Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 31—የሕይወት ተግባር

  «ይኸንን እፈጽማለሁ፡፡»EDA 295.1

  በማንኛውም የሥራ መሥመር የሚገኝ ውጤት አንድ የተወሰነ ዓላማ ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡ በሕይወት ውስጥ በእውነተኛ የተሳካለት ሰው የልፋቱ ዋጋ የሚሆነውን ነገር በማየት በጽናት አተኩሮ መጠበቅ አለበት፡፡ ይህን የመሰለ ዓላማ በዛሬዎቹ ወጣቶች ፊት እነሆ ቀርቦላቸዋል፡፡ በዚህ ትውልድ ዘመን ወንጌልን ለዓለም የማዳረስ በሰማይ የተመረጠ ዓላማ ለማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር የሚቀርብለት እጅግ ክቡር የሆነው ዓላማ ነው፡፡ ክርስቶስ ልቡን ለነካው ለማንኛውም ሰው ሁሉ የሥራ መስክ ይከፍትለታል፡፡EDA 295.2

  ባጠገባችን ሆነው ለሚያድጉ ልጆች እግዚአብሔር ያሰበላቸውን ዓላማ የእኛ ውስን የሆነ የመመልከትና የማሰተዋል አቅም ሊገነዘበው ከሚችለው በላይ እጅግ ሰፊና እጅግ ከፍ ያለው ነው፡፡ ታማኝ መሆናቸውን አይቶ በጥንት ጊዜ ፍፁም ትሁት ከሆነው እጣቸው ጋር በዓለም ከፍተኛ ቦታ ላይ ለእርሱ ይመሰክሩ ዘንድ ጠርቷቸዋል ብዙ የዛሬ ወጣቶችም ዳንኤል በይሁዳዊ ቤቱ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃልና ሥራዎች እያጠና እንዳደገ ሁሉ እነርሱም እያደጉ ሲሄዱና የታማኝነትን አገልግሎት ሲማሩ ወደፊት በሕጋዊ ስብሰባዎች በፍርድ አዳራሾች ወይም በንጉሣዊያን አደባባዮች የነገሥታት ንጉሥ ለሆነው ምስክር በመሆን ይቆማሉ፡፡ ሰዎች ለሰፊ አገልግሎት ይጠራሉ፡፡ መላው ዓለም በወንጌል ክፍት ነው፡፡ ኢትዮጵያም እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች፡፡ ከጃፓን፣ ከቻይና፣ ከህንድ፣ በራሳችን አህጉር ውስጥም እንኳ እስካሁን የጨለመባቸው አገሮች በዚች ዓለማችን ከጫፍ እስከ ጫፍ ድረስ በኃጢአት የተመታ ልብ የእግዚአብሔር ፍቅር ያውቁ ዘንድ ጥሪው ይሰማል፡፡ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ወይም በክርስቶስ አማካይነት ስለተገለጠው የርሱ ፍቅር አንዳችም ሰምተው አያውቁም፡፡ ይኸንን እውቀት ማግኘት መብታቸው ነው፡፡ የመድኀናችንን ምህረት ለማግኘት ከእኛ ጋር እኩል ጥያቄ አላቸው፡፡ ለጩኸታቸው ምላሽ ልናካፍላቸው ከሚገባን ከልጆቻችን ጋር በእኛ ላይ ያንን እውቀት ባገኘን ሰዎች ላይ ኃላፊነት ወድቆብናል፡፡ በእያንዳንዱ ቤተሰብ ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ለእያንዳንዱ ወላጅና መምህር የወንጌል መብራት ያረፈበት እያንዳንዱ ልጅ ሁሉ ለእስራኤል ታሪክ ውስጥ እጅግ ወሳኝ በነበረው ወቅት ላይ ለነገሰችው ለንግሥት አስቴር የቀረበላት የቀውጢ ጊዜ ጥያቄ በዚህ የተቃወሰ ጊዜ ላይ ቀርቦላቸዋል፡፡EDA 295.3

  ወንጌልን በፍጥነት በማደናቀፍ ውጤት ይገኛል ብለው የሚያስቡ ከራሳቸውና ከዓለም ጋር ያለውን ግንኙነት ብቻ ስለሚያስቡ ነው፡፡ ጥቂቶች ወንጌል ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት ያስባሉ፡፡ በክርስቶስ መከራና ሰቆቃ ሰማይ በሙሉ አብሮ ተሰቃየ፡፡ ነገር ግን ያ መከራ እርሱ ሰው መሆኑ በተገለጠበት ጊዜ የተጀመረ ወይም በዚያ ጊዜ ያበቃም አልነበረም፡፡ ስለ ስቃዩ እኛ ላለን የደነዘዘ ስሜት ኃጢአት ገና ከጀመሪያው በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ስሜት የሚገልጽልን መስቀሉ ነው፡፡ ከትክክለኛው መንገድ ትንሽ እንኳ ፈቀቅ የሚል እያንዳንዱ እርምጃ እያንዳንዱ የጭካኔ ተግባር ከርሱ ከፍተኛ ሀሳብ ለመድረስ ባለመቻል የሚኖር እያንዳንዱ ሰብዓዊ ውድቀት ሁሉ ለርሱ መራራ ሀዘን ያመጣበታል፡፡ ከእግዚአብሔር የመለየት ትክክለኛ ውጤት የሆኑ አደጋዎች በእስራኤል ላይ በወረዱ ጊዜ አጠቃላይ በጠላቶቻቸው ሱገዙ ጭካኔና ሞት ሲደርስባቸው እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፡፡ «ነፍሱም ስለ እሰራኤል ጉስቁልና አዘነች፡፡» «በጭንቀታቸ ሁሉ እርሱ ተጨነቀ... በፍቅሩና በርህራሄውም ተበዣቸው» መሣ 16፡10 ኢሳ 63፡19EDA 296.1

  የርሱ መንፈስ «እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፡፡... መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናልና፡፡» «ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ መቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና፡፡» ሮሜ 8፡26፡22 ወሰን የሌለው አምላክ ልብም በርህራኄው ከእኛ ጋር ተሰቃየ፡፡ ዓለማችን እጅግ ሰፊ ቤት ነው፡፡ ሐሳቦቻችን እንኳ እንዲያርፉበት ለማድረግ የማያስደፍር የስቃይ ትዕይንት ያለበት ነው፡፡ እንደዚሁ እንዳለ ከተገነዘብነው ሸክሙ እጅግ አስጨናቂ ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ይህም ይሰማዋል፡፡ ኃጢአትንና ውጤቶቹን ለመደምሰስ እጅግ አድርጐ የሚወደውን ልጁን ሰጠ፡፡ እናም ይኸንን ስቃይም ወደ ፍፃሜ ለማምጣት ከርሱ ጋር በሚኖር ትብብር በውስጣችን ኃይል እንዲኖረን አደረገልን፡፡ «ለሕዝብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፡፡ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል፡፡» ማቴ 24፡14EDA 297.1

  «ወደ ዓለም ሁሉ ሄዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ሰበኩ፡፡» ማር 16፡5 ክርስቶስ ለተከታዮቹ የሰጠው ትዕዛዝ ነው፡፡ ማር 16፡5 ክርስቶስ ለተከታዮቹ የሰጠው ትዕዛዝ ነው፡፡ በቃሉ የተለምዶ አገባብ መሠረት ሁሉም ሰው ወንጌላዊ እንዲሆን ወይም የወንጌል መልዕክተኛ እንዲሆን አይደለም፡፡ ሁሉም ከርሱ ጋር «የደስታ የምሥራች» ለወገኖቻቸው የሚያዳርሱ ሠሪተኞች እንዲሆኑ ነው እንጂ፡፡ ለሁሉም፤ ታላቅ ታናሽ ሳይል ለተማረ ለመሐይም አረጋዊ ወይም ወጣት ሳይል ትዕዝዙ ተሰጥቷል፡፡EDA 297.2

  ከዚህ ትዕዛዝ አንፃር ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን የተከበረ ባህሪይ፤ በቃል ክርስቲያን የሆነ ሕይወት ፤ነገር ግን የእርሱን ራስን መስዋዕት የማድረግ ባህሪይ የሌለው ሕይወት እውነት የሆነው የርሱ ፍርድ «አላውቃችሁም» በማለት የሚፈርድበትን ሕይወት ልናስተምር እንችላለንን?EDA 297.3

  በሽህ የሚቆጠሩ ሰዎች ይኸንን እያደረጉ ነው፡፡ የወንጌልን ጥቅሞች ለልጆቻቸው ጠብቀው መስጠት ይፈልጋሉ፡፡ መንፈስን ግን ይክዳሉ፡፡ ይህ ደግሞ የማይሆን ነገር ነው፡፡ ከክርስቶስ ጋር በአገልግሎት መገናኘት የአባልነትን ጥቅም የሚቃወሙ በርሱ ክብር ከርሱ ጋር የመሳተፍ ብቃትን ከፍሎ የሚሰጠውን ሥልጠና ብቻ የሚቃወሙ ናቸው፡፡ በዚህ ሕይወት ውስጥ ለባህሪይ ብርታትና ክቡርነትን የሚሰጠውን ስልጠና ይክዳሉ፡፡ ብዙ አባትና እናቶች ልጆቻቸው የክርስቶስን መስቀል የማየት እድል እንዳያገኙ ይነፍጓቸዋል፡፡ በኋላ ግን ለእግዚአብሔርና ለሰው ልጅ ጠላት ለሆነው አሳልፈው እንደ ሰጧቸው የሚረዱት ብዙ ከዘገዩ በኋላ ነው፡፡ ለወደፊቱም ብቻ ሣይሆን ለአሁኑ ሕይወትም ጥፋት መፈፀማቸው ይሰማቸውና እጅግ ያዝናሉ፡፡ ፈተና አሸንፏቸዋልና ለዓለም እርግማንን አሳደጉ፡፡ ያንን ትምህርት ለሰጧቸውም መከራና ሐፍረትን አመጡባቸው፡፡EDA 298.1

  ለእግዚአብሔር አገልግሎት ዝግጅት ሲፈልጉም እንኳ በተሳሳቱ የትምህርት ዘዴዎች ምክንያት ከመንገድ ወጥተዋል፡፡ ሕይወት በጥቅሉ የትምህርት ዘመን የሥራ ዘመንና የዝግጅትና የውጤት ዘመን ተብሎ ለተወሰኑ ዘመኖች እንደተሠራ ተደርጐ ተወስዷል፡፡ የአገልግሎት ሕይወት እንዲኖራቸው ለማዘጋጀት ወጣቶች መጽሐፍትን በማጥናት እውቀት ያገኙ ዘንድ ትምህርት ቤት ይላካሉ፡፡ ከቀን ተቀን የሕይወት ኃላፊነቶች ተነጥለው በጥናት ብቻ ይዋጣሉ፡፡ እናም ዘወትር የሕይወትን ዓላማ ለማየት የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ይገባሉ፡፡ የልጅነታቸው ትኩስ ኃይልና ለተለየ ቅድስና ሕይወት ወኔአቸው ይሞታል፡፡ ብዙዎቹም የግል የራስ ወዳድነትን ምኞት ዓላማ ያደርጋሉ፡፡ ትምህርት ጨርሰው ተመርቀው ሲወጡ በሽህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ከሕይወት የተነጠሉ ሆነው ያገኙታል፡፡ ምክንያቱም ለብዙ ጊዜ ረቂቅና ንድፈ ሐሳብዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ብቻ ይታክቱ ነበርና አሁን አጠቃላይ ስብዕናቸው በዚህ እውን ሕይወት ለጦፈ ውድድር የተዘጋጁ አይደሉም፡፡ በሀሳባቸው ውስጥ ለነበረው ክቡር ሥራ ከመዋል ይልቅ ጉልበታቸው ሁሉ ለዕለት ጉርስ ኑሮአቸው ብቻ በመታገል ይሞላል፡፡ ከተደጋጋሚ ተስፋ መቁረጥ በኋላ ደህና ኑሮ እየኖሩ እያሉም እንኳ ብዙዎች ወደ አጠያያቂ ሕይወት ወይም የወንጀል ተግባር ይዞራል፡፡ ዓለም ማግኘት የነበረባትን አገልግሎት ተነጥቃለች፡፡ እግዚአብሔር ከፍ ሊያደርጋቸው ፤ በማነሳሳትም ክቡር ሊያደርጋቸው፣ የርሱ ወኪል በመሆን እንዱከበሩ ያስብላቸው የነበሩ ነፍሳትን ተነጥቆአል፡፡EDA 298.2

  ብዙ ወላጆች በትምህርት ጉዳይ ላይ በልጆቻቸው መካከል ልዩነት ይፈጥራሉ፡፡ በጣም ንቁና ቀልጣፋ ለሆነው ልጃቸው የሚጠቅመውም ነገር ሁሉ እንዲያገኝ አስፈላጊውን መስዋዕትነት በመክፈል የማያደርጉለት ነገር የለም፡፡ እነዚህ እድሎች ግን ለሌሎች አነስ ያለ ተስፋ ለሚጣልባቸው ልጆች ጨርሶም አይታሰቡላቸውም፡፡ ለሕይወት የተለመዱ ተግባራት አፈፃፀም ጥቂት ትምሀርት ብቻ እንደሚያስፈልግ ተደርጐ ይታያል፡፡EDA 299.1

  ነገር ግን በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ከሚገኙ መካከል እጅግ ከባድ የሆነ ኃላፊነት የሚወድቅባቸውን ለይቶ መምረጥ የሚችለው ማን ነው የሰው ልጅ ግምት በእንዲህ ዓይነት ጉዳዮች ላይ የተሳሳተው ስንት ጊዜ ነው ከእሴይ ልጆች መካከል ለእስራኤል ንጉሥ የሚሆነውን ልጅ መርጦ ለመቀባት ሲሄዱ ሳሙኤል ያጋጠመውን አስታውሱ፡፡ ሰባት መልከ መልካም ትልልቅ ልጆች በርሱ ፊት አለፉ፡፡ በመጀመሪያ የቀረበውን ልድ ሲመለከት፤ መልኩ ውብ ቁመናው የተሟላ ያማረ ነበረና ነበዩ «በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው» በማለት በአድናቆት ተናገረ፡፡ እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለ፡፡ «ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ... ሰው ፊትን ያያል እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል፡፡» 1ኛ ሣሙ 16፡6-7 ለሰባቱም የተሰጠው ቃል «እግዚአብሔር አልመረጠውም» የሚል ነበር፡፡ ዳዊት ከመንጋዎቹ መካከል እስከሚጠራ ድረስ ገብዩ ተልዕኮውን እንዲፈጽም አልተፈቀደለትም ነበር፡፡EDA 299.2

  ከታላላቅ ወንድማማቾች መካከል ሣሙኤል ሊመርጥ ያዘጋጅ እንጅ እግዚአብሔር ከእነርሱ መካከል የርሱን ሕዝብ ለመምራት የሚያስችለውን ብቃት የያዘ ሰው አላየም፡፡ ኩራት በራሱ ላይ ብቻ ያተኮረ በራሱ የሚተማመን እንዚህ ባህሪያት እነሱ በቀላሉ በቀጥታ ይሆናል ብለው ካሰቡት ሰው ወደጐን ተጥለው ነበረ ነገር ግን የወጣትነት ዕድሜውን ለቀላል አኗኗርና ለንጽህና የጠበቀ እናም በራሱ አመለካከት ራሱ ትንሽ ልጅ እንደ ሆነ አድርጐ ሲገምት ለመንግሥት ኃላፊነት እግዚአብሔር የሚያሰለጥነው ሰው ሆነ፡፡ ዛሬም እንዲሁ ወላጆቻቸው አይሆንም ብለው የሚያልፏቸው ተብለው ከሚጠበቁት በላይ የበለጠ ችሎታ እንዳላቸው እግዚአብሔር ይመለከታል፡፡EDA 300.1

  እናም በሕይወት ውስጥ የሚኖር ዕድሎችን በተመለከተ ይህ ታላቅ ይሆናል የ ትንሽ ይሆናል ብሎ መፍረድ የሚችለው ማነው በኑሮአቸው ዝግቀኛ ደረጃ ላይ ሆነው ለዓለም በረከት በባዶ እግራቸው እየተጓዙ ነገሥታት በቅሬታ ቢመለከቷቸውም ውጤት ላይ የደረሱ ስንት ናቸው?EDA 300.2

  ስለዚህ እያንዳንዱ ልጅ ለከፍተኛ አገልግሎት የሚጠቅም ትምህርት ይሰጠው፡፡ «ወይም ይህ ወይም ያ ማናቸውም እንደበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንዲሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ ፡፡» መዝ 11፡6EDA 300.3

  በሕይወታችን ውስጥ ቦታ ተመርጦ የሚመደብልን በችሎታዎቻችን መጠን ነው፡፡ ሁሉም ሰው እኩል ደረጃ ላይ አይደርስም ወይም አንዱን ሥራ ሁሉም ሰዎች በእኩል ብቃት አያከናውኑትም፡፡ እግዚአብሔር የሂሶጵን ድርሻ ከዝግባ፤ ወይም የበለስን ቁመት ከወይራ አይጠብቅም፡፡ ሁሉም የመለኮትና የሰብዓዊ ኃይል አንድ ላይ ተባብረው ያደረጉለትን እንክብካቤ ያክል ያድጋል፡፡EDA 300.4

  ብዙዎች ማደግ የሚገባቸውን ያክል አያድጉ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም በራሳቸው ውስጥ ያለውን ኃይል ሙሉ ለሙሉ አልተጠቀሙበት ይሆናል፡፡ መያዝ የሚገባቸውን ያክል የመለኮትን ኃይል አጥብቀው አልጨበጡምና፡፡ ብዙዎች እውነተኛ ስኬታማነትን ሊያገኙ ከሚችሉበት መስመር እየወጡ ነው፡፡ የበለጠ ከፍተኛ ክብር ወይም ከፍተኛ ደስታ ለማግኘት ሲሉ ያለ ችሎታዎቻቸውና መሥመራቸው ባልሆነ ሥራ ላይ ይሰማራሉ፡፡ አንዳንድ ሰው የተጠራበት ተሰጥኦው ለሌላ ዘርፍ ሆኖ ሳለ ሌላ ሙያ ውስጥ መግባት ይመኛል፡፡ ገበሬ፤ የእጅ ባለሙያ ፤ ወይም ነርስ ቢሆን ኖሮ የተሳካለት ሰው ይሆን የነበረው የማይሆን ቦታ ማለትም ሚኒስትር ጠበቃ ሐኪም ለመሆን ይሞክራል፡፡ እንደኝህ ሌሎች ደግሞ ለትልቅ ኃላፊነት ቦታ የሚመጥኑ ሆነው ኃይል ተግባራዊ ችሎታ እያላቸው ቁጥብነትን በመፈለግ ራሳቸውን ቀለል ባለ ቦታ ላይ ያስቀምጣሉ፡፡EDA 301.1

  እግዚአብሔር ለሕይወት ያመጣውን ዕቅድ በጥብቅ መከታተል ያስፈልገናል፡፡ ለእኛ ቀላልና ቅርብ በሆነልን ሥራ ውስጥ በጣም በከፍተኛ ደረጃ የተቻለንን ያክል ለመሥራት፣ መንገዳችንን ለእግዚአብሔር ለመስጠትና የርሱ ስጦታዎች ምልክት የሆኑትን ነገሮች ለመጠበቅ አንድን ሥራ ለመምረጥ እነዚህ ሕጐች አስተማማኝ መመሪያ ናቸው፡፡EDA 301.2

  ለእኛ ምሳሌ ለመሆን ከሰማይ የመጣልን ክርስቶስ ወደ ሠላሳ ዓመታት የሚሆን ጊዜ ያሳለፈው በተለመደ ሚካኒካዊ ተግባራት ላይ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ጊዜ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃልና ሥራዎች በማጥናትና በመርዳት የርሱ ስበት ሊደርስ እስከቻለበት ድረስ ባለው ቦታ ሁሉ ያሉትን በማስተማር ሥራ ላይ ነበር፡፡ ሕዝባዊ አገልግሎቱን ሲጀምር የታመሙትን መፈወስ፤ ያዘኑትን ማጽናናት ወንጌልን ለድሆች መስበክ ቀጠለ፡፡ የርሱ ተከታዮች ሁሉ ሥራቸው ይኸው ነበር፡፡EDA 301.3

  «_ _ _ እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ ነገር ግን ለእናንተ ታላቅ የሆነ በመካከላችሁ እንደ ታናሽ የሚገዛም እንደሚያገለግል ይሁን፡፡» ሉቃ 22፡26፣27 «እኔ በመካከላችሁ ነኝና፡፡»EDA 302.1

  ክርስቶስን ለማፍቀርና ለርሱ ታማኝ መሆን የእውነተኛ አገልግሎት ሁሉ ምንጭ ናቸው፡፡ በርሱ ፍቅር በተነካ ልብ ውስጥ ለርሱ የመሥራት ፍላጐት ይገኛል፡፡ ይህ ፍላጐት መበረታታትና በትክክል መመራት አለበት፡፡ በቤት ውስጥም ሆነ በጐረቤት ወይም በትምህርት ቤት ውስጥ የድሃው የተጨነቀ ችግረኞች የመሃይማን ወይም የእድለቢሶች መኖር እንደ መጥፎ አጋጣሚ ሳይሆን ለአገልግሎት የሚሆን ክቡር እድል እንደተሰጠ ሆኖ መታየት አለበት፡፡EDA 302.2

  በዚህ ሥራ ውስጥ በሌላው እንደሚደረገው ሁሉ በሥራው አማካይነት የሙያው እውቀት ይገኛል፡፡ ብቃት የሚገኘው በሕይወት የተለመዱ ጉዳዮችና ርዳታው ለሚያስፈልጋቸውና ለተሰቃዩ ሁሉ በማገልገል በሚገኝ ልምድ አማካይነት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ከፍተኛ የሚባለው ጥረትም ቢሆን ብዙ ጊዜ ዋጋ የለሽ እንዲያውም ጐጂም በሚሆንበት ጊዜም አለ፡፡ ሰዎች ዋና መማር የሚችሉት ውሃ ውስጥ እንጅ በመሬት ላይ አይደለም፡፡EDA 302.3

  ብዙ ጊዜ ቀለል ተደርጐ የሚታይ ክርስቶስ ለሚጠይቃቸው ነገሮች የተነሳሳ ወጣት ግልጽ መሆን ያለበት ሌላው ግዴታ ከቤተ ክርስቲያን ጋር በሚኖረው ግንኙነት ላይ ያለ ግዴታ ነው፡፡EDA 302.4

  በክርስቶስና በርሱ ቤተክርስቲያን መካከል በጣም የጠበቀ ግንኙነት አለ፡፡ እርሱ እንደ ሙሽራው እርሷም እንደ ሴቷ ሙሽራ ናቸው፡፡ እርሱ እንደ ራስ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ አንድ አካል ናቸው፡፡ ስለዚህ ከክርስቶስ ጋር መገናኘት ከቤተ ክርስቲያን ጋር መገናኘትን ይጠይቃል፡፡EDA 303.1

  ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት የተደራጀች ነች፡፡ ስለዚህ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ግንኙነት መፍጠር ከእርምጃዎች ሁሉ የሚቀድመው እርምጃ ነው፡፡ ለክርስቶስ ታማኝ ለመሆን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሥራዎች ታማኝ መሆንን ይጠይቃል፡፡ በአንድ ሰው የሥልጠና ጊዜ ውስጥ ዋናው ክፍል ይህ ነው፡፡ እናም በጌታ ሕይወት በተሞላና በተነቃቃ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቀጥታ ይህ እድል ወደ ሌላው ዓለም ያመራል፡፡EDA 303.2

  ወጣቱ ጠቃሚ የሆነ ተግባር ለማከናወን የሚችልበት ብዙ እድሎች አሉት፡፡ ለክርስቲያን አገልግሎት ራሳቸውን በቡድን በቡድን ያደራጁ፡፡ ሕብረቱም ጠቃሚና አበረታች ሆኖ ያገኙታል፡፡ ወላጆችና መምህራን ወጣቱን በሚመለከት ሥራ ላይ ፍላጐት በማሳየት ከሰፊ የሥራ ልምዳቸው በማካፈል ሊጠቅሟቸውና ጥረታቸው ሁሉ ለመልካም ነገር ውጤታማ እንዲሆን ሊረዷቸውም ይችላሉ፡፡EDA 303.3

  ርህራሄና ፍቅርን ማነቃቃት የሚችለው መተዋወቅ ነው፡፡ ርህራሄ ደግሞ ውጤት ላለው አገልግሎት ምንጭ ነው፡፡ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ በስቃይ ላይ ለሚገኙ «ከሀገራችን አካባቢ ውጪ» ለሚገኙ ሰዎች በልጆችና ወጣቶች ልቦና ውስጥ ርህራሄና የመስዋዕትነት መንፈስ እንዲያድርባቸው ለማድረግ መጀመሪያ ከነዚህ አካባቢዎችና ከራሳቸው ሕዝብ ጋር ይተዋወቁ፡፡ ይኸንን ጉዳይ በተመለከተ በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ብዙ ሊከናወን ይቻላል፡፡ በታወቁት በአሌክሳንደርና በናፖሊን ታሪክ ላይ አቀርቅረው ከመዋል ይልቅ እንደ ሐዋሪያው ጳውሎስና ማርቲን ሉተር እንደ ሞፋትና ሊቪንግ ስቶን እንደ ካሪ በመሳሰሉት የሰዎች የሕይወት ታሪክ ላይና አሁንም በየቀኑ በሚገለፀው የወንጌል አገልግሎት ታሪክ ላይ ያተኩሩ፡፡ በሕይወታቸው ላይ ምንም ስርፀት በሌላቸው የስም ዝርዝሮችና ንድፈ ሐሳቦች ሸክም እና ከመማሪያ ክፍሎች ውጪ በሚወጡበት ጊዜ በሚያስታውሱት ነገር አእምሮአቸውን ከማስጨነቅ ይልቅ በወንጌል ብርሃን ሁሉንም ሀገሮች ያጥኑ፡፡ እናም ከሕዝቦቹና ከፍላጐቶቻቸው ጋር ይተዋወቁ፡፡EDA 303.4

  በዚህ የወንጌል ሥራ መዝጊያ ሰዓት መሸፈን ያለበት ሰፊ መስክ አለ፡፡ እናም ከምን ጊዜውም በበለጠ ሥራው ከተራው ሕዝብ ውስጥ ረዳት የሆኑትን ሰዎች መመዝገብ ነው፡፡ ወጣቶችም ይሁኑ በዕድሜ ገፋ ያሉት ሰዎች ከመስክ ሥራ፣ ከወይን እርሻና ከዕቃ መሣሪያዎች ቤት (ወርክ ሾፕ) ላይ በጌታ ይጠሩና የርሱን መልዕክት እንዲያደርሱ ይላካሉ፡፡ ከእነኝህ ውስጥ ብዙዎቹ ለትምህርት የነበራቸው ዕድል ትንሽ ብቻ ነበር፡፡ ክርስቶስ ግን የርሱን ሐሳብ አሟልተው ለመፈፀም የሚያስችላቸው ብቃት በውስጣቸው እንዳለ ያያል፡፡ ልባቸውን ሙሉ ለሙሉ በሥራው ላይ ካሳረፉትና ትምህርቱን በመከታተል ከቀጠሉ ለእርሱ ሥራ የሚመጥኑ ያደርጋቸዋል፡፡EDA 304.1

  የዓለም ሥቃይና ጭንቅ ጥልቀቱ ምን ያክል እንደሆነ የሚያውቀው እርሱ በምን ዓይነት መንገድ ረፍት ሊገኝ እንደሚቻል ያውቃል፡፡ ነፍሳት በጨለማውስጥ በኃጢአት በሀዘንና በስቃይ አጐንብሰው ወድቀው እንዳሉ ያያል፡፡ ነገር ግን ያሏቸውን እድሎችም ይመለከታል፡፡ ሊደርሱ የሚችሉበትን የከፍተኛ ደረጃ ጣራ ሁሉ ያስተውላል፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች የተሰጣቸውን ምህረት ያለአግባብ ቢጠቀሙበትም ችሎታዎቻቸውንም በከንቱ ቢያባክኑአቸውም እግዚአብሔር የመምሰል ስብዕናን ቢያጡም በቤዘነት ስለታደጋቸው ፈጣሪ ከፍ ብሎ ይከበራል፡፡EDA 304.2

  ክርስቶስ እነዚህ ርዳታ እጅግ በሚያስፈልጋቸው በዚህ አስቸጋሪ በሆነ ዓለም ለመሐይማን በሚያዝኑና በዚህም ምክንያት ከመንገድ ውጪ በሆኑት ላይ የሥራ ሸክም ጥሎባቸዋል፡፡ ምንም እንኳ እጆቻቸው ሸካራና በሙያም ያልሰለጠነ ቢሆኑም ልባቸው በቀላሉ የሚለወጥ፤ በሀዘን የሚሰበር ሰዎችን ለመርዳት በቅርብ ይገኛል፡፡ በስቃይ ውስጥ ምህረት፤ ለሚያዩ፤ በጥፋት ውስጥም ማትረፍ ከሚችሉ ሰዎች ጋር ይሠራል፡፡ የዓለም ብርሃን በሚያርፍበት ጊዜ ጥቅም ከፈተና ሥርዓት ከምስቅልቅል ውስጥ ውጤትም ከውድቀት ይለያል፡፡ አደጋዎች እንደ በረከት ዋይታም እንደ ምህረት ሆነው ይታያሉ፡፡ ከተርታው ሕዝብ መካከል በሚወጡ ታታሪዎች ጌታቸው የመላውን የሰው ዘር ሀዘን እንደ ተካፈለ ሁሉ እነርሱም የወገኖቻቸውን ሐዘን የሚካፈሉ ሠራተኞች፤ ከእነርሱ ጋር ሲሠራ ሣለ በእምነት ያዩታል፡፡EDA 305.1

  «ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧል፤ የእግዚአብሔር ቀን ድምጽ ቀርቧል እጅግም ፈጥኗል» ሰፎ 1፡14 ዓለምም ማስጠንቀቂያ ያስፈልጋታል፡፡EDA 305.2

  እንዲህ ዓይነት የዝግጅት ጊዜ ስለሚኖራቸው በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች በእድሜ ጠና ያሉትም ጭምር ራሳቸውን ለዚህ ሥራ አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡ ብዙ ሰዎች ለታላቁ ሠራተኛ ጥሪ ምላሽ በመስጠት ልባቸውን አስረክበዋል፡፡ እያንዳንዱ የክርስቲያን መምህር ለእንዲህ ዓይነት ሠራተኞች ርህራሄና ትብብር ያድርግላቸው፡፡ በርሱ እንክብካቤ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ለደረጃ ዝግጅት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁሉ ማበረታቻ ድጋፍ ይስጣቸው፡፡ EDA 305.3

  ወጣቱ ታላቅ ጥቅም ሊያገኝ የሚችልበት ሌላ የሥራ መስመር የለም፡፡ በአገልግሎት ውስጥ የሚሳተፉ ሁሉ ለእግዚአብሔር ሥራ የሚያግዙ እጆች ናቸው፡፡ የመላዕክት ተባባሪ ረዳት ሠራተኞች ናቸው፡፡ እንዲያውም መላዕክት ሥራቸውን ለማከናወን የሚጠቀሙባቸው ሰብዓዊ ወኪሎች ናቸው፡፡ መላዕክት በራሳቸው ድምጽ ይናገራሉ፡፡ በእጆቻቸውም ይሠራሉ፡፡ ሰብዓዊ ሠራተኞች ደግሞ ከሰማይ ተወካዮች ጋር በመተባበር ከሚሰጡት ትምህርትና ከሚያካፍሉት ልምድ ይጠቀማሉ፡፡ እንደ አንድ የትምህርት አሰጣጥ ዘይቤ ይህንን የሚስተካከል «የዩቨርሲቲ ኮርስ» የትኛው ነው?EDA 306.1

  ወጣቶቻችን እንዲህ ዓይነት የሠራተኛ ሠራዊት ሲሆኑ በትክክል ከሰለጠኑ የተሰቀለው፤ ያረገውና በቅርቡ የሚመለሰው መድኅናችን መልዕክት ምንኛ በፍጥነት ለመላው ዓለም በተዳረሰ ነበር! ፍፃሜው እንዴት በፍጥነት በተከናወነ ነበር! የስቃይ የሐዘንና የኃጢአት ፍፃሜ! እዚህ በያዙት ቦታ በኃጢአትና በስቃይ እንደ ተበላሸ ልጆቻችን ርስታቸውን ይረከቡ ዘንድ «ፃድቃን ምድርን ይወርሳሉ፡፡ በርሷም ለዘላለም ይኖራሉ፡፡» «በርሷም ለሚቀመጡ ሰዎች በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል፡፡» «ከዚያ ወዲያም የልቅሶ ድምጽና የዋይታ ድምጽ አይሰማባትም፡፡» መዝ 37፡29 ኢሳ 33፡24 ምዕ 65፡19EDA 306.2

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents