Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  መግቢያ

  እንደዚህ በአዲስ አሠራር እንደተዘጋጀው፤ እጅግ ትምህርታዊ የሆነ፣ የዘመናትን የለውጥ ፈተናዎችን የተቋቋመ፣ በሰፊው ተነባቢ ለመሆን የቻለ፣ እንደዚህ ዓይነት መጽሐፍ የሚገኘው ከስንት አንድ ነው፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተቀመጡ መሠረተ ሃሳቦች በብዙ አሥርቶችና በብዙ ሺህዎች ለሚቆጠሩ ወላጆችና መምህራን ለብዙ አሥርተ ዓመታት የእጅ ማስታወሻ አይነት ሆኖላቸው ቆይቷል፡፡EDA 3.1

  አሁን ደግሞ አንዳችም የቃላትና የገጾች ለውጥ እንኳ ሳይደረግበት ቀደም ሲል በነበረው ሰፊ ስርጭትና ተነባቢነት ላይ ይበልጥ ለመጨመር በአንድ ክርስቲያን ቤት ውስጥ መጽሐፍት መደርደሪያው ላይ መገኘት ካለባቸው መጽሐፍት መካከል አንዱ ሊሆን በሚችል መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡EDA 3.2

  እያንዳንዱ ግለሰብ በተግባር የሚታዩ የሕይወት እውነታዎችን፣ በሕይወት ውስጥ የሚገኙ እድሎችን ፣ የሚኖሩ ኃላፊነቶችን ሽንፈቶችንና ስኬታማነቶችን መጋፈጥ አለበት፡፡ እነዚህን ገጠመኞች እንዴት ሊጋፈጣቸው እንደሚችልና የሁኔታዎቹ አሸናፊ ወይም ተሸናፊ የመሆን እድሉ የሚመሠረተው በአመዛኙ ሰውየው ራሱ ከእነዚህ የትምህርት ደረጃዎች ጋር ለመስተካከል ባለው ዝግጅት መጠን ነው፡፡EDA 3.3

  እውነተኛ ትምህርት ለዚህ ዓለምና ለወደፊቱ ዘለዓለማዊ ሕይወት ሙሉና በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚጠቅም፣ የሁሉም ችሎታዎች የተቀነባበረ እድገት መሆኑ በጥሩ ሁኔታ ተገልጿል፡፡ የአእምሮ መዳበር፣ የኑሮ ዘይቤ መሠረት የሚጣለውና ባሕሪይም የሚቀርፀው፣ በልጅነት ጊዜ በቤት ውስጥና በመደበኛው የትምህርት ሥራ ነው፡፡EDA 3.4

  የዚህ መጽሐፍ ደራሲ እውነተኛ ትምህርት ከምን ከምን ተውጣጥቶ የተቀረፀ እንደሆነ በሰፊ መልኩ ሊጨበጥ የሚችልበትን መንገድ በቀጥታ ታመለክታለች፡፡ በአእምሮ ውስጥ ያሉ ችሎታዎች ሁሉ በሚገባ ሊዳብሩ የሚችሉበት የትምህርት ዓይነት በግልጽ ተቀምጧል፡፡ እጆችም ጠቃሚ በሆኑ የሙያ መስኮች ሊሰለጥኑ የሚችሉበት ትምህርት ትኩረት ተሰጥቶበት ተቀምጧል፡፡ ይህ ትምህርት የጥበብና የማስተዋል ሁሉ ምንጭ እግዚአብሔር መሆኑን አምኖ የተቀበለና የመረጠ የትምህርት ዓይነት ነው፡፡EDA 4.1

  የደራሲዋ ቀስቃሽ የሆነ ታላቅ ዓላማ በሥነ-ትምህርትም ላይ የፃፈችው እጅግ ሰፊ ጠቃሚ ትምህርት ልጆች ገና ከጧቱ የልጅነት ሕይወታቸው ጀምሮ ጥሩ ዜጐች በመሆን ቦታቸውን ለመያዝ እንዲዘጋጁና በተግባር ለሚታየው ሕይወት በጥሩ ሁኔታ ተሰናድተው በሚገባ የዳበረ አካል ያላቸው ፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ፤ ያልተበላሸ ባሕሪይ ያላቸውና ለመሠረታዊ ሐሳቦች ተገዢ የሆኑ ፤ ልብ ያላቸው ይሆኑ ዘንድ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ወጣቶችን በቤትና በትምህርት ቤት ውስጥ የመምራት ኃላፊነት ያለባቸው ሁሉ ሊያስተውሏቸው የሚገቡ መሠረታዊ ሐሳቦች የሞሉበት፤ በዚህ ዘርፍም ከተፃፉ ሌሎች ተመሳሳይ መጽሐፎች ሁሉ እጅግ የላቀው ሥራ ነው፡፡EDA 4.2

  የእነዚህ ገጾች ፀሐፊ የወጣት ወንዶችና ሴቶች የቅርብ ባልንጀራ የነበረች ናት፡፡ በብዙ ዓመታት ከትምህርት ተቋሞች ጋር የቀረበ ግንኙነት የነበራት ስትሆነ ወጣቶች ለዘላቂ የሕይወት ሥራዎቻቸው በሚያደርጉት ዝግጅት ከሚያጋጥሟቸው ችግሮች ጋር በሚገባ የተዋወቀች ነበረች፡፡ ከሁሉም በላይ በተለምዶ ከሚታወቀው በላይ እጅግ የላቀ የጽህፈትና የመናገር ዕውቀት የተሰጣት ነበረች፡፡EDA 4.3

  በታላላቅ መሪ መሠረታዊ ሐሳቦች የተሞላ እንደመሆኑ፤ ይህ መጽሐፍ ወደ ዝርዝር የሥርዓተ ትምህርት አዘገጃጀት ወይም ልዩ ወደ ሆነ የትምህርት አሰጣጥ ሥርዓት አቀራረጽ ውስጥ ሳይገባ በመላው ዓለም ተወዳጅ ለመሆን በቅቷል፡፡ ግንባር ቀደም ታዋቂ በሆኑ የሌሎች አህጉሮች ቋንቋዎችም ታትሞ ወጥቷል፡፡ በአሜሪካ አገር ታትሞ የወጣው ይህ አዲስ እትም የባህሪይ ሥነ-ትምህርትን ታላላቅ መሠረታዊ ሐሳቦች በስፋት ያዳርስ ዘንድ ትልቅ ተስፋ ጥለውበታል፡፡EDA 5.1

  አሳታሚዎቹና የኤለን ጂ-ኋይትEDA 5.2

  ጽሑፎች አደራ ጠባቂ ድርጅትEDA 5.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents