Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 13—ሕሊና እና መንፈሳዊ ትምህርት

  «አካላቶችህ እጅግ ልዩ
  በሆነው እውቀት ይሞላሉ፡፡»
  EDA 133.1

  ለአዕምሮ ለመንፈስ እንዲሁም ለአካል የሚጠቅም ብርታት የሚገኘው በብዙ ጥረት መሆኑ የእግዚአብሔር ሕግ ነው፡፡ የሚያጐለብተውና የሚያዳብረው ልምምድ ነው፡፡ ከዚህ ሕግ ጋር ስንዋሀድ ለአእምሮና ለመንፈስ መዳበር የሚጠቅም ነገር እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ሰጥቶናል፡፡EDA 133.2

  መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህኛውም ሆነ ለሚመጣው ዓለም ኑሮአቸው የሚያስፈልጋቸውን ጠቃሚ መሠረታዊ ሐሳቦች ሁሉ ይዞአል፡፡ እነኝህ መሠታዊ ሀሳቦች ደገሞ በሁሉም ሰው ዘንድ ሊስተዋሉ የሚቻሉ ናቸው፡፡ ትምህርቱን በአድናቆት የሚቀበል መንፈስ ያለው ማናቸውም ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚያነብበት ጊዜ አንዲት ገጽ እንኳ ብትሆን ጠቃሚ ሀሳቦች ሳያገኝ አያልፍም፡፡ ነገር ግን ዋናው ጥቅም የሚገኘው አልፎ አልፎ በሚደረግና ባልተያያዘ ጥናት አይደለም፡፡ ታላቁ የእውነት ሥርዓት ችኩልና ግዴየለሽ በሆነ አንባቢ አማካይነት የሚሰጥ አይደለም፡፡ ብዙዎቹ የወርቅ መዝገቦች ከላይኛው የመሮት ልባስ ሥር በጣም ጠለቅ ብለው ነው የሚገኙት፡፡ ሊደርስባቸው የሚችሉትም ትጋት በተሞላበት ምርምርና ባላቋረጠ ጥረት ነው፡፡ በታላቁ ጥቅል ውስጥ የሚካተቱ እውነቶች ተፈልገው መሰብሰብ አለባቸው፡፡ «ከዚህም ጥቂት ከዝያም ጥቂት፡፡» ኢሳ 28፡10EDA 133.3

  እንግዲህ እንዲህ እየተፈለጉ ሲሰበሰቡ አንደኛው ከሌላው ጋር ፍፁምና በትክክል የሚስማማ ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ወንጌል የሌሎቹ ደጋፊ፣ እያንዳንዱ ትንቢት የሌላው መግለጫና ማብራሪያ፣ እያንዳንዱ የልማት እውነት ለሌላው ውነት መግለጫ ይሆናል፡፡ የአይሁዶች የኢኮኖሚ አያያዝ ዓይነት በወንጌል ውስጥ ተብራርቷል፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እያንዳንዱ መሠታዊ ሀሳብ የራሷ ቦታ አላት፡፡ እያንዳንዷ እውቀትም የራሷ የሆነ ፍሬ አላት፡፡ በንድፍና በአፈፃፀም ላይ ያለው የተሟላ ቅርጽ ባለቤት ለሆነው ደራሲ ምስክርነት ይሰጣሉ፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ግሩም ድንቅ ቅርጽ ፈልፍሎ ሊያንጸው የሚችለው የሰው አእምሮ ሳይሆን ሊያስበው የሚችለው ወሰን የሌለበት አምላክ ብቻ ነው፡፡EDA 134.1

  የተለያዩትን ክፍሎች በመፈላለግና መስተጋብራቸውንም ለማጥናት የሰው ልጅ አእምሮ ዋና ዋና ክፍሎች እጅግ ከባድ ሥራ ተጥሎባቸዋል፡፡ ማንም ሰው ቢሆን የአእምሮ ጉልበቱን ሳያጠናክር በእንዲህ ዓይነት ሥራ ውስጥ ሊጠመድ አይችልም፡፡EDA 134.2

  በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ውስጥ ከተካተተው ቁምነገር ሁሉ እውነትን ማፈላለግ እና ማሰባሰብ ብቻም አይደለም ጥቅም የሚገኘው፡፡ የቀረቡትን የጥናት ርዕሶች ለመጨበጥ የሚደረገውን ጥረትም ያካትታል እንጅ፡፡ በተለመዱ ጉዳዮች ብቻ የተሞላ አዕምሮ ቃጩራና ደካማ ይሆናል፡፡ ታላላቅና ራቅ ብለው የመጠቁ ዕውቶችን ለማስተዋል ተገድዶ የማያውቅ አዕምሮ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የማደግ ኃይሉን ያጣል፡፡ ከዚህ የማሽቆልቆል ባህሪይ ለመዳንና ወደ እድገት እንዲያመራ ለመቀስቀስ ከሚረዱት ነገሮች የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናትን የሚስተካከል ሌላ መፍትሄ የለም፡፡ እንደ አንድ የአእምሮ ማሰለጠኛ መጽሐፍ ቅዱስ ከሌላ ከማንኛውም መጽሐፍ በበለጠ ወይም ሌሎች መፃህፍት ሁሉ በአንድ ላይ ሆነው ከሚሰጡት የበለጠ ውጤት ያስገኛል፡፡ የርዕሶቹ ታላቅነት ክቡርና ቀላል ንግግሮቹ ፣ የሐሳቦቹ ውበት፣ ሌሎች ማንኛቸውም ነገሮች ሊያደርጉ ከሚችሉት በበለጠ ፍጥነት ሐሳቦችን ያነሳሳሉ፡፡ ግሩም ድንቅ የሆኑ የመገለጡን እውነቶችን ለመጨበጥ ከሚደረግ ጥረት የበለጠ ሌላ ዓይነት ጥናት እንዲህ ዓይነት የእእምሮ ኃይል ሊያስገኝ አይችልም፡፡ ወሰን ከሌለበት አምላክ ሀሳብ ጋር ሀሳቡ የተገናኘ ሰው ያለው ዕድል መስፋፋትና መጠንከር ብቻ ነው፡፡EDA 134.3

  በመንፈሳዊ ተፈጥሮ እድገት ውስጥ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይል ከሁሉም የበለጠ ታላቅ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲወዳጅ የተፈጠረው ሰው እውነተኛውን ሕይወትና እድገት ማግኘት የሚችለው በእንዲህ ዓይነት ዝምድና ብቻ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ከፍተኛውን ደስታውን እንዲያገኝ የተፈጠረው የሰው ልጅ በሌላ በምንም ዓይነት የልቡን ጉጉት የሚያርስለትና የነፍሱን ረሐብና ጥማት ሊያረካለት የሚችል ነገር ከቶ አያገኝም፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ፍፁም በሆነና ለመማር በሚችል መንፈስ የሚያጠና ሰው እውነቶቹንም ለማስተዋል የሚሻ ከደራሲው ጋር እንዲገናኝ ይሆናል፡፡ እናም በራሱ ምርጫ ብቻ ካልሆነ በስተቀር ለእድገቱ ወሰን አይኖረውም፡፡EDA 135.1

  አሠራሩ ለየት ያለና እጅግ ሰፊ እንደመሆኑ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ የእያንዳንዱን ሰው አእምሮ የማያስደስትና የእያንዳንዱን ሰው ልብ የሚማፀን አንድ ነገር አለበት፡፡ በገጾቹ ላይ ታሪክ ተጽፎአል፡፡ እጅግ ጥንታዊ የሆነ ታሪክ፡፡ እጅግ እውነተኛ የሆነ የሕይወት ታሪክ፡፡ አንድን ግዛት ለመቆጣጠር የሚያስችል መንግሥታዊ መሠረተ ሐሳቦች፣ የቤት ውስጥ አስተዳደር ደንቦች፣ የሰው ልጅ ጥበብ እስካሁን ያልደረሰባቸው መሠረታዊ ሀሳቦች እጅግ ጥልቀት ያለውን የፍልስፍና ሀሳቦችን ይዟል፡፡ እጅግ ጣፋጭ እና ድንቅ የሆኑ ሥነ-ግጥሞችን፣ ስሜትን የሚነኩና ልብ የሚሰብሩ ቅኔዎችን ይዟል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሁፎች ማንም ሰብዓዊ ደራሲ ካሳተማቸው መጽሐፍት በላይ በቁጥር ለማስቀመጥ በማይቻል ወደር በሌለው ብልጫ ፋይዳ አላቸው፡፡ እንደዚህም ሆኖ እንኳ ሲነፃፀሩ ከትልቁ ዋና ሐሳብ ጋር ከሚኖራቸው ግንኙነት አንፃር ሲታዩ ደግሞ ወሰን የሌለው የስፋትና ወሰን የሌለው ታላቅ የፋይዳ ልዩነት አላቸው፡፡ ከዚህ ሀሳብ (ነጥብ) አንፃር ሲታይ እያንዳንዱ ዋና ሐሳብ አዲስ አስፈላጊነት ወይም ጠቀሜታ አለው፡፡ በቁላል አገላለጽ የተብራሩ እውነቶች እንደሰማይ በራቁና ዘለዓለማዊነትን የሚያካልል መሠረታዊ ሀሳቦች ተካትተውበታል፡፡EDA 135.2

  የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ሐሳብ በጠቅላላው በመጽሐፉ ውስጥ ያሉት እያንዳንዱ ርዕሶች ያተኮሩበት ማዕከላዊ ሐሳብ በመዳን ዕቅድ ላይ ነው፡፡ ዋናው ዓላማው የእግዚአብሔርን ተምሳሌት በሰው ልጅ መንፈስ ውስጥ መልሶ ማስቀመጥ ነው፡፡ በኤደን ገነት ውስጥ ከተገባው የመጀመሪያ የተስፋ ቃል በመጨረሻም በራዕይ ዮሐንስ ከተገለፀው የክብር ተስፋ ቃል «ፊቱንም ያያሉ ስሙም በግንባራቸው ይሆናል፡፡» ዮሐ ራዕ 22፡4 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለ የእያንዳንዱ መጽሐፍና በእያንዳንዱ ምንባብ ላይ ያለው ሸክም ሁሉ ይኸንን አስገራሚ ርዕስ የሚገልጡ የሰውን ልጅ ወደላይ መነሳትና «በጌታ በየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መነሳትን ለሚሰጠን» የእግዚአብሔር ኃይል ይገልፃሉ፡፡ 1ኛ ቆሮ 15፡57EDA 136.1

  ይኸንን ሀሳብ የያዘ ሰው ለማጥናት ከፈለገ እፊቱ የማያልቅ የጥናት መልስክ ተከፍቶለታል፡፡ የእግዚአብሔርን የቃሉን ግምጃ ቤት የሚከፍትበት ቁለፍ አግኝቷል ማለት ነው፡፡EDA 136.2

  የመዳን ሳይንስ የሳይንሶች ሁሉ ሳይንስ ነው፡፡ የመላዕክትና የማይወድቀው ዓለም አለቆች ጥናት ሳይንስ ነው፡፡ የጌታችንና የመድኃኒታችንን ትኩረት የያዘ ሳይንስ ወሰን በሌለበት አምላክ አእምሮ ወደ ተዘጋጀው ዓላማ ዘልቆ የሚገዛ ሳይንስ «ከዘለዓለም ዘመንም የተሰወረው፡፡» ሮሜ 16፡25 በእግዚአብሔር የዳኑት ሰዎች የሚያጠኑት የዘለዓለም ሳይንስ ነው፡፡ ይህም የሰው ልጅ ሊደርስበት የሚቻለው ከፍተኛ ጥናት ነው፡፡ ሌላው ጥናት ፈጽሞ ሊያደርግ የማይችለውን ይህ ጥናት አእምሮን ቀልጣፋ ያደርጋል ነፍስንም ወደላይ ያነሳሳል፡፡EDA 136.3

  «የእውቀትም ብልጫዋ ጥበብ ገንዘብ ላደረጋት ሕይወትን እንድትሰጥ ነው፡፡» «እኔ የነገርኳችሁ ቃል» አለ የሱስ «መንፈስ ነው ሕይወትም ነው፡፡» «የላክኸውን የሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት» መክ 7፡12 ዮሐ 6፡63 ምዕ 17፡3EDA 137.1

  የመፍጠር ችሎታ ያለው ኃይል ዓለማትን ወደሕልውና ያመጣ በእግዚአብሔረ ቃል ውስጥ ያለው ኃይል ነው፡፡ ይህ ቃል ኃይሉን ከፍሎ ይሰጣል፡፡ ሕይወት ያስገኛል፡፡ እያንዳንዱ ትዕዛዝ ተስፋ ነው፡፡ በፈቃደኝነት ከተቀበሉት ወደ ነፍስ ውስጥም ካስገቡት ወሰን የሌለበትን አምላክ ሕይወት ያመጣልናል፡፡ ተፈጥሮአችንን ይለውጠዋል፡፡ ነፍስንም እንደገና በእግዚአብሔር አምሳል እንድትፈጠር ያደርጋታል፡፡EDA 137.2

  ስለዚህም የተከፈለችው ነፍስም እንደዚያው እንድትቀጥል ትደረጋለች፡፡ ሰው የሚኖረው «ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጅ» ማቲ 4፡4EDA 137.3

  አእምሮና ነፍስ በሚመግባቸው ነገር ላይ ይመሰረታሉ፡፡ በምን ላይ እንደሚመገብ ለመወሰንም በእኛ ላይ ይተማመናል፡፡ ሐሳቦቹን ሊይዝለትና ባህሪውን ሊቀርጽለት የሚችለውን ርዕስ መምረጥ የእያንዳንዱ ሰው የራሱ ምርጫ ነው፡፡ ወደ መጽሐፎቹ ዘልቆ በመግባት ለሚጠቀም ማንኛውም ሰው ሁሉ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡፡ «የሕጌን ብዛት ጽፌልሃለሁ፡፡» «ወደ እኔ ጩህ እኔም እሰማሃለሁ አንተ የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ፡፡» ሆሴ 8፡12 ኤር 33፡3EDA 137.4

  የእግዚአብሔርን ቃል በእጆቹ ይዞ ማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር የሕይወት ዕጣው የትም ብትወድቅ በራሱ ምርጫ የሚፈልገውን እንዲህ ዓይነት ጓደኝነት ሊያገኝ ይችላል፡፡ በየገጾቹም እጅግ ቅዱስ የሆነውንና ከሰው ዘርም ውስጥ እጅግ በጣም ጥሩ ከሆነው አምላክ ጋር በመነጋገር ዘላለማዊ ድምጽ ከሰዎች ጋር ሲነጋገርም ሊሰማ ይችላል፡፡ እያጠናና በተመስጾ ፀሎት ሐሳቡን አሰባስቦ «መላዕክት ሊመለከቱት በሚመኙት» 1ኛ ጴጥ 1፡12 ነገር ላይ ሲያተኩር ወዳጅነታቸውን ያገኛል፡፡ የሰማዩን መምህር እርምጃዎች ሊከተልና በተራራው ላይ በሜዳና በባህር ዳርቻ ሲያስተምር የተሰማውን ድምጽ ሊሰማ ይችላል፡፡ በዚህ ዓለም ሲኖር በሰማይ ድባብ ውስጥ እንዳለ ሆኖ እየተሰማው ይኖራል፡፡ በምድር ላይ በሀዘን ላሉና ለተፈተኑ ሰዎች የተስፋና ቀድስናን የመመኘት ሀሳብን እያካፈለ ራሱም ከማይታየው ጋር ወዳጅነቱን ከጊዜ ወደጊዜ እያጠበቀ የሚሄድ እንደሱም በድሮ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር የተራመዱ ከጊዜ ወደጊዜ ወደ ዘለዓለማዊው ዓለም በሮች ተከፍተውላቸው እዚየ እስከሚገቡ ድረስ እየቀረቡ እንደሄዱ ሰዎች ይሆናል፡፡ በዚያም ሥፍራ እንግዳ አይሆንም፡፡ ሰላምታ የሚያቀርቡለት ድምጾች የቅዱሳን ድምጾች፣ ሳይታዩ ግን በምድር ላይ የእሱ ጓደኞች የነበሩ፣ እዚህ መለየትንና ማፍቀርን የተማረባቸው ድምጾች ናቸው፡፡ በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት ከሰማያት ጋር የመቀራረብ ዝምድና የፈጠረ ሰው ወደ ሰማይ ሲሄድ በራሱ ቤት ውስጥ ይገባል ፡፡EDA 138.1

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents