Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 30—እምነትና ፀሎት

    «እምነት ተስፋ ለተደረገበት ነገር ማረጋገጫ ነው»
    «እንደምታገኙ እመኑ ይሰጣችኋል፡፡»
    EDA 284.1

    እምነት ማለት በእግዚአብሔር ላይ በእርግጠኝነት መተማመን ማለት ነው፡፡ እንደሚያቅረንና ለእኛ ከሚበጁን ነገሮች ውስጥ እጅግ የተሻለውን እንደሚያውቅልን ማመን ነው፡፡ ስለሆነም ከራሳችን ይልቅ የርሱን መንገድ እንድንመርጥ ይመራናል፡፡ በድንቁርናችን ምትክ የርሱን ጥበብ በድክመቶቻችን ፋንታ የእርሱን ድንቅ ሐሳብ እንቀበላለን፡፡ ሕይወታችን እና እኛነታችን ራስ የእርሱ ነው፡፡ እምነት የርሱን ባለቤትነት ትቀበላለች ታመሰግናለች እናም በረከት ታገኛለች፡፡ እውነት ትክክለኛነት፤ ንጽህና፤ የሕይወት ስኬታማነት ምስጢር መሆናቸው ተመልክቷል፡፡ የእነዚህ መሠረተ ሃሳቦች ባለቤት የምታደርገን እምነት ነች፡፡EDA 284.2

    እያንዳንዱ የልብ አመታትና መንፈሳዊ ፍላጐት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ እምነት እውነተኛ ዕድገትና ብቃትን ብቻ የምታፈራ ሕይወትን ከእግዚአብሔር ትቀበላለችEDA 284.3

    እምነት እንዴት የተለመደ ተግባር ማድረግ እንደሚቻል ግልጽ ሊደረግ ይገባዋል፡፡ ለእያንዳንዷ እግዚአብሐር ለገባልን ቃል አንዳንድ ሁኔታዎች አሉ፡፡ የርሱን ፈቃድ ለመፈፀም ፈቃደኞች ከሆንን የርሱን ኃይል ሁሉ እናገኛለን፡፡ ምንም ዓይነት ነገር ለመስጠት ቃል ቡገባ በራሱ በተስፋው ውስጥ «ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡» ሉቃ 8፡11፡፡ የዋርካው ፍሬ ያለጥርጥር በዋርከው ዛፍ ውስጥ እንዳለ ሁሉ የእግዚአብሔር ስጦታም እርሱ በሰጠው ተስፋ ውስጥ በእርግጥ አለ፡፡ የተስፋውን ቃል ከተቀበልን ስጦተውን ወዲያውኑ እናገኛለን፡፡EDA 284.4

    የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድንቀበል የሚያስችለን ሃይማኖት ራሱ ለሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ የተወሰነ ተከፍሎ የሚታደለው ስጦታ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል በማደላደል ሥራ ላይ በዋለ መጠን ያድጋል፡፡ ሃይማኖትን ለማጠናከር ሲፈለግ አውትሮ ከርሱ ቃል ጋር ማገናኘት ነው፡፡EDA 285.1

    በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ውስጥ ተማሪው የእግዚአብሔርን ኃይል በቃሉ ውስጥ እንዲያይ ተደርጐ መማር አለበት፡፡ በፍጥረት ጊዜ «እርሱ ተናግሯልና፣ ሆነም፤ እርሱ አዘዘ ፀኑም» «የሌለውን እንዳለ አድርጐ በሚጠራ» በጠራቸው ጊዜ ሆነው ይገኛሉና፡፡ መዝ 33፡9 ሮማ 4፡17EDA 285.2

    የእግዚአብሔርን ቃል ያመነ ሁሉ፤ ምንም እንኳን በራሳቸው ፈጽሞ ረዳት የሌላቸው የነበሩ ዘወትር የመላውን ዓለም ኃይል እንዴት መቋቋም እንደቻሉ ሄኖክ ልቡ ንፁህ ሕይወቱም የተቀደሰ ሰው የነበረ፤ በስስት እያጋበሰ በመብላትና በመጠጣት ፈንጠዝያና ፌዝ በተበከለ ትውልድ ፊት በጽድቅ አሸናፊነት እምነቱን በጽናት የያዘ፤ ኖህና ቤተሰቦቹ በርሱ ዘመን የነበሩ ሰዎችን በመቋቋም እነኛን በአካላቸውና በአእምሮአቸው እጅግ ብርቱ የነበሩ ሰዎች ነገር ግን በምግባራቸው እጅግ ብልሹ የነበሩትን የተቋቋመ የእስራኤል ልጆች የተጨነቀ ባሪያ ሕዝብ በቀይ ባሕር ዳርቻ ያለምንም ረዳት በዚያ ዘመን እጅግ ኃይለኛ በነበረው መንግሥት ሠራዊት ፊት በፍርሃት ተውጠው በነበረ ሰዓት ዳዊት አድ ወጣት በግ እረኛ እግዚአብሔር ለዙፋኑ ቃል ገብቶለት ሳለ ሳውልም ያለ ኃይሉን በሙሉ ሥልጣን ለመያዝ ሙጭጭ ብሎ ዳዊትን አስጨነቀው ሲደራቅና ጓደኞቹ በእቶን እሳት ውስጥ ሆነው ንጉሥ ናቡከደነጾር ደግሞ በዙፋኑ ላይ ሆኖ ዳንኤል በአናብስት ተከብቦ ሳለ የርሱ ጠላቶች ደግሞ በመንግሥት ከፍተኛ ቦታ ላይ ሆነው የሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ የአይሁድ ቄሳውስትና ገዢዎች ሮማዊው ገዥ እንደ ፈቃዳቸው ያደርግላቸው ዘንድ እየገፋፋ የስገድዱት በነበረ ጊዜ ጳውሎስ በሰንሰለት ታስሮ ወደ ወንጀለኞች የሞት ስፍራ ሲወስዱት፤ አምባ ገነኑ ኔሮ በመላው ዓለም ላይ የንጉሠ ነገሥት ግዛት ነበረው፡፡EDA 285.3

    እንዲህ ዓይነት ምሳሌዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ የሚገኙ አይደለም፡፡ በእያንዳንዱ የሰው ልጅ እድገት ውስጥ ሁሉ ይኖራሉ፡፡ ቫውደዋዊያንና ሀጐኖትስ፤ ዋይድፊና ሁስ ጀሮምና ሉተር፤ ታይድልና ኖክስ፤ ዚንዜንዶርፍና ዌስሌይና ሌሎችም ብዙዎች ከሰብዓዊ ኃያላንና የክፋት ሕጐች ፊት ተጋፍጠው የእግዚአብሐርን የቃሉን ኃይል መስክረዋል፡፡ የዚች ዓለም እውነተኛ ክቡራን እነዚህ ናቸው፡፡ ንጉሣዊ መስመሩም ይኸም ነው፡፡ የዛሬዎቹ ወጣቶች ቦታቸውን ሄደው መውሰድ ያለባቸው በዚሁ መስመር ነው፡፡EDA 286.1

    እምነት በትልልቆቹ የሕይወት ጉዳዮች ውስጥም እንደዚያው ያስፈልጋል፡፡ በየቁኑ ፍላጐቶቻችንና ተግባሮቻችን ውስጥ ሁሉ በእምነት በምንገዛበት ጊዜ አበረታች የሆነው የእግዚአብሔር ኃይል እውን ይሆንልናል፡፡EDA 286.2

    ከሰው ልጅ አመለካከት አንፃር ሲታይ ሕይወት የማያክም መንገድ ነው፡፡ ከጠለቀ ተሳትፎ ሕይወታችን አንፃር እኛ ሁላችንም በየግላችን የምንጓዝበት መንገድ ነው፡፡ ወደውስጣዊ ሕይወታችን ማንም ሰው ሙሉ በሙሉ ጠይቆ ሊገባ አይችልም፡፡ አንድ ሕፃን ልጅ በዚያ ጉዞ ላይ መንገድ ሲጀምር ወዲያውኑም ሆነ ዘግይቶ የራሱን መንገድ መምረጥ ይኖርበታል፡፡ ለዘለዓለም የሚሆኑ የሕይወትን ጉዳዮች ራሱ እየወሰነ እምነቱን ወደ እውነተኛው መሪና ረዳት ለመምራት ጥረቱ ታዲያ ምን ያክል ልባዊ መሆን አለበት፡፡EDA 287.1

    ከፈተና ሁሉ እንደ አንድ መከላከያ ጋሻ የሚሆንና ለንጽህና፤ ለእውነት የሚኖር ፍላጐት ሁሉ እግዚአብሔር በመካከለችን ሲኖር የሚሰማንን ስሜት ሌላ ምንም ዓይነት ስበት ሊስተካከለው አይችልም፡፡ «በርሱ ዓይኖች ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው፡፡» እርሱ «ዐይኖቹ ክፉን እንዳያዩ ንፁህ ናቸው፡፡ ጠማማነትን ይመለከት ዘንድ አይችልም፡፡» እብራ 4፡13 እንባ 1፡13 ይህ ሐሳብ በምልጃና በብዙ ቅሌት በተበከለች ግብጽ ውስጥ የዮሴፍ ጋሻ ነበረ፡ በፈተና ውስጥ ለቀረበለት የሚማረክ ሐሳብ በጽናት መልስ ሰጠ፡፡ «እንዴት ይኸን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ? አላት፡፡» ዘፍ 39፡9 እንዲህ ዓይነት ጋሻ እምነት ለሚያፈቅረው ነፍስ ሁሉ ይሰጣል፡፡EDA 287.2

    ሕይወትን ለአንድ የሚፈራ ሕፃን እንደ ሸክም የሚያከብድበት ፍርሃት ሊወገድ የሚችለው እግዚአብሔር በመካከላችን መኖሩን የሚገልጽ ስሜት ብቻ ነው፡፡ «የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ይድናቸውማል፡፡» መዝ 34፡7 የሚለውን የተስፋ ቃል በመታሰቢያነት በአዕምሮው ውስጥ ይቅረጽ ያንን አስገራሚ የኤልሳዕን ታሪክ ያንብብ፤ በዚያ ታላቅ ከተማ በርሱና በጠላቶቹ ሠራዊት መካከል እጅግ ብዙ የሰማይ ሠራዊት የከበበበው ዕለት የነበረውን ታሪክ ያንብብ፡፡ ጴጥሮስ በእርስ ቤት ውስጥ ሞት ተፈርዶበት በነበረ ጊዜ የእግዚአብሔር መለአክ እንዴት ተገለጠለትና የታጠቁትን ጠባቂ ወታደሮች አልፎ ግዙፍ የብረት አጥር መዝጊያ በሮች ተሸካሚ ጉበኞችና አግዳሚ ብረቶች ሁሉ መልአኩ አልፎ የእግዚአብሔርን አገልጋይ በደህና እንዴት መርቶ እንዳወጣው ያንብብ፡፡ በባሕር ላይ ስለታየው ትዕይንት ወታደሮችና የባሕር ሰዎች ደክሞአቸውና ታክተው ለረዥም ጊዜ በመጾም የባሕሩን ሞገድ ብዙ ሲተገሉ ፈጽሞ አድክሞአቸው በነበረ ጊዜ እስረኛው ጳውሎስ ወደፍርድና ሞት እየሄደ እያለ እነኛን የድፍረትና የተስፋ ክቡር ታላላቅ ቃላት ተናገረ፡፡ «አይዟችሁ ብየ እመከራችኋለሁ፡፡ ይህ መርከብ እንጅ ከእናንተ አንድ ነፍስ እንኳ አይጠፋምና፡፡ የርሱም የምሆንና ደግሞም የማመልከት የእግዚአብሔር መልአክ በዚች ሌሊት አጠገቤ ቆሞ ነበረና እርሱም ጳውሎስ ሆይ፣ አትፍራ በቄሳር ፊት ልትቆም ይገባሃል እነሆም እግዚአብሔር ካንተ ጋር የሚሄዱትን ሁሉ ሰጥቶሃል አለኝ» አለ፡፡ በዚህ የተስፋ ቃል በማመንም ጳውሎስ ለጓደኞቹ አረጋገጠላቸው፡፡ «ከእናንተ ከአንድ የራስ ጠጉር እንኳ አትጠፋምና፡፡» እንዳለውም ሆነ፡፡ ምክንያቱም በዚያ መርከብ ውስጥ እግዚአብሔር ሥራውን ሊያካሂድበት የሚችል አንድ ሰው ነበረ፡፡ በመርከቡ ሙሉ የነበሩ አረማዊያን ወታደሮችና መርከበኞች ሁሉ ዳኑ » ሁሉም በደህና ወደምድር ደረሱ፡፡» የሐዋ. ሥራ27፡22-24፣ 34፣44EDA 287.3

    እነዚህ ነገሮች የተፃፉት እኛ አንብበን እንድንገረም ብቻ አይደለም፡፡ በጥንተዊያን የእግዚአብሔር አገልጋዮች ውስጥ የነበረው የእና እምነት በእኛ ውስጥም ይሠራ ዘንድ ነው እንጂ፡፡ የእርሱ ኃይል አስተላለፊ መስመሮች መሆን የሚችሉ ልቦች በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ ያን ጊዜ ሠርቶ ከቀረፀበት ሁኔታ ባለነሰ መልኩ አሁንም ይሠራል፡፡EDA 288.1

    በራሳቸው መተማመን የጐደላቸው ጥንቃቄ መውሰድንና ኃላፊነትን ከመሸከም የተሸማቀቁ ተጠራጣሪዎች በእግዚአብሔር ላይ መተማመንን ይማሩ፡፡ ስለዚህም ብዙ በዓለም ላይ የማይረቡ ሆነው ሊቀሩ ይችሉ የነበሩ ሰዎች ምናልባትም ያለምንም ረዳት ሸክም የበዛባቸው የሐዋሪያው ጳውሎስ ጋር እንዲህ ማለት ይችሉ ይሆናል፡ «ኃይልን የሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ፡፡» ፊሊጱ 4፡13EDA 289.1

    አንድ ገገር ሲያጋጥመው ቶሎ ለሚከፋ ልጅ እምነት ክቡር ድንቅ ትምህርቶች አሏት፡፡ ክፉን ለመቋቋም ወይም የስህተት አድራጐትን ለማስወገድ ዘወትር ፈጣንና ንቁ በሆነ የብርታት መንፈስ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ልጅ እግዚአብሔር ወደቀና መንገድ የሚመራ ዘለዓለማዊ ኃይል መሆኑን ይማር፡፡ እጅግ በጣም የሚያፈቅረው ውድ ልጁን እስከሚሰጥ ድረስ ፍጡራንን ለማዳን በገርነት ወዷቸዋልና እያንዳንዱን ስህተት የሚፈጽም ሰው «የሚነካችሁ የዐይኑን ብሌን ይነካል፡፡» ይላል ዘካ 2፡8 «መንገድህን ለእግዚአብሐር አደራ ስጥ በርሱ ታመን እርሱም ያደርግሃል ጽድቅህን እንደብርሃን ፍርድህም እንደቀትር ይመጣል፡፡» 37፡5፡6EDA 289.2

    «እግዚአብሔርም ለድሆች መጠጊያ ሆናቸው እርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው፡፡ ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፡፡ አቤቱ የሚሹህን አትተዋቸውምና፡፡» መዝ 9፡9፡10EDA 289.3

    እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ርህራሄና ሐዘኔታ እኛም ለሌሎች እንድገለጽ ያዝዘናል፡፡ ጥለኞች ለራሳችን በቃን ባዮች በቀልተኞች ወደ የዋሁና ምስኪኑ ይመልከቱ እደጠቦት ወደመሰውያው ሲወሰድ በሸላቹ ፊት ያለ ሁከት ዝም እንዳለ ይመልከቱ፡፡ ስለኃጢአታችን የተወጋ ሐዘናችንንም የተሸከመልንን እርሱን ይመልከቱ፡፡ በዚህም በዘላቂነት መታገስና ይቅር ማለትን ይማራሉ፡፡EDA 289.4

    በክርስቶስ ላይ በሚኖረን እምነት እያንዳንዱ የባሕሪይ ጉድለት ይተካል፡፡ እያንዳንዱ ጉድፈትም ይፀዳል፡፡ እያንዳንዱ ስህተት ይታረማል፤ እያንዳንዱ ችሎታም እንዲዳብር ይደረጋል፡፡EDA 290.1

    «በርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋልና፡፡» ቆላ 2፡10EDA 290.2

    ፀሎትና እምነት የተያያዙ ናቸው፡፡ በአንድ ላይ መጠናትም ይኖርባችኋል፡፡ በእምነት በሚፀለይበት ጊዜም መለኮታዊ ሳይንስ አለው፡፡ ሕይወት ሥራው ሁሉ የተሳካ እንዲሆንለት ለማድረግ ለማድረግ የሚጥር ሁሉ ሊያስተውለው የሚገባ ሣይንስ ነው፡፡ ክርስቶስ እንዲህ ይላል፡፡ «የፀለያችሁማል፡፡ ማር 11፡24 አጠያየቃችንም እንደ እግዚአብሔር ፍላጐት መሆን እንደአለበት ግልጽ ያደርጋል፡፡ እርሱ ቃል የገባልንን ነገሮች ነው መጠየቅ ያለብን፡፡ የምናገኘውንም ሁሉ መልሰን የርሱን ፈቃድ ለማሟላት ተግባራት እንዲውሉ ማድረግ አለብን፡፡ ለሚገጥሙ ሁኔታዎች ሁሉ የገባልን የተስፋ ቃል እኩልና ተመጣጣኝ ነው፡፡EDA 290.3

    ኃጢአታችን ይቅር እንዲባልልን፤ መንፈስ ቅዱስ እንዲመጣልን የክርስቶስ ዓይነት መንፈስ ለማግኘት የርሱን ሥራ ለመሥራት ለሚያስፈልገን ጥበብና ብርታት፤ እርሱ እንደሚሰጠን ቃል የገባልንን ማንኛውንም ነገር ሁሉ ልንጠይቅ እንችላለን፡፡ ከዚያ በኋላ እንደምናገኘው ማመንና ለሰጠን አምላክም ምስጋና ማቅረብ ይገባናል፡፡EDA 290.4

    ለሚሰጠን በረከት ሌላ ውጫዊ ማስረጃ መሻት አያስፈልገንም፡፡ ስጦታው በተስፋው ቃል ውስጥ አለ፡፡ እገዚአብሔር ቃል የገባልን ነገር እንደሚፈጽምልን የተረጋገጠ ጉዳይ መሆኑን ለመፈፀምም ችሎታው ያለው መሆኑን አምነን ወደሥራችን እንድንሄድና ስጦታውም በእጃችን ውስጥ ያለ ስለሆነ እጅግ አስፈላጊ በሚሆን ጊዜ ተግባራዊ ይሆንልናል፡፡EDA 290.5

    ስለዚሁም በእግዚአብሔር ቃል መኖር ማለት ጠቅላላ ሕይወትን በእርሱ ማስረከብ ማለት ነው፡፡ ከዚያም የማያቋርጥ እርሱን የመፈለግና በእርሱ የመተማመን ስሜትና ልብም እግዚአብሔርን እንድትከተል የሚያደርግ ስሜት ብቻ ይቀራል፡፡ ፀሎት አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ለነፍስ ሕይወት ነውና፡፡ የቤተሰብ ፀሎት፤ የሕዝብ ፀሎት የየራሳቸው ቦታ አላቸው፡፡ ነገር ግን የነፍስን ሕይወት የሚሰጥና የሚያሳድግ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖር ምስጢራዊ ግንኙነት ነው፡፡EDA 291.1

    ሙሴ የክብሩ ማረፊያ እንዲሆን የታሰበውን የዚያን አስገራሚ ሕንፃ ንድፍ የተመለከተው ከእግዚአብሔር ጋር በተራራው ላይ ነበር፡፡ እርሱ ለሰው ልጅ ያሰበውን ክብርና ሞገስ በተመስጦ ልናስብበትና ከእግዚአብሔር ጋር በምስጢር ልንገናኝበት የሚገባን በተራራ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ እርሱ የገባልን ቃል ይፈፀምልን ዘንድ የባህሪያችንን ግንባታ መቅረጽ የምንችል እንሆን ዘንድ «በእነርሱም እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፡፡» ብሏልና፡፡ 2ኛ ቆሮ 6፡16EDA 291.2

    የሱስ ክርስቶስ ለምድራዊ ሕይወቱ ጥበብና ኃይል ያገኘው ብቻውን ፀጥ ባሉ ሰዓታት በሚያደርገው ፀሎት ነበር፡፡ ጧት ሲነጋጋ ወይም በምሽት ከሰማይ አባቱ ጋር ፀጥ ባለ ሰዓት ለመገናኘት ይፀልይ ነበር፡፡ ወጣቱ የርሱን ምሳሌ ይከተል፡፡ ቀኑንም በሙሉ ልባቸውን ወደ እግዚአብሔር ያቅኑ፡፡ በእያንዳንዱ እርምጃችን እንዲህ ይላል፡፡ «እኔ አምላክህ እግዚአብሔር አትፍራ እረዳሃለሁ ብየ ቀኝህን እይዛለሁና» ኢሳ 41፡13 ልጆችን እንዚህን ትምህርቶች ገና በጧት በልጅነት እደሜአቸው ቢማሩ እንዴት መታደስና ኃይል ደስታና ጣፋጭነት የተሞላበት ሁኔታ ምንኛ ወደ ሕይወታቸው በመጣላቸው ነበር፡፡EDA 291.3

    እነኝህን ትምህርቶች ራሱ በአስተማሪነት ሊገልፃቸው የሚችለው ያስተማራቸው ጌታ ብቻ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በወጣቱ ላይ ይኸን ያክል የማይሰርጽበት ምክንያት ብዙ ወላጆችና መምህራን የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚያምኑ ቢናገሩም በሕይወታቸው ግን የርሱን ኃይል የካዱ በመሆናቸው ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወጣቶች የቃሉ ኃይል እንዲሰማቸው ይደረጋል፡፡ የክርስቶስን ፍቅር ክቡርነት ያያሉ፡፡ የርሱን ባህሪይ ውበትና ለርሱ አገልግሎት የተሰጠች ሕይወት የሚኖራትን እድሎች ያያሉ፡፡ በሌላ በኩል ግን የእግዚአብሔርን እቅዶች ለማስፈፀም እየገለገልን ነው የሚሉትን ሰዎች ሕይወት በማየት ያነፃጽራሉ፡፡ ለነብዩ ሕዝቅኤል ከተናገሩት ቃላት ስንቶቹ ናቸው እውነት ሆነው የተገኙት፡፡EDA 292.1

    ያንተ ሕዝብ «ሕዝቡ እነሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ ቃልህንም ይሰማሉ፡፡ ግን አያደርጉትም በአፋቸው ብዙ ፍቅር ይገልጣሉ ልባቸው ግን ስስታቸውን ትከተላለች፡፡... ቃልህንም ይሰማሉ፡፡ ነገር ግን አያደርጉትም፡፡» ሕዝቅ 33፡30-32EDA 292.2

    መጽሐፍ ቅዱስ እንደ አንድ የሥነ ምግባር መማሪያ ከጊዜው መንፈስ ጋር እስከ ሄደ ድረስና በዓለም ላይ የሚኖረንን ደረጃ እስከ ጠበቀልን ድረስና እንደ አንድ ጥሩ መጽሐፍ አድርጐ መቀበል አንድ ነገር ነው፡፡ የሕይወት አምላክ ቃል እንደሆነ በእንደሆነ በእርግጥም ነውና እንደ አንድ ሕይወታችን የሆነ ቃል ሥራዎቻችን የምንናገራቸውን ቃላት አስተሳሰቦቻችን የሚቀርጽልን ቃል እንደሆነ አድርጐ መቀበል ሌላ ነገር ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ከዚህ ባነሰ ደረጃ መቀበል መካድ ነው፡፡ ይህ ክህደት በወጣቱ ውስጥ የሚታየው እውነትን በመካድና ታማኝ ባለመሆኑ ነው፡፡EDA 292.3

    ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቀው የተፋፋመ ሁኔተ ዓለምን በባለቤትነት እየያዛት ነው፡፡ በፈንጠዝያ ገንዘብ በማጋበስ፣ በሥልጣን በመሸቀዳደም ለሕልውናም በማደረግ ትግል አካልን አእምሮን ነፍስን አጠቃልሎ የሚይዝ እጅግ ብርቱ ኃይል አለ፡፡ በዚህ የእብደት ግፊያ ውስጥ ሁሉ እግዚአብሔር እየተናገረ ነው፡፡ ከዚያ ተለይተው ወጥተን ከእርሱ ጋር እንድንገናኝ ይጠራናል፡፡ «እኔም አምላክ አንደሆንሁ እወቁ» መዝ 46፡10EDA 293.1

    ብዙዎች ለጾምና ፀሎት ልባቸው በተመስጦ በሚያሰባስቡበት ሰዓት እንኳ ከእግዚአብሔር ጋር መኖር የሚገባውን የግንኙነት በረከት አያገኙም በታላቅ ጥላቻ ውስጥ ገብተዋል፡፡ በችኮላ ርምጃዎች የክርስቶስ ፍቅር በሚገኝበት ዙሪያ ክቦሽ ውስጥ እየዳበሱ ምናልባትም ለአንድ አፍታ ቆም ብለው መመለስ ብቻ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እርሱ ምክሩን እስከሚሰጣቸው አይጠብቁም፡፡ ከመለኮታዊው መምህር ጋር ለመቆየት ጊዜ የላቸውም፡፡ ከነሸክማቸው ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ፡፡EDA 293.2

    እነዚህ ሠራተኞች የብርታትን ምስጢር እስከሚማሩ ድረስ የከፍተኛ ደረጃ ውጤቶችን ማግኘት አይችሉም፡፡ ለራሳቸው የሚያስቡበት ጊዜ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ለመፀለይ ከእግዚአብሔር ጋር በመገናኘት የአካል የሕሊናና የመንፈስ መታደስ ለማግኘት ጊዜ ወስደው መመደብ አለባቸው ልብን የሚያነሳሳው የርሱ መንፈስ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይኸንን ሲቀበሉ ትኩስ በሆነ አዲስ ሕይወት ቀልጣፋ ይሆናሉ፡፡ የደከመው አካልና አእምሮ ይታደሳል፡፡ ሸክም የበዛበት ልብም ይቃለልለታል፡፡ EDA 293.3

    የሚያስፈልገን እርሱ ባለበት ለአንድ አፍታ ቆም ማለት ሳይሆን ከክርስቶስ ጋር በግል ግንኙነት፤ ከርሱ ጋር በወዳጅነት መቀመጥ ነው፡፡ ወላጆችና መምህራን በራሳቸው ሕይወት ውስጥ ሲማሩ ከመዝሙሮች መዝሙር ውስጥ ያለውን እነኚህን የከበሩ ቃላት የቤቶቻችን ልጆች የትምህርት ቤት ተማሪዎቻችን ሁሉ ደስተኞች ይሆናሉ፡፡EDA 294.1

    «በጫካ ውስጥ እንደለ የበለስ ዛፍ
    የምወደው በልጆች መካከል ነው፡፡
    በጥላው ሥር በታላቅ ደስታ እቀመጣለሁ፡፡
    ፍሬውም እጅግ አድርጐ ይጣፍጠኛል፡፡
    ወደ ድግስ ቤት አመጣኝ ቃሉም በላየ
    ላይ ፍቅርን መላ፡፡»
    EDA 294.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents