የከዋክብት መልዕክት፡፡
ከዋክብትም ለእያንዳንዱ ሰው መልካም የደስታ መልዕክት አላቸው በተለይም ማንኛውም ሰው የሚያጋጥመው ልብ የሚደክምበት ፈተናም መራር የሚሆንበት ሰዓት መሰናክሉን ማለፍ ወይም ልንወጣው የማንችል በሚመስልበት ሰዓት የሕይወት ግቦች ፈጽሞ ሊደረስባቸው የማይቻል በሚመስሉበት ሰዓት ለሕይወት የተገባው የተስፋ ቃልም የሰዶም ፍሬ በሚመስልበት ጊዜ ድፍረትና ጽናት ታዲያ ከወዴት ይገኛል? እግዚአብሔር ከከዋክብትና ከማይታወከው መንገዳቸው እንማር ዘንድ ከሰጠን ትምህርት በስተቀር፡፡EDA 125.4
«ዐይናችሁን ወደላይ አንስታችሁ ተመልከቱ እነዚህን የፈጠረ ማነው? ሠራዊታቸውን በቁጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፡፡ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፡፡ በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም፡፡ ያዕቆብ ሆይ እስራኤልም ሆይ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? አላወቅህንም? አልሰማህንም? እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፡፡ አይደክምም፡፡ አይታክትምም፡፡ ማስተዋሉም አይመረመርም ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፡፡ ጉልበት ለሌለው ብርታትን ይጨምራል፡፡» «እኔ ካንተ ጋር ነኝና አትፍራ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ አበረታሃለሁ እረዳህማለሁ በጽድቄ ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ» «እኔ አምላክህ እግዚአብሔር አትፍራ እረዳሃለሁ ብየ ቀኝህን እይዝሃለሁ፡፡» ኢሳ 40፡26-29 ምዕ 41፡10‚13EDA 126.1
የዘምባባ ዛፍ ኃይለኛ ፀሐይ አየወረደበት አቧራማ ሞቃት ነፋስ እየመታው አረንጓዴ እንደለመለመ በምድረበዳ ውስጥ ሙሉ ፍሬ ይሰጣል፡፡ ሥሮቹ ከማይደርቁ ምንጮች ይመገባሉ የእናቱን የቅጠሉ ልምላሜ በደረቁ በርሃ ቦና ባጠቃው ሜዳ ውስጥ ገና ከሩቁ ይታያል፡፡ በዚህ የሚጓዝ ሊሞት የደረሰ መንገደኛ የዛለ እርምጃውን በዚየ ጥላ ለማሳረፍና ሕይወት የሚሰጠውን ውሃ ለማግኘት ይጣደፋል፡፡EDA 126.2
የበረሃው ዛፍ እግዚአብሔር የልጆቹ ሕይወት በዚህ ዓለም ውስጥ ሲኖሩ ምን እንደሚመስል እንደሚፈልግ የሚያመለክት ነው፡፡ የጭንቀት ኑሮ መምራት አለባቸው፡፡ ረፍት የሌለበት በኃጢአት ምድረበዳ ውስጥ በሕይወት ውሃ ለማረፍ መዘጋጀት አለባቸው፡፡ ወገኖቻቸውንም ወደእሱ ወደሚጋብዘው «የሱስም ቆሞ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣ ይጠጣም፡፡» (ዮሐ 7፡37) ወደሚለው ማመልከት አለባቸው፡፡EDA 126.3
ስፋትና ጥልቀት ያለው ትልቅ ወንዝ እንደ አውራጐዳና ሀገሮችን አቋርጦ የሚጓዘው ውሃ እንደ ዓለም አቀፍ ጥቅም የሚታይ ሲሆን ይኸንን በእርጋታ የሚጓዝ ትልቅ ወንዝ የሚመግቡት ትንንሽ ጅረቶችና ማህናዎችስ? እነሱ ባይኖሩ ኖሮ ወንዙም ባልኖረም ነበር፡፡ የወንዙ ሕልውና በእነሱ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ለታላቅ ሥራ የተጠሩ ሰዎች የሚያገኙት ውጤት የእነሱ የግል ጥረት ብቻ ያስገኘው ይመስል ይከበሩበታል፡፡ ነገር ግን ያ ስኬት ቁጥር ሥፍር የሌላቸው የትሁት ሠራተኞችን ዓለም ጭራሽ ስለመኖራቸው የማታውቃቸው ሠራተኞችን ታማኝነት የተሞላበት ትብብር ጠይቋል፡፡ ያልታወቀላቸው ግዳጅ ለፋትና ከባድ ሥራ የአብዛኛዎቹ በዓለም ላይ ያሉ ሠራተኞች እጣ ነው፡፡ በዚህም እድላቸው ብዙዎች ደስተኛ አይሆኑም፡፡ ሕይወታቸው ብኩን እንደሆነ ይሰማቸዋል፡፡ ነገር ግን ትንሿ ምንጭ ድምጿን ሳታሰማ በቁጥቋጦው በጢሻውና በሜዳው ስትጓዝ ለተክሎች ጤናን በመስጠት መሬቱን የማልማትና ውበትን በማላበስ የምትሰጠው ጥቅም ከሰፊው ወንዝ ያላነሰ ነው፡፡ ለወንዙ ሕይወት በሚኖራት አስተዋጽኦ ወንዙ ብቻውን ሊፈጽመው የማይችል የነበረውን እንዲያከናውን ትረዳዋለች፡፡EDA 127.1
ትምህርቱ በብዙዎች ዘንድ የሚፈልግ ነው፡፡ ክህሎት ሁሉ እንደጣኦት ተመልኳል፡፡ ሥልጣንም ብዙዋች የሚቋምጡለት ነገር ሆኗል፡፡ እንደ መሪ ካለታዩ በስተቀር ምንም ነገር መሥራተ የማይፈልጉ ብዙ ናቸው፡፡ መመስገን የሚፈልጉ ያንን ካላገኙ ደግሞ ምንም ዓይነት የመሥራት ፍላጐት የሌላቸው እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ መማር የሚያስፈልገን ያሉንን ኃይሎችና ጥሩ አጋጣሚ እድሎች ከፍተኛ ጠቀሜታ ላይ ለማዋል እንደእጣ ፈንታ አምላክ በሰጠን መስመር በመርካት ታማኝ መሆን ብቻ ነው፡፡EDA 127.2