የሥቃይ ውስጥ ሥነ ሥርዓት መማር
በዚህ አለም ላይ ለእግዚአብሔር ወይም ለሰው እውነተኛ አገልግሎት የሚያበረክቱ ሁሉ በሀዘን ትምህርት ቤት ውስጥ የዝግጅት ስልጠና ይቀበላሉ፡፡ ከባድ እምነት በተጣለባቸው መጠን፣ አገልግሎቱም ከፍ ባለ መጠን ፈተናው እየቀረበ ሥነ-ሥርዓቱም እየጠበቀ ይሄዳል፡፡EDA 167.2
የዮሴፍንና የሙሴን ሕይወት ተመልከቱ፡፡ የዳንኤልንና የዳዊትንም፡፡ የዳዊትን የልጅነት ታሪክ ከሰለሞን ታሪክ ጋር አመዛዘኑት ውጤቶቻቸውንም አንፃጹሩ፡፡EDA 167.3
ዳዊት በወጣትነቱ ከሳውል ጋር በጣም የጠበቀ ወዳጅነት ነበራቸው፡፡ በአደባባይ መቆየቱ ደግሞ ከንጉሡ የቤት ውስጥ ጉዳዮች ጋር በነበረው ግንኙነትም ጥንቃቄ ማድረግን ሀዘንንና ድብልቅልቅ ያሉ ሁኔታዎችን በንጉሣዊ ክብርና ደማቅ የሕዝብ ሰልፍ ውስጥ ተደብቆ ማስተዋልን ሰጠው፡፡ ለነፍስ ሰላምን ለመስጠት የሰው ክብር ምን ያክል እጅግ አነስተኛ እንደሆነ ተመለከተ፡፡ እናም ከንጉሡ አደባባይ ወደ በጐቹና መንጋው በረት ሲመለስ እረፍትና ደስታ አየተሰማው ነበር፡፡EDA 167.4
በሳውል ቅናት ተሳድዶ በሽሽት ወደ በረሃ ሲገባ ዳዊት ከሰው እርዳታ ተለየ፡፡ ተነጥሎም ሳለ ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር ቀረበ፡፡ ተነጥሎም ሳለ ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር ቀረበ፡፡ አስተማማኝ ያልነበረውና ረፍት የለሹ የበረሃው ሕይወት ያላቋረጠው የአደጋ ስጋት ዘወትር ሽሽት የሚያስፈልገው ኑሮ በዚያ ስፍራ ለእሱ የተሰበሰቡ ሰዎች ጠባይ «የተጨነቀም ሁሉ ብድርም ያለበት ሁሉ የተከፋም ሁሉ ወደ አርሱ ተከማቸ፡፡» 1ኛ ሣሙ 22፡2 ሁሉም እጅግ አስፈላጊ የነበረውን ጥብቅ ሥርዓት ፈለጉ፡፡ እነዚህ የሕይወት ገጠመኞች የሰዎችን አያያዝ ዘዴ ለተጨቆኑ ማዘንን፣ ክፉውን የመጥላትን ኃይል አነሳሱ አሳደጉም፡፡ በእነኛ የአደጋና የጥበቃ ዘመናት ዳዊት በእግዚአብሔር ዘንድ ምቾትን ድጋፍና ሕይወቱን መልሶ ማግኘትን ተማረ፡፡ በሀዘንና በሥቃይ ትምህርት ቤት ውስጥ ባገኘው ስልጠና ነበር ዳዊት ታላቅ ታሪክ የሠራው፡፡ ምንም እንኳን በኋላ በትልቅ ኃጢአት ቢያበላሸውም «ለሕዝቡ ሁሉ ፍርድና ጽድቅን አደረገላቸው፡፡» 2ኛ ሣሙ 8፡15፡፡EDA 168.1
ዳዊት ቀደም ባሉት ዘመኖቹ የነበረውን ሥነ-ሥርዓት ሰለሞን በዚያ እድሜ አላገኘውም ነበር፡፡ በአካባቢው በነበሩ ሁኔታዎች በባህሪ እና በሕይወት ከሌሎች በላይ የበለጠ የሚወደድ የነበረ ይመስላል፡፡ በወጣትነቱ ክቡር በጐልማሳነቱ የተከበረ በአምላኩም የተወደደ የነበረው ሰለሞን ለብልጽግናና ለክብር ከፍተኛ የተስፋ ቃል በተሰጠበት የግዛት ዘመን ውስጥ ገባ፡፡ ብዙ ሕዝቦች በእሱ እውቀትና እግዚአብሔር በሰጠው ጥበብ በጣም ተደነቁ፡፡ ነገር ግን በብልጽግና መኩራራት ከእግዚአብሔር መለየትን አመጣ፡፡ ከመለኮት ግንኙነት ያገኝ የነበረውን ደስታ ትቶ እርካታን ከስሜቶቹ ለማግኘት በመፈለግ ፊቱን አዞረ፡፡ ስለዚህ ሁኔታ ራሱ እንዲህ ይላል፡፡EDA 168.2
«ትልቅ ሥራን ሠራሁ ቤቶችንም አደረግሁ፤ ወይንም ተከልሁ፡፡ አትክልትና ገነትን አደረግሁ፣ ልዩ ልዩ ፍሬ ያለባቸውንም ዛፎች ተከልኩባቸው፡፡ ...ወንዶችና ሴት ባሪያዎችን ገዛሁ፡፡... ከእኔ አስቀድመው በእየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ብዙ ከብቶችና መንጋዎች ነበሩን፡፡ ብርና ወርቅን የከበረውን የነገሥታትና የአውራጆችን መዝገብ ሰበሰብሁ አዝማሪዎችንና አረሆዎችን የሰዎች ልጆችንም ተድላ እጅግ የበዙ ሴቶችንም አከማቸሁ፡፡ ታላቅም ሆንሁ፣ ከእኔም አስቀድመው በእየሩሳሌመ ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ከበርሁ...ዐይኖቼም ከፈለግሁት ሁሉ አልከለክልኋቸውም ነበረና፡... ልቤም ከደስታ ሁሉ አላራቅሁትም፡፡ ልቤም በድካሜ ሁሉ ደስ ይለው ነበር፡፡ እጄ የሰራቻትን ሥራየን ሁሉ የደከምሁበትንም ድካሜን ተመለከትሁ እነሆ ሁሉ ከንቱ ነፋስንም አንደመከተል ነበረ፡፡ ከፀሐይ በታችም ትርፍ አልነበረም፡፡ እኔም ጥበብን እብደትንና ስንፍናን አይ ዘንድ ተመለከትሁ በፊቴ ከተደረገው በቀር ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ያደርጋል?...ከፀሐይ በታች የተሠራው ሥራ ሁሉ ከብዶኛልና ሕይወትን ጠላሁ፡፡» መክ 2፡4-12‚17‚18EDA 169.1
በራሱ መራራ ሕይወት ሰለሞን የምድር ደስታን የሚፈልግ ሕይወት ምን ያክል ባዶ እንደሆነ ተማረ ለአረማዊያን አማልክት መሰዊያ አቆመ፡፡ ለነፍስ ረፍት የሚሰጡት ተስፋ ምን ያክል ከንቱ እንደሆነ ለመማር ሲል ብቻ አደረገው፡፡EDA 169.2
ወደ ኋለኛው ዘመኖቹ ሰለሞን ከሚያፈስስ ምድራዊ ገንዳ ተመልሶ እንደተጨነቀና እንደ ተጠማ ከሕይወት ፏፏቴ ለመጠጣት ፊቱን አዞረ፡፡ የባከኑ ዘመኖቹ ታሪክ ከማስጠንቀቂያ ትምህርቶቹ ጋር በመንፈስ ቅዱስ ተነሳስቶ ለኋለኛው ትውልዶች ይጠቅሙ ዘንድ ፃፋቸው፡፡ ስለዚህም ምንም እንኳ እሱ የዘራው ዘር ክፉ ፍሬ ወይም መከራው በራሱ ሕዝብ ቢሰበስብም የሰለሞን የሕይወት ሥራ ሙሉ ለሙሉ ጠፍቶ አልቀረም፡፡ ለእሱ ለመጨረሻ የስቃይ ሥነሥረዓት ሥራዋን ፈፀመች፡፡EDA 169.3
መሰቃየት ለሌሎች የሰጠውን ትምህርት ሰለሞን በወጣትነቱ ተምሮ ቢሆን ኖሮ ከእንዲህ ዓይነት ንጋት ጋር ሕይወቱ ምን ያክል ግርማ ሞገስ የተሞላ በሆነ ነበር፡፡EDA 170.1