሁለቱም በደረቅ ተሻገሩ፡፡ ከተሻገሩም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን ካንተ ሳልወሰድ የመትሻውን ለምን አለው፡፡ ኤልሳዕም መንፈስህ በኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ አለ፡፡ እርሱም አስቸጋሪ ነገር ለምነሃል ነገር ግን አይሆንልህም አለ፡፡ ሲሄዱም እያዘገሙ ሲጫወቱ እነሆ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሏቸው ኤልያስም በአውሎ ነፋስ ወደሰማይ ወጣ፡፡ ኤልሳዕም አይቶ አባቴ አባቴ ሆይ የእስራኤል ሠረገላና ፈረሶች ብሎ ጮኸ፡፡ ከዚያም ወዲያ አላየውም፡፡ ልብሱንም ይዞ ከሁለት ተረተረው፡፡ ከኤልያስም የወደቀውን መጐናፀፊያ አነሳ፡፡ ተመልሶም በዮርዳኖስ ዳር ቆመ ከኤልያስም የወደቀውን መጐናፀፊያ ወስዶ ውኃ ውስጥ መታና የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት? አለ፡፡ ውኃውንም በመታ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተከፈለ፡፡ ኤልሳዕም ተሻገረ፡፡ ከኢያሪኮም መጥተው በአንፃሩ የነበሩት የነቢያት ልጆች ባዩት ጊዜ የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ አርፏል አሉ፡፡» 2ኛ ነገሥ 2፡6-15EDA 63.2
ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ኤልሳዕ በኤልያስ እግር ተተካ፡፡ እጅግ ትንሽ በነበረው ነገር ታማኝ የሆነው ሰው ትልቅ በሆነውም ነገር ላይ ብቁና እምነት ያለው መሆኑን አስመሰከረ፡፡EDA 64.1
ኤልያስ በኃይል የተሞላው የእግዚአብሔር መሳሪያ በመሆን እጅግ ግዙፍ የነበሩ በአሃብና በአረመኔዋ ኢዛቤል እየተረዱ ሕዝብን ያሳሳቱ ሰይጣናዊያን ጣኦቶችን ገለባብጦ ወዲያ ለመጣል በቅቷል፡፡ የባአል ነቢያት ወዲያ እንዲቆዩ ተደረገ፡፡ የእስራኤል ሕዝብም በሙሉ ወደ እግዚአብሔር አምልኮ ተመለሱ፡፡EDA 64.2
የኤልያስ ተተኪ አንደመሆኑ እስሪኤልን በሰላም መንገድ ለመምራት በጥንቃቄና በትዕግሥት እንዲሠራ ተምሯል፡፡EDA 64.3
ትምህርቱ ለሁሉም ነው፡፡ እግዚአብሔር በሚሰጠው ትምህርት ውስጥ ያለውን ዓላማ ማንም ሊያውቅ አይችልም፡፡ ነገር ግን በትንንሽ ነገሮች ታማኝ መሆን ትልልቅ ነገሮች መሸከም ለመቻላችን ማስረጃ መሆናቸውን ሁሉም ያውቃል፡፡ በሕይወት ውስጥ የምትደረግ እያንዳንዷ እንቅስቃሴ የባህሪይ መግለጫ ናት፡፡ እናም በትንሽ ሥራ «የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍር ሠራተኛ፡፡» 2ኛ ጢሞ 2፡15 መሆኑን ያረጋገጠና ያስመሠከረ ሰው ከበድ ያሉ እምነቶች የሚጣሉበት፤ በእግዚአብሔር ዘንድም የተከበረ ይሆናል፡፡EDA 64.4