Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 20—መጽሐፍ ቅዱስን ማስተማርና ማጥናት

  «ጆሮህን ወደ ጥበብ አዘንብል፡፡»
  «መዝገቦችን እንደምትሻ
  እርሷንም ፈልጋት፡፡»
  EDA 206.1

  የሱስ በልጅነት በወጣትነቱና በጐልማሳነቱ መጽሐፍ ቅዱስን ያጠና ነበር፡፡ እንደ አንድ ትንሽ ሕፃን በእናቱ ጉልበቶች ሥር ሆኖ ከትንቢት ብራናዎች ብዙ ይማር ነበር፡፡ በወጣትነቱ ደግሞ ዘወትር ጧት በማለዳ እና ወደ ምሽት አካባቢ ደግሞ ምንጊዜም የሚገኘው በተራራው አካባቢ በጫካው ዛፎች ውስጥ ፀጥታ በተሞላበት ሰዓት ይፀልይና የእግዚአብሔርን ቃል ያጠና ነበር፡፡ በአገልግሎት ጊዜው ከመጽሐፍት ጋር የሚኖረው ግንኙነትና የጠበቀ ትውውቅ በትጋት ያጠናቸው እንደ ነበረ መስክረውለታል፡፡ እኛም ልናገኝ እንደምንችለው ሁሉ ከመጽሐፍቱ ውስጥ ባገኘው እውቀት፤ አስገራሚ ኃይሉ መንፈሳዊዩና የእምሮው ኃይል፤ እንደ አንድ የትምህርት መሣሪያቱ መጽሐፍ ቅዱስ የሚኖረውን ዋጋ አስመስክሯል፡፡EDA 206.2

  የሰማዩ አባታችንም ቃሉን በመስጠት ረገድ ልጆቹን አልዘለላቸውም፡፡ ሰዎች በፃፉት ውስጥ ሁሉ ልብን እንደዚህ መያዝ የሚችል ምን ነገር ይገኛል? የታናናሾችን ልብ የሚያነቃቃና ጉጉት የሚያሳድርባቸው እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ያለ ሌላ ምን ይገኛል?EDA 206.3

  በእነኝህ ቀላል ታሪኮች ውስጥ ታላቁ የእግዚአብሔር ሕግ መሠታዊ ሐሳቦች ግልጽ እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ ወላጆችና መምህራን ስለ ጌታ የሚኖርን ሐሳብ በአዕምሮ ውስጥ ለማስገባት ለልጁ የማስተዋል አቅም የሚመጥኑና እጅግ ተስማሚ የሆኑ መግለጫዎችን ቀደም ብለው መጀመር አለባቸው፡፡ «…. ለልጆችህም አስተምረው፤ በቤትህም ስትቀመጥ፤ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛም ስትነሳም ተጫወተው፡፡» ዘዳግ 6፡7 ፡፡EDA 206.4

  የትምህርት መሣሪያዎች፣ ጥቁር ሰሌዳዎች፣ ካርታዎችና ስዕሎች እነዚህን ትምህርቶች ለመግለጽና በአእምሮአቸው ውስጥ እንዲሰርጽ ለማድረግ በጣም የሚረዱ ነገሮች ናቸው፡፡ ወላጆችና መምህራን ያለማቋረጥ የተሻሻሉ ልዩ ልዩ ዘዴዎችን መፈለግ አለባቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ስናስተምር በትኩሱ ሐሳባችንና እጅግ ምርጥ በሆነው ዘዴዎቻችን እንዲሁም እጅግ ልባዊ በሆነው ቅን ጥረታችን ነው፡፡EDA 207.1

  ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚኖራቸውን ፍቅር ለማነሳሳትና ለማበረታታት ዋና መሠረት ሊሆንላቸው የሚችለው የፀሎት አገልግሎት ሰዓት ነው፡፡ የጠዋትና የማታ የስግድት ሰዓቶች ከቀኑ ውሎአችን የሚረዱ እጅግ ጣፋጭ ጊዜያት መሆን አለባቸው፡፡ ይህ ሰዓት ወላጆችና ልጆች ተሰብስበው ከየሱስ ጋር የሚገናኙበትና ቅዱስ መላዕክት ወደ ቤታቸው እንዲገቡ የሚጋብዙበት ሰዓት በመሆኑ ምንም ዓይነት ችግርና ያልሆነ ሐሳብ ሊያቋርጠው እንደማይገባ መስተዋል አለበት፡፡ አገልግሎቱ አጭርና ሕይወት ያለው፤ ከሁኔታዎች ጋር የሚስማማ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለያዩ ይሁን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ፣ በማጥናትና የእግዚአብሔርን ሕግ አዘውትሮ በመደጋገም ሁሉም በንቃት ይሳተፍ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትኛው ቢነበብ እንደሚፈልጉ ልጆች ራሳቸው እንዲመርጡ ቢፈቀድላቸው ፍላጐታቸው እንዲጨምር ለማድረግ ይረዳል፡፡ በዚያው ጊዜ በዚያው ላይ ጠይቋቸው፣ እነሱም እንዲጠይቁ ፍቀዱላቸው፡፡ ትርጉሙን ለማብራራት የሚያስችል አንድ ነገር አንሱ፡፡ በዚህ ዓይነት አገልግሎቱ ካልተራዘመባችሁ በስተቀር ትንንሾቹ ልጆች በፀሎት እንዲካፈሉና ከመዝሙርም አንዷን አዝማች ብቻ በመዘመር እንዲካፈሉ አድርጉ፡፡EDA 207.2

  እንዲህ ዓይነት አገልግሎት መሆን በሚገባው መልኩ ለማዘጋጀት ዝግጅቱ በሚገባ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ወላጆችም በየቀኑ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከልጆቻቸው ጋር ጊዜ ሊወስዱ ይገባቸዋል፡፡ ጥረት፣ ዕቅድና ለማዘጋጀትም ጊዜ መውሰዱ አያጠራጥርም፡፡ ነገር ግን ጥረቱ እጥፍ ዋጋ ያስገኛል፡፡EDA 208.1

  የእርሱን ሐሳቦች ለማስተማር በሚደረግ ዝግጅት እግዚአብሔር በወላጆች ልብ ውስጥ እንዲቀመጡ ያዝዛል፡፡ «እነሆ ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ ለልጆችህም አስተምረው» ዘዳ 6፡6,7 ለልጆቻችን በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲሳቡ ለማድረግ እኛ ራሳችን የመጽሐፍ ቅዱስ ፍላጐት ሊኖረን ይገባል፡፡ በውስጣቸው የጥናት ፍቅር እንዲያድርባቸው ለማነቃቃት እኛ ራሳችን ፍቅሩ ሊኖረን ያስፈልጋል፡፡ እኛ የምንሰጣቸውን ትምህርት የሚቀርጹት እኛ በምንሰጠው ትኩረት መጠን ነው፡፡EDA 208.2

  እግዚአብሔር ቃሉን የሚያስተምር ሰው ይሆን ዘንድ አብርሃምን ጠራው፡፡ የአንድ ታላቅ ሕዝብ አባት እንዲሆን መረጠው፡፡ ምክንያቱም አብርሃም ልጆቹንና ቤቱን በእግዚአብሔር መርሆች መሠረት ለመምራትና ለማስተማር የሚችል ሰው መሆኑን አውቋልና፡፡ ለአብርሃምም የማስተማር ኃይል የሰጠው የራሱ ሕይወት ልዩ ባህሪይ ነው፡፡ በነፍስ ወከፍ ሲቆጠር ከአንድ ሽህ በላይ አባላት የነበረው ትልቁ ቤተሰቡ፣ በርካታ አባውራዎችን የያዘ ሲሆን ምንም እንኳ ከእነኛ አነስ ቢልም የአዲስ አማኞች ቁጥርም ጥቂት አልነበረም፡፡ በእንዲህ ዓይነት ቤተሰብ አናት ላይ ጠንከር ያለ እጅ የሚፈልግ ነበር፡፡ ደካማ ወይም ወላዋይ የአሠራር ዘዴ ይኸንን ሊፈጽም አይችልም፡፡ እግዚአብሔር ስለ አብርሃም ይኸንን ተናገረ፡፡ «ልጆቹንና ቤተሰቡን ማዘዝ እንደሚችል አውቃለሁ፡፡» ዘፍ 18፡29፡፡ ሥልጣኑን ተግባራዊ ያደርግ የነበረው በጥበብና በገርነት ስለ ነበረ ብዙ ልቦችን አሸነፈ፡፡ ስለዚህም መለኮታዊው ጠባቂ እንዲህ ሲል መሰከረለት፡፡ «ጽድቅንና ፍርድን ለማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ» ዘፍ 18፡19 የአብርሃም ማራኪነት ደግሞ ከቤተሰቡ አልፎ ተስፋፋ፡፡ በሄደበት ሁሉ ድንኳኑን ይተክላል፡፡ ከጐኑም መሰውያና ፀሎት የሚያደርስበት ስፍራ ያዘጋጃል፡፡ ድንኳኑ ሲነሳ መሰውያው እዚያ ይቀራል፡፡ በአካባቢው የሚዘዋወሩ ከለዳዊያንም ከዚያ መሰውያ፣ ከአገልጋዩ ከአብርሃም ሕይወት ስለ እግዚአብሔር አወቁ፡፡ የመስዋዕት ማቅረብን አስፈላጊነት ተማሩ፡፡EDA 208.3

  ታማኝ የሆነ መምህር ሕይወት ካገኘ የእግዚአብሔር ቃል የሚሰጠው ትምህርት ዛሬም ከያኔው በምንም የሚያንስ አይደለም፡፡EDA 209.1

  ሌሎች ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተማሩትን ወይም የተማሩትን ማወቅ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ እያንዳንዱ ሰው ራሱን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቦ መናዘዝ እና ሁሉም ያን እውነት የሆነውን መማር አለበት፡፡ ነገር ግን ጥናቱ ገቢራዊ ይሆን ዘንድ የተማሪው ፍላጐት እግዚአብሔር የሚለውን የሚያዳምጥ መሆን አለበት፡፡ በተለይም በደረጃ፣ በሥልጠና በአስተሳሰብ ልማድ በሰፊው የሚለያዩ ልጆችንና ወጣቶችን በሚያስተምር ሰው ዘንድ ይህ ሊተኮርበት የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ ልጆችን መጽሐፍ ቅዱስ ስናስተምር የአእምሮአቸውን ዝንባሌ በማየት፤ ፍላጐታቸው ያተኮረባቸውን ነገሮች በመረዳት ብዙ ልንጠቀም እንችላለን፡፡ ከተለያዩ ዝንባሌዎቻችን ጋር የፈጠረን አምላክ በቃሉ ውስጥ ለእያንዳንዳችን አንድ አንድ ነገር አስቀምጦልናል፡፡ ተማሪዎቹ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ትምህርቶች ከራሳቸው ሕይወት ጋር የተያያዙ መሆናቸውን እያዩት ሲሄዱ እንደ አንድ አማካሪ አድርገው እንዲመለከቱት አድርጋችሁ አስተምሯቸው፡፡EDA 209.2

  አስገራሚ የሆነውን ውበቱንም እንዲያደንቁት እርዷቸው፡፡ እውነተኛ ፋይዳ የሌላቸው፣ በስሜት የሚያስፈነድቁ፣ ጤናማ ያልሆኑ በርካታ መፃህፍት ከሥነ ጽሁፍ ጠቀሜታቸው አንፃር ብቻ ታይተው መነበብ እንዳለባቸው ተደርጐ ይጠቀሳሉ ወይም ቢያንስ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሥራ ላይ ውለዋል፡፡ ታዲያ ልጆቻችን ከዚያ ንፁህ ከሆነው የእግዚአብሔር ቃል ፏፏቴ በነፃ መጠጣት ሲችሉ ከተበከሉ ምንጮች እንዲጠጡ የምናደርገው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉነት፤ ብርታት ጥልቀት ያለው የማያልቅ ትርጉምን የያዘ ነው፡፡ ልጆችና ወጣቶች በውስጡ ያሉትን የሐሳብና የመግለጫ መዝገቦችን ይፈልጓቸው ዘንድ አበረታቷቸው፡፡EDA 210.1

  የእነዚህን ውድና ክቡር ነገሮች ውበት አእምሮአቸውን እየሳበው እየማረከው ሲሄድ የሚያለሰልስና የሚገራ መንፈስ ልባቸውን ይነካል፡፡ ራሱን ወደ ገለጠላቸው አምላክ ወደ አርሱ ይበልጥ ይሳባሉ፡፡ ስለ እርሱ ሥራዎችና መንገዶች የማወቅ ፍላጐት የሌላቸው ጥቂቶች አሉ፡፡EDA 210.2

  የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ የሆነ ሁሉ ትምህርቱን በተማሪነት መንፈስ ሊከታተል እንደሚገባው መማር አለበት፡፡ የእኛን ሐሳብ በእርግጠኝነት እንዲደግፍ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ምን እንደሚል ለማወቅ ከገጽ ገጽ ማፈላለግ አለብን፡፡EDA 210.3

  እውነተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት ሊገኝ የሚችለው ቃሉ ራሱ በርሱ በኩል በተሰጠው በዚያ መንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው፡፡ እናም ይኸንን ዕውቀት ለማግኘት በእርሱ መኖር አለበት፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የሚያዝዘውን ነገር መታዘዝ አለብን፡፡ የተገባልንን ቃል ሁሉም ልንጠይቀው እንችላለን፡፡ ከእርሱ ጋር በርሱ ኃይል የተገጣጠመው ሕይወት ልንኖርበት የሚገባን ሕይወት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ዓይነት ሲያዝ በሚገባ ሊጠና ይችላል፡፡EDA 210.4

  በእየቀኑ በሚደረግ ጥናት ውስጥ ቁጥር በቁጥር በቃል የመያዝ ዘዴ ዘወትር እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ተማሪው አንድ ቁጥር ወስዶ እግዚአብሔር በዚያች ቁጥር ውስጥ ለእርሱ ያስቀመጠለት ምን እንደሆነ አረጋግጦ በማሰብ ያተኩርበት፡፡ ከዚህ በኋላ ቁጥሩ ከራሱ ጋር እስከሚዋሐድና የራሱ እስከሚሆን ድረስ በዚያ ሐሳብ ላይ አእምሮውን ያሳርፍበት ያለ አንዳች ዓላማ ትምህርታዊ ፍሬ የሌለው ብዙ ምዕራፎችን ከማንበብ ይልቅ ጠቀሜታው ግልጽ እስከሚሆን ድረስ አንድ ገጽ አንብቦ ማጥናት የበለጠ ዋጋ አለው፡፡EDA 211.1

  ለሕሊና ብቃት ማነስና የሞራል ድክመት ዋነኛው ምክንያት ዋጋ ባለው ዓላማ ላይ አለማተኮር ነው፡፡ ስነጽሑፎችን በብዛት በማሰራጨታችን እንኩራራ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የመጽሐፍት ብዛት ብቻውን ጐጂ ያልሆኑ መጽሐፍት ጭምር ቢሆኑ ለክፉው ነገር የሚመቹ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ያለማቋረጥ ከማተሚያ ቤቶች እጅግ በብዙ ጥራዝ የሚወጡ መፃህፍትን ከንባብ ልማድ በጥድፊያ ማንበብን ልማድ ያደረጉ ላይ ላዩን የሚጋልቡ ወጣቶችና አረጋዊያን አእምሮ የጠነከረና የተያያዘ አስተሳሰባቸው ኃይል ይቀንስና መጽሐፍት ጥንት በግብጽ ምድር ላይ እንደ ፈሉ እንቁራሪቶች አገሩን ቢያለብሱትም በዘልማድ የታወቁ ዝም ብለው የበዙ ነገሮች ሳይሆኑ መንፈስን የሚያደክሙ፣ ያልነፁና ክብርን የሚቀንሱም ናቸው፡፡ ውጤታቸውም አእምሮአችን ማዞርና ማበላሸት ብቻ ሳይሆን ነፍስንም የሚበክልና የሚያጠፋ ነው፡፡ ፈዛዛና ዓላማ የለሽ የሆነ አእምሮና ልብ በቀላል ፈተና ክፉ ወጥመድ ውስጥ ይወድቃል፡፡ ፈንገስ የተባለው ደረመን የቆዳ በሽታ ሥሩን የሚሰደው በሌላ በሽታ በተበከለና ሕይወት በሌለው አካል ላይ ነው፡፡ የቦዘነ አእምሮ የሰይጣን መሥሪያ ቤት ነው፡፡ አእምሮአችሁ እጅግ ከፍተኛና ቅዱስ ወደ ሆኑ ሐሳቦች እንዲያመራ አድርጉት ሕይወት ክቡር አላማና የሚማርክ ሐሳብ እንዲኖረው ይሁን በዚህ ጊዜ ክፉው የእግር መርገጫ ቦታ ያጣል፡፡EDA 211.2

  ከዚያ በኋላ ወጣቶች የእግዚአብሔርን ቃል በቅርበት ማጥናትን ይማሩ፡፡ ወደነፍሳቸው ውስጥ ሲቀበሉት ለፈተና እጅግ ትልቅ መከላከያ ጋሻ ይሆንላቸዋል፡፡ «ቃልህ» ይላል ባለመዝሙሩ ዳዊት «በፊትህ ኃጢአትን እንዳልሠራ ታደርገኝ ዘንድ በልቤ ውስጥ ደበቅኋት» «ከከንፈርህ በምትወጣው ቃልህ ከአጥፊው መንገድ ጠብቃኛለች፡፡» መዝ 119፡11 ፣ 17፡4፡፡ EDA 212.1

  መጽሐፍ ቅድስ ራሱን በራሱ ገላጭ ነው፡፡ አንዱ ከሌላው ጋር የሚነፃፀር ነው፡፡ ተማሪው ቃሉን በጥቅሉ እንዳለ መመልከትና አንዱ ክፍል ከሌላው ጋር እንዴት እንደሚገናኝ መማር አለበት፡፡ ታላቁንና ዋናውን አስኳል የሆነ ሐሳብ እግዚአብሔር ለዚች ዓለም በቅድሚያ ያሰበላት ዓላማ ምን እንደ ነበረ፤ የታላቁ ተጋድሎ አነሳስ እና የመታደግንም ሥራ ጥሩ አድርጐ ዕውቀት ሊጨብጥበት ይገባዋል፡፡ የበላይነትን ለመያዝ በሚደረግ ፉክክር፤ የሁለቱን መሠረተ ሐሳቦች ባሕሪይ ማስተዋልና በታሪክና በትንቢት ውስጥ የተመዘገበውን አሠራራቸውን ከታላቁ ፍፃሜ ጋር ያላቸውን ግንኙነት መስመር በመስመር መከታተልን መማር አለበት፡፡ እነኝህ ተጋድሎዎች በሰው ልጅ ኑሮ ውስጥ በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ እንደሚገቡ ማየት አለበት፡፡ በእያንዳንዷ የሕይወት ገቢራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እርሱ ራሱ ከተቃራኒዎቹ ሐሳቦች በአንደኛው እንዴት ራሱን እንደሚገልጽና ፈለገም አልፈለገም ከትግሉ በአንደኛው ወገን ውስጥ መሆኑን ራሱ አሁኑኑ ይወስናል፡፡EDA 212.2

  የመጽሐቅ ቅዱስ የእያንዳንዱ ክፍል በእግዚአብሔር መንፈስ የተሰጠና ጠቃሚም ነው፡፡ ብሉይ ኪዳን ከሐዲስ ያላነሰ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ብሉይ ኪዳንን በምናጠናበት ጊዜ ግዴለሽ የሆነው አንባቢ ምድረበዳውን ብቻ ሲመለከት እኛ ሕያው የሆኑ ምንጮች የሚፈልቁበትን እናገኛለን፡፡EDA 213.1

  የራዕይ መጽሐፍ ከዳንኤል መጽሐፍ ጋር ሲገናኝ ልዩ ትኩረትን ይሻል፡፡ እያንዳንዱ እግዚአብሔርን የሚፈራ አንባቢ ሁሉ ወንጌልን እንዴት በጣም ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስተዋልና ለማስተማር ይቻል ዘንድ መድህናችን በአካል ወደዚህ ዓለም በመምጣት ለአገልጋዩ ለዮሐንስ «ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር በየሱስ ክርስቶስ የሰጠው በእርሱም የተገለጠው» ራዕ ዮሐ 1፡1፡፡ እንደ ገለጠለት ያመዛዝን፡፡ በራዕይ ዮሐንስ ውስጥ በተገለጡ ልዩ ልዩ ምስጢራዊ ምስሎች ምክንያት ማንም ተስፋ ሊቆርጥ አይገባውም፡፡ «ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጐድለው ሳይነቅፍና በልግሥና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን» ያዕ 1፡5EDA 213.2

  «ዘመኑ ቀርቧልና የሚያነበው የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተፃፈውን ቃል የሚጠብቁ ብፁአን ናቸው፡፡» ራዕ ዮሐ 1፡3፡፡EDA 213.3

  ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ፍቅር ሲያድርበትና ሲነሳሳ፤ ተማሪውም የትምህርቱ መስክ ምን ያክል ሰፊ እንደሆነ በውስጡ ያሉት መዝገቦች ምን ያክል ውድና ክቡር መሆናቸውን ሲገነዘብ በሚያጋጥመው ዕድል ሁሉ ራሱን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ለማስተዋወቅ ይፈልጋል፡፡ ጥናቱም በሰዓትና በቦታ የተገደበ አይደለም፡፡ ይህ ያላቋረጠ ጥናትም በቅዱስ መጽሐፍት ላይ ፍቅር እንዲያድርብን ለማድረግ አይነተኛው መንገድ ነው፡፡ ተማሪው መጽሐፍ ቅዱስ ከእጁ እንዳይለየው ይሁን፡፡ ዕድሉ ባጋጠመ ሰዓት ሁሉ አንድ ጥቅስ አንብብና በርሱ ላይ ሐሳብህን አሰባስበህ በጽሞና ፀልይ፡፡ በመንገድም እየተጓዝህ እያለህም ሆነ ወይም ባቡር ስትጠብቅ ወይንም ከሰው ጋር ቀጠሮ ኖሮህ በምትጠባበቅበት ሰህት ከእውነት ግምጃ ቤት ክቡር ሐሳቦችን የማፈላለግ ልምድህን አሻሽል፡፡EDA 213.4

  ታላላቅ የነፍስ አነቃቂ ኃይሎች እምነት ፤ ተስፋና ፍቅር ናቸው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትም የሚገፋፋን ወደ እነሱ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ውጫዊ ውበት ሐሳባዊና ገላጭ አሠራር ብቻ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እውነተኛ መዝገቦች የቅድስና ውበት መግለጫዎች ናቸው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ተጓዙ ሰዎች በተፃፈው ታሪክ ውስጥ የርሱን አሠራር ጭላንጭል ልናገኝ እንችላለን፡፡ «ፍፁም ተወዳጅ» በሆነው እርሱን እናያለን፡፡ የመሬትና የሰማይ ውበት ሁሉ እንደ ጭጋግ ብቻ ነው፡፡ «እነሆ ከዚህ ወደ ላይ በሄድሁ ጊዜ …. ወደ እኔ እወስዳችሁ ዘንድ» ዮሐ 12፡32፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ቤዛ የሆነለትን መድህን በያዘ ጊዜ የእምነት መሠረታዊ ኃይል መወድስና ፍቅር በነፍሱ ውስጥ ይነሳሳል፡፡ ክርስቶስን ስንመለከት ትኩረታችን አይነቃነቅም ተመልካቹም በሚያከብረውና በሚሰግድለት ምሳሌ እየተቀረፀ ያድጋል፡፡ የሐዋሪያው ጳውሎስ ቃላትም የነፍስ ቋንቋ ይሆናል፡፡ «በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ እየሱስ ስለ ጌታየ እውቀት …. ተጐዳሁ ክርስቶስን አገኝ ዘንድ በክርስቶስ በማመን…. በእርሱ አገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጉድፍ ቆጠርኩት፡፡» ፊሊ 3፡8-10፡፡EDA 214.1

  የሰማዩ ሰላምና ደስታ ምንጮች በመንፈስ ቃል አማካይነት ወደ ልብ ሲገቡ ለደረሱበት ሁሉ ታላቅ በረከት የሚሆን እጅግ ትልቅ ወንዝ ይሆናል፡፡ የዛሬ ወጣቶች፤ መጽሐፍ ቅዱስን በእጃቸው ይዘው በማደግ ላይ ያሉ ወጣቶች፤ ሕይወት ሰጪ የሆነውን ኃይል የሚቀበሉና የሚያስተላልፉ ይሁኑ፡፡ ታዲያ ከዚያ በኋላማ እንዴት ዓይነት የበረከት ምንጮች በዓለም ላይ በወረዱ ነበር! የመፈወስና የማጽናናት ኃይል ያለው፤ ልናስተውለው የምንችለውም ጥቂቱን ብቻ የሆነ የሕይወት ውሃዎች ፏፏቴ «ወደ ዘለዓለም ሕይወት ሽቅብ የሚፈልቁ፡፡» እንሆናለን፡፡EDA 214.2

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents