Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 12—ሌሎች ተጨባጭ ትምህርቶች

    «ጠቢብ የሆኑ እነዚህን ነገሮች ይረዳሉ፡፡
    አፍቃሪ የሆነውን የጌታን ቸርነትም ያስተውላሉ፡፡»
    EDA 123.1

    የእግዚአብሔር የማዳን ኃይል በፍጥረት ሁሉ ዘንድ ሞልቷል፡፡ አንድ ዛፍ ከተቆረጠ አንድ ሰው ከቆሰለ ወይም አጥንቱ ከተሰበረ ተፈጥሮ ያንን ጉዳት ለመጠገን ፈጥኖ ሥራ ይጀምራል፡፡ የመፈወሱ ሥራ ከማስፈለጉ በፊት እንኳ እነኝህ የማዳንን ሠራ የሚያከናውኑ ብልቶች ተዘጋጀተው እየተቀመጡ ናቸው፡፡ አንዱ የአካል ክፍል እንደተጐዳ ወዲያውኑ እያንዳንዱ ኃይል ወደ መልሶ ግንባታ ሥራ ያዘነብላል፡፡ በመንፈሳዊው ዓለምም ያው ነው፡፡ ኃጢአት ነገሩን አስፈላጊ ሳያደርግው በፊት እግዚአበሔር የማዳን መፍትሄውን ቀድሞ አዘጋጅቷል፡፡ ወደ ፈተና የምታዘነብል እያንዳንዷ ነፍስ ትቆስላለች በክፋት ትበልዛለች፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ባለበት ቦታ ሁሉ መድኃኔዓለም አለ፡፡ «ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ የተጠቁትም ነፃ አወጣ ዘንድ» ሉቃ 4፡18 ይህ ነው የክርስቶስ ሥራ፡፡EDA 123.2

    በዚህ ሥራ ውስጥ እኛም መተባበር አለብን፡፡ «ሰው በማናቸውም በደል ሳንካ ቢገኝ በየዋሃት መንገድ አቅኑት፡፡» ገላት 6፡1 «መመለስ» ወይም ማቅናት የሚለው ቃል ትርጉም የወለቀ አጥንትን በቦታው አስተካክሎ ማስገባት ማለት ነው፡፡ ጥሩ ስዕላዊ መግለጫ ነው፡፡ ወደስህተት ወይም ኃጢአት ውስጥ የገባ ሰው በዙሪያው ካለው ከማናቸውም ዓይነት ግንኙነት ውጪ የተጣለ ነው፡፡ ስህተቱን ሊገነዘብ ይችል ይሆናል፡፡ እጅግ ልቡን ሰብሮ ተፀጽቶም ይሆናል፡፡ ነገር ግን ራሱን በራሱ መመለስ ወይም ማዳን አይቻለውም፡፡ በተምታታና በተደበላለቀ ቀውስ ውስጥ ተጠቅልሎ ረዳት የለሽ ሆኖ ነው ያለው፡፡ መልሶ መሠራት አለበት፡፡ መፈወስና እንደገና መታደስ መንፈሳዊያን የሆናችሁ እንደዚህ ያለውን ሰው በየዋሀት መንፈስ አቅኑት፡፡ ገላ 6፡1 ለመፈወስ ችሎታ ያለው ከክርስቶስ ልብ የሚፈስሰው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ በወስጡ ያ ፍቅር የሚፈስበት ሰው ብቻ ነው ከዛፍ እዥ ወይም ከሰውነት በሚወጣ ደም የቆሰለችን ነፍስ መመለስ የሚቻለው፡፡EDA 123.3

    የፍቅር ብልቶች አስገራሚ ኃይል አላቸው፡፡ መለኮታዊ ናቸውና፡፡ «ቁጣን የምትመልስ» ለሰላሳ መልስ «የምትታገስና ቸርነት የምታደርግ» ፍቅር ለሀጢአትን ብዛት የምትሸፍን» ደግነት እነዚህን ትምህርቶች አስተውለናቸዋልን? ለሕይወታችን የተሰጠው ምንኛ ፈዋሽ የሆነ ኃይል ነው? (ምሳ 15፡1 1ኛ ቆሮ 13፡4 1ኛ ጴጥ 4፡8) ሕይወት በምን ዓይነት ሁኔታ ይለወጣል! መሬትም በአስደናቂ ሁኔታ ፍፁም በሰማይ ተምሳሌት ትለወጣለች፡፡EDA 124.1

    እነኝህ ግሩም ድንቅ ትምህርቶች በቀላሉ ለህፃናት እንኳን ለማስተማርና ለማስተዋል የሚመቹ ናቸው፡፡ የልጅ ልብ በቀላሉ የሚቀበልና ገር ነው፡፡ እኛ በእድሜ ጠና ያልነው ደግሞ «እንደ ሕፃናት» ስንሆን (ማቴ 18፡3) የመድኃኒታችንን የዋህ ርጋታ የተሞላበት ገር ፍቅር ስንማር የታናናሾቻችንን ልብ ለመንካትና የፍቅርን የመፈወስ አገልግሎት ለማስተማር ከባድ አይሆንብንም፡፡EDA 124.2

    በጥቃቅኖቹም ሆነ በትልልቆቹ የእግዚአብሔር ሥራዎች ውስጥ ሁሉ ፍጽምና ተሞልቶባቸዋል፡፡ ዓለማትን ሁሉ በሕዋው ላይ ያንጠለጠለው ያው እጅ ነው፡፡ በየሜዳው ላይ ያሉትን አበባዎች የገራ፣ በየመንገዱ በዘልማድ የሚበቅሉ አበባዎችን አንድ ላባ ወስዳችሁ አጉልቶ በሚያሳይ መነጽር ተመልከቱ፡፡ እናም በሁሉም አካሎቿ ላይ ያለው ድንቅ ውበት ፍጽምና አስተውሉ፡፡ ትህትና በተላበሰው እድሏ እውነተኛ ክብር ታገኝበት ዘንድ የተለመደው ግዴታ ፍቅር በተሞላበት ታማኝነት በእግዚአብሔር ፊት መልካምና የሚያምሩ ናቸው፡፡ ለትንንሽ ነገሮች በጥንቃቄ መከታተል ከርሱ ጋር የምናብር ሠራተኞች ያደርገናል፡፡ ሁሉን የሚያውቅና ተመልካች የሆነ እርሱ ያሰበልንን ያስገኝልናል፡፡EDA 124.3

    በሰማይ ላይ በቅስት የጌጥ መብራት የምታሳየው ቀስተዳመና «በእግዚአብሔርና በሰው መካከል በምድር ላይ በሚኖር ሕያው ነፍስ ሁሉ የዘላለም ቃል» (ዘፍ 9፡16) ናት፡፡ ከዙፋኑ በስተላይ የሚከበው ቀስተዳመና እግዚአብሔር ልጆቹን ለገባው የሰላም ቃልኪዳን ምልክት ነው፡፡EDA 125.1

    በዳመናው ውስጥ የሚታየው ቅስት በፀሐይ ብርሃን ጨረርና በዝናቡ ካፊያ አማካይነት የተፈጠረ ሽብርቅ ውጤት እንደመሆኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ዙፋን በላይ ያለው ቅስትም የምርቱንና የፍርዱን አንድነት ያመለክታል፡፡ በሀጢአት የተሞላ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ንስሀ በሚገባ ነፍስ እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል፡ «ቤዛ አግኝቻለሁ» (ኢዮ 33፡24) አንተ ሕያው ሁን፡፡EDA 125.2

    «ይህ ለእኔ እንደኖህ ውኃ ነው፡፡ የኖህ ውሃ ደግሞ በምድር ላይ እንዳያልፍ እንደማልሁ አንችን እንዳልቆጣ እንዳልዘልፍሽም ምያለሁ፡፡ ተራሮች ይፈልሳሉ ኮረብቶችም ይወገዳሉ ቸርነቱ ግን ከአንች ዘንድ አይፈልስም፡፡ የሰላሜም ቃልኪዳን አይወገድም ይላል መሀሪሽ እግዚአብሔር፡፡» ኢሳ 54፡9‚10EDA 125.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents