Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 26—የማስተማሪያ ዘዴዎች

    «ማስተዋልን ለድሃ ለመስጠት
    ለወጣት ሰውም እውቀትንና መለየትን፡፡»
    EDA 256.1

    ትምህርት ለብዙ ዘመናት ከሸምደዳ ጋር ብቻ የተያያዘ ነበረ፡፡ ይህ ችሎታ ሌሎች ችሎታዎች በተጓዳኝነት እኩል እንዲያደጉ ሳይደረጉ ይኸኛው ብቻ እጅግ ከመጠን ባለፈ ሁኔታ ይበዘበዛል፡፡ ተማሪዎችም በጣም ጥቂቱ ብቻ ሥሪ ላይ ሊውል በሚችል አድካሚ እውቀት አእምሮአቸውን በመሙላት ጊዜአቸውን አባክነዋል፡፡ ስለሆነም አእምሮ ሊጨምቀውና ሊያዋህደው በማይችለው ሸክም ተጨናንቆ ይደክማል፡፡ በጠንካራ መንፈስ በራስ መተማመነ ጥረት ማድረግ ይሳነዋል፡፡ ስለዚህም በሌሎች ሰዎች ውሳኔዎችና ሐሳቦች ላይ የሚተማመን ይሆናል፡፡EDA 256.2

    ይህ የማስተማር ዘዴ ያለበትን ስህተት እየዩ አንዳንዶች ወደሌላው ጫፍ ሄደዋል፡፡ በእነሱ አመለካከት ሰው ማዳበር ያለበት በራሱ ውስጥ ያለውን ብቻ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ትምህርት ደግሞ ተማሪውን ለራሱ የሚሆነውን ካገኘሁ ይበቃኛል ወደሚል አስተሳሰብ ይመራዋል፡፡ በመሆኑም ሰውየውን ከእውነተኛው የእውቀትና የኃይል ምንጭ አቆራርጦ ይለየዋል፡፡EDA 256.3

    የማስታወስ ችሎታን ለማሰልጠን በተካተተው ትምህርት ውስጥ በራስ ነፃነት ማሰብን ተስፋ የሚያስቆርጥ ከሞራል ጋር ግንኙነት ያለው ግን ብዙ ጊዜ አድናቆት የማያገኝ አሠራር ነው፡፡ ተማሪው ደግሞ ለራሱየማሰብና የመወሰን ኃይሉን አሳልፎ በከንቱ በሰጠ መጠን በእውነትና በሐሰት መካከል ያለውን ልዩነት መለየት የማይችል ደካማ ይሆናል፡፡EDA 256.4

    ሆን ተብሎ በሰፊው እየታወቀ የተተወ እውነታ ነው፡፡ መቸም ቢሆን አደጋ ሳያስከትል የቀረበት ጉዜ ባይኖርም ያ ስህተት በትክክለኛ ገጽታው ይታያል፡፡ ተቀባይነት የሚያገኘው ራሱን ከእውነት ጎር በማቀላቀል ወይም በማያያዝ ነው፡፡ ክፉና በጐውን የምታስተውቀውን ዛፍ መመገብ ለመጀመሪያ ወላጆቻችን ውድቀትና ጥፋት ምክንያት ሆነ፡፡ ደጉን አውቆ አንድ ላይ የመቀበል ሁኔታ ለዛሬ ዘመን ወንዶችና ሴቶች ጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡ በሌሎች ሰዎች ውሳኔ የሚተማመን አእምሮ ቀደመም ዘገየም በተሳሳተ መንገድ መመራቱ የማይቀር ቁጥር ነው፡፡EDA 257.1

    በትክክለኛውና በተሳሳተው መንገድ መካከል ያለውን ልዩነት ለይቶ የማወቅ ኃይል ልናገኝ የምንችለው የግል እምነታችን በእግዚአብሔር ላይ ስናሳርፍ ብቻ ነው፡፡ እያንዳንዱ ለራሱ በርሱ ቃል አማካኝነት ከእርሱ መማር አለበት፡፡ የማሰብና የማመዛዘን ኃይሎቻችን እንጠቀምባቸው ዘንድ ከእርሱ የተሰጡን ናቸው፡፡ እግዚአብሔርም እንድንሠራባቸው ይፈልጋል፡፡ «ኑና እንወቃቀስ፡፡» ኢሳ.1፡18 በማለት ይጋብዘናል፡፡ በርሱ ላይ በመተማመን «ክፉውን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ፡፡» (ኢሳ 7፡15 ኤር 7፡15 አረ 1፡5) ጥበብ ይኖረን ዘንድ ነው፡፡EDA 257.2

    እውነት በሆነ ትምህርት ሁሉ ግላዊ የተፈጥሮ ባሕሪይው እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ጊዜ ሰዎችን በየግላቸው የነጋግራቸው ነበር፡፡ አስራ ሁለቱን ያስተማረው በግል ግንኙነትና ማኅበራዊ መግባባት ነበር፡፡ እጅግ ግሩም ድንቅ የሆነውን መመሪያ ብዙ ጊዜ የሚሰጠው ለእያንዳንዱ አድማጭ ለብቻው ነው፡፡ ለተከበረው ረቢ በኦሌቭ ለእያንዳንዱ አድማጭ ለብቻው ነው፡፡ ለተከበረው ረቢ በኤሌቭ ተራራ በነበረው ስብሰባ ላይ ሊታዘንላት ለሚገባው መበለት በውሃ ጉድጓድ አጠገብ አነጋግሯቸዋል፡፡ እጅግ ውድ ዋጋ ያላቸውን መዝገቦቹን ከፈተላቸው፡፡ ምክንያቱም በእነኝህ አድማጮቹ ውስጥ የተሰበረ ልብ ክፍት የሆነ አእምሮና ተቀባይ ወይም ዝግጁ የሆነ መንፈስ እንዳላቸው ለይቶ አውቋል በእየአርምጃዎቹ ሁሉ የሚያጅበው ሕዝብ ሁሉ ስለክርስቶስ ለይቶ ሊያውቀው የማይችል ጀማ አልነበረም፡፡ ለእያንዳንዱ ሰው አእምሮ በቀጥታ ተናግሯል፡፡ እያንዳንዱንም ልብ ተማጽኖአል፡፡ የአድማጮቹን ፊት አስተውሎ ይከታተል ነበር፡፡ በገፃቸው ላይ ብርሃን መብራቱን ይገነዘብ ነበር፡፡ እውነቱ ልባቸው ውስጥ መግባቱን የሚናገር ልብ በጣም ፈጥነው የሚያስተውሉትን ልባቸው የተመለሰውን አድማጮች በርሱ መርካታቸውን የሚገልጽ የምላሽ መዝሙር በርሱ ልብ ውስጥ ይንቆረቆር ነበር፡፡EDA 257.3

    ክርስቶስ በእያንዳንዱ ፍጡር ውስጥ የሚኖሩትን ችሎታዎች ለይቶ ያውቅ ነበር፡፡ ተስፋ ቢስ በሆኑ ውጫዊ ሁኔታዎች ወይም ያልተመቻቹ አካባቢዎች ምክንያት የተመለሰበት ሁኔታ አልነበረም፡፡ ማቲዎስን ከወደብ ጴጥሮስንም ወንድሙን ከአሣ ማጥመድ ሥራ አስነስቶ ከርሱ ይማሩ ዘንድ ጠራቸው፡፡EDA 258.1

    በዛሬ ጊዜ ትምህርታዊ ሥራ ውስጥ ያ ዓይነት ግላዊ ፍላጐት ያ ዓይነት ግላዊ የእድገት ፍላጐት ተፈላጊ ነው፡፡ ተስፋ ሊጣልባቸው አልቻሉም፡፡ እነኝህ ችሎታዎቻቸው ተደብቀው ሊቀሩ የቻሉት አስተማሪዎቻቸው ለይተው ሊመድቧቸው ባለመቻላቸው ነው፡፡ ወንዶችና ሴቶች መልካቸው አዲስ የተፈለጠ ድንጋይ የሚመስል የማያምር ሆኖ ሳለ እሳትን የሚያክል ፈተና ሞገድና ግፊትን መቋቋም የሚችሉ ድንቅ ፍጥረቶች ሆነው ይገኛሉ፡፡ እውነተኛ መምህር ተማሪዎቹ ወደፊት ምን ደረጃ ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ በዓይን ሕሊናው በመመልከት የሚጠቀምባቸውን መሣሪያዎች ፋዳይ ይገነዘባል መምህሩ ለእያንዳንዱ ተማሪ የተለየ የግል ትኩረት ይሰጣል፡፡ እያንዳንዳቸውም ለየራሳቸው ያላቸውን ኃይል የሚያዳብሩበትን መንገድ ይፈልጋል፡፡ ምንም ያክል ጥራት ቡጐድለው ወደ ትክክለኛው መሠረታዊ ሐሳቦች የሚያዘነብል ማናቸውም ጥረት መደገፍ አለበት፡፡EDA 258.2

    እያንዳንዱ ወጣት የተግባርን አስፈላግነትና ኃይል መማር አለበት፡፡ ስኬታማነት በዘር ወይም በልዩ ተፈጥሮአዊ ችሎታ ከሚገኝ ይልቅ በዚህ ላይ የሚመሠረት ነው፡፡ የተማረውን በሥራ ላይ ካላዋለው እጅግ ብሩህ የሆነ አእምሮ ያለው ሰው ችሎታውን ማሣየት የሚችለው በትንሹ ብቻ ነው፡፡ በሌላ በኩል ግን በትክክል የተመራ ጥረት የሚያደርጉ ሰዎች መጠነኛ የሆነ የተፈጥሮ ችሎታ ያላቸው ሆነው እንኳ እጅግ የማያስደንቅ ሥራ አከናውነዋል፡፡ የላቀ የተፈጥሮ ችሎታ ያላቸው ሰዎች በውጤታቸው ዘወትር የምናደንቃቸው ቢሆንም ከሌላው ባልተለየ ያለመታከት ትኩረት ከሚሻ ጥረት ጋር የተዛመደ ነበር ነው፡፡EDA 259.1

    ደካማውም ሆነ ጠንካራው ወጣቶች ሁሉንም ዓይነት ችሎታዎቻቸውን በማዳበር ትምህርት ላይ ማተኮርን መማር አለባቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ብዙዎች በተፈጥሮ ትሎታና ዝንባሌአቸው በሆነው የትምህርት መስመር እንኳ እንዳይገፉ መከልከል የሚያስፈልግበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ ወደዚህ ስህተት እንዳይገቡ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡ የተፈጥሮ ዝንባሌ የወደፊቱን ዘላቂ የሕይወትን የሥራ አቅጣጫ ያመለክታል፡፡ እናም ሕጋዊ መብትም ስለሚሆን በጥንቃቄ መኮትኮት አለበት፡፡ በዚሁ ጊዜም በጥሩ ሁኔታ የተመጣጠነ ባሕሪይና ብቃት የተሞላበት የሥራ አፈፃፀም በማንኛውም መስመር ቢሆን በአመዛኙ እኩልና ተመጣጣኝ እድገት የሚኖረው ዝርዝር ግልጽና ሁለገብ በሆነ የሥልጠና ውጤት ላይ የሚመሠረት መሆኑ በአእምሮ ውስጥ መጠበቅ አለበት፡፡EDA 259.2

    መምህሩ ያለማቋረጥ በቀላሉ የሚስተዋልና ተግባራዊ በሚሆን ነገር ላይ ማለት አለበት፡፡ በአብዛኛው በሚታይ መግለጫ ማብራብት ይኖርበታል፡፡ በእድሜ ትንሽ ከፍ ላሉት ተማሪዎችም እንኳ ቢሆን እያንዳንዱ ማብራሪያ ቀላልና ግልጽ ይሆንላቸው ዘንድ መጠንቀቅ አለበት፡፡ ብዙ ተማሪዎች በእድሜአቸው ትልቅ ሆነው ሳለ በማስተዋል ረገድ ግን ገና ልጅ ይሆናሉ፡፡EDA 260.1

    በትምህርት ሥራ ውስጥ አንድ ዋና አስፈላጊ ነገር ንቃት ነው፡፡ በዚህ ነጥብ ላይ በአንድ እውቅ የመድረክ ሰው አንድ ጠቃሚ አስተያየት ተነግሮ ነበር፡፡ ተዋኒያን አንድ ተውኔታ በሕዝብ ፊት በሚጫወቱበት ጊዜ ሐሳባዊ የሆኑ ነገሮችን በነቃ ኃይል በመናገር የተመልካቹን ልቦና ሰርፀው መግባት ይችላሉ የወንጌል አገልጋዮች ግን እውነትን ይዘው ሳለ ሕዝብን መሳት የሚችሉት በትንሹ ነው፡፡ ይህ ለምን እንደሆነ የካንተበሪው ሊቀጳጳስ የታወቀውን ተዋናይ ሲጠይቁት «ብፁዕነትዎ ሆይ» አለ ተዋናዩ በአክብሮት፡፡ «ምክንያቱ ቀላልና ግልጽ መሆኑን እንድናገር ይፈቀድልኝ በንቃት ኃይል ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እኛ ተዋንያን በመድረክ ላይ ሐሳባዊዩን ነገር እውነት አስመስለን በኃይል እንናገራለን፡፡ ነገር ሐሳባዊ እንደሆነ አስመስላችሁ ስለምትናገሩት ነው » አላቸው፡፡EDA 260.2

    መምህሩ በሥራው በዕውን ተጨባጭ ከሆነ ነገሮች ጋር ሲደክም ይውላል፡፡ እናም ስለ እነዚህ እውነታዎች በሚናገርበት ግዜ እውነትና አስፈላጊ መሆናቸውን የሚገልጽ እውቀት ማነቃቃት የሚችለውን ያክል ባለው ጉልበትና ቅልጥፍና ሁሉ ተጠቅሞ መናገር አለበት፡፡EDA 260.3

    እያንዳንዱ መምህር ሥራው አንድ የተወሰነ ውጤት ያለው መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡ አንዱን ትምህርት ለማሰተማር ከመጀመሩ በፊት በአእምሮው ውስጥ አንድ የተወሰነ ዕቅድ ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡ በትክክል ሊያከናውነው ስለፈለገው ነገር ሊያውቅ ይገባዋል፡፡ ተማሪው በየትኛውም የትምህርት ዓይነት ውስጥ ያለውን መሠረታዊ ሐሳብ እስከሚያስተውለው ዕውነቱን እስከሚረዳና የተማረውን ራሱ መልሶ ማብራራት እስከማችል ድረስ መምህሩ በቃኝ ብሎ ማረፍ የለበትም፡፡EDA 261.1

    ታላቁ የትምህርት ዓላማ እስከ ተጠበቀ ድረስ ወጣቶች ችሎታዎቻቸው የሚፈቅዱላቸውን ያክል ዘልቀውና መጥቀው እንዲሄዱ መበረታታት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ የጥናት ዘርፎችን መከታተል የመጀመራቸው በፊት በዝቅተኛው ትምህርት ላይ ሊካኑ ይገባቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ግን ይህ ሁኔታ ችላ ይባላል፡ በሁለተኛ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና በኮሌጆች ውስጥ ከሚኖሩ ተማሪዎች መካከል እንኳ ስለሚተወቁት ዋና ዋና የትምህርት ክፍሎች ሊኖር በሚገባው እውቀት ላይ በጣም ትልቅ ጉድለት አለ፡፡ ብዙ ተማሪዎች ቁላል የሂሳብ አያያዝ ዘገባ የሚሳናቸው ሆነው ሳለ ከፍተኛ ደግሞ በሚገባና ችሎታ ያለው ሰው ለመሆን የንግግር ዘይቤን ብዙዎች ደግሞ ሥነ-ጽሁፍና ሥነ-ቃላት ያጠናሉ፡፡ ትምህርታቸውን ጨርሰው እንኳ በተራ ደብዳቤ አፃፃፍ ድርሰት በሆሄያት ላይ /ሰፔሊንግ/ ይወድቃሉ፡፡EDA 261.2

    እጅግ መሠረታዊ በሆነ ትምህርቶች ላይ ዝርዝር ዕውቀት ማግኘት ማለት ወደ ከፍተኛ ተቋሞች መግባት መቻል ብቻ መሆን የለበትም ባለሰለሰ ሁኔታ እድገት ማሳየቱን ያለማቋረጥ መፈተሽ እንጅ፡፡EDA 261.3

    በእያንዳንዱ አጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ቴክኒካዊ በሆኑ ትምህርቶች ብቻ ከሚገኘው የበለጠ ጠቃሚ ፍሬ ነገር ይገኝበታል፡፡ ለምሳሌ ቋንቋን ውሰዱ አሁን እየተሠራበት ያለው ይሁን የጠፋ የጥንት የውጪ ሀገር ቋንቋ ከማጥናት ይልቅ ዋናው ነገር የእናትን ቋንቋ በቀላሉና በጥሩ ሁኔታ መናገር መቻል ነው፡፡ ነገር ግን ከጠቃሜታው አንፃር ሰዋሰዋዊ ሕጐችን ጠንቅቆ ከማወቅ የበለጠ ቋንቋን በከፍተኛ ደረጃ ማጥናት የትኛውንም ሌላ ሥልጠና ሊወዳደረው አይችልም፡፡ የሕይወት ደህንነትም ሆነ ዋይታ በአመዛኙ ከዚህ ጥረት ጋር የተቆራኘ ነው፡፡EDA 262.1

    በቋንቋ ውስጥ ዋናው መሟላት ያለበት መጠይቅ ንፁህ የዋህና እውነት መሆኑ ነው፡፡ «የውስጣዊ ፀጋ ውጫዊ መግለጫ ነው፡፡» ይላል እግዚአብሔር፡፡ «እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ ንፁህ የሆነውን ነገር ሁሉ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ መልካም ወሬ ያለበትን ሁሉ በጐነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን እነዚህን አስቡ፡፡» ፊሊ 4፡8 ሐሳቦች ሁሉ እነኝህ ከሆኑ መግለጫዎቻቸውም እንደዚሁ ነው፡፡EDA 262.2

    በዚህ ቋንቋ ጥናት እጅግ ጥሩ የሚሆነው ትምህርት ቤት የምናድግበት ቤት ነው፡፡ ነገር ግን የቤት ውስጥ ሥራ ብዙ ጊዜ በቸልታ ስለሚታይ ተገቢውን የአነጋገር ልማድ እንዲይዙ ለመርዳት ኃላፊነቱ ወደ አስተማሪው ይሸጋገራል፡፡EDA 262.3

    ያንን መጥፎ ልማድ እርም ብለው እንዲተውት መምህሩ ብዙ ሉረዷቸው ይችላል፡፡ የኅብረተሰብ ርግማን የጐረቤት የቤትም ውስጥ መጥፎ ልማድ ሐሜት ስም ማጥፋት ተገቢ ያልሆኑ ትችት ወይም ነቀፋና የመሳሰሉትን መጥፎ ልማዶች፡፡ በዚህ ነጥብ ላይ አንዷም ሳትቀር መወገድ አለበት፡፡ ይህ መጥፎ ለማድ የትምህርት ማነስ የንጽህና እና ከልብ ደግ የመሆን ጉድለት መሆኑን በተማሪዎቹ አእምሮ ውስጥ ቅረፁባቸው፡፡ አንድን ሰው ለኅብረተሰቡ እውነተኛ ባህል የማይሰማማና ብቃት የሌለው በዚህ ዓለምም ፍፁም ሆኖ በሰማይ ላሉ ቅዱሳን ማኅበር አባል እንዳይሆን የሚያደርገው ነው፡፡EDA 262.4

    የራሱን ሥጋ የሚበላ የአውሬነት ጠባይ የተጠናወተውን የሚንቀጠቀጠው የተሸናፊው ስጋ ስናስበው እጅግ ይዘገንነናል፡፡ ነገር ግን በዚህ ትክክል ባልተወከለ ፍላጐት ስም የማጥቆር ተግባር ባህሪና የማበላሽት ውጤቶቹ እጅግ የከፉ ስቀይና ጥፋት ይከተላል አይደለምን? ልጆችና ወጣቶችም ጭምር እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንደሚል ይማሩ፡፡EDA 263.1

    «ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፡፡» ምሣ 18፡21 በቅዱስ መጽሐፍት ውስጥ ሐሜተኞች «እግዚአብሔርን ከሚጠሉ» «ከፋትን ከሚፈላልጉ» «ፍቅር ከሌላቸው ምህረትንም ካጡ «ክፋት ከሞላባቸው ከነፍስ ገዳዮች ከሚከራከሩ ከተንኮለኞች» ይወድባቸዋል፡፡ «የእግዚአብሔረ ሕግ ነውና ሞት ይገባቸዋል፡፡» ሮሜ 1፡29፡30፡31፡32 እግዚአብሔር የጽዮን ዜጋ አድርጐ የሚቀጥለው በልቡ እውነትን የሚናገረውን «በአንደበቱ የማይሸነግል» «በባልንጀራው ላይ ከፋትን የማያደርግ » ሰውን ነው፡፡ መዝ 15፡2-3EDA 263.2

    የእግዚአብሔር ቃል ትርጊም የለሽ የንግግር ሀረጐች ወደ ብልግና የሚጠጉ ሐሳቦችና አባባሎችን ያወግዛል፡፡ የማታለል የተቃውሞ ሐሳቦችን ከእውነት የራቀ ንግግር ማጋነን በሥራ ዓለምና በሕብረተሰቡ ውስጥ በንግድ ሥራ ላይ ሸፍጥና ማጭበርበርን የወግዛል፡፡ «ቃላችሁ አወን አወን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን ከዚህም የወጣ ከክፉው ነው፡፡» ማቴ 5፡37EDA 263.3

    «እንደ እብድ ሰው ባልንጀራውን የሚያታልል በጨ ዋታ አደረግሁት የሚ ል ሰው ም እንዲሁ ነው ፡፡» ምሣ 26፡19 EDA 264.1

    ከስም ማጥፋት ጋር በጣም የተቀራረበ ድብቅ ትርጉም ያለው አነጋገር ከልባቸው ንፁህ ያልሆኑ የደካሞች አሽሙር በግልጽ ሊናገሩት የሚ ፈሩት ስው ር አስተያየት ነው ፡፡ ወደ እንደዚህ ዓይነት ተገቢ ያልሆኑት ተግባራዊ ልማ ዶች ወጣቶች ከለም ፃም ሰው የሚ ሸሹትን ያክል እንዲሸሹ መ ማ ር አለባቸው ፡፡ EDA 264.2

    በቃላት አጠ ቃቀም በኩል አረጋዊያንም ሆኑ ወጣቶች ምናልባት ሳያሰቡት በችኮሎ ላና በንዴ ት ጊዜ በቀላሉ አፍ እላፊ እንደ መናገር የሚ ፈጽሙ ት ሌላ ሰህተት የለም ፡ «መ ቆጣጠር ባለመ ቻሌ ነው ፤ የተናገርኩት ቃል ከልቤ አልነበረም ፡፡» በማለት ይቅርታ ለመ ጠ የቅ በቂ ምክንያት የሚ ኖራቸው ይመስላቸዋል ፡፡ የእግዚአብሔ ር ቃል ግን ይኸንን በቀላሉ አያልፈው ም ፡፡ መ ጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ፡፡ EDA 264.3

    «በቃሉ የሚ ቸኩለው ን ሰው ብታይ ከርሱ ይልቅ ለሰነፍ ተሰፋ አለው ፡፡» ምሣ 29፡20 EDA 264.4

    «ቅጥር እንደሌላት እንደ ፈረሰች ከተማ መ ንፈሱን የማ ይከለከል ሰው እንዲሁ ነው ፡:» ምሳ 25፡28 EDA 264.5

    በአንድ አፍታ በችኮላ ስሜ ታዊ በመሆን በግደለሽነት የተነገረ ቃል የእድሜ ልክ ኑዛዜ ሊመ ልስው የማይችል ክፉ ጉዳት ይሆናል ፡፡ እነሆ እርዳታና ፈው ስ ሊሰጡ ይችሉ በነበሩ ሰዎች የችኮላ ሻካራ ንግግር ልባቸው የተሰረ፤ ከወዳጀነታቸው ተቃቅረው የተለያዩ ሕይወታቸውም የተበለሸ ስንት ናቸው! EDA 264.6

    «እንደሚ ዋጋ ሰይፍ የሚለፊልፍ ሰው አለ ፡፡ የጠቢባን ምላስ ግን ጤ ና ነው ፡፡» ምሳ 12፡18EDA 265.1

    uእያንዳንዱ ልጅ ዘንድ በተለያየ ሁኔታ መፈቀር የሚገባው እና እንክብካቤ ሊደረግላቸው ከሚገባቸው ባህሪያት አንደኛው ያለሰቡት ፀጋ ለሕይወት የሚያጐናጽፍ ራስን የመርሳት ፀባይ ነው፡፡ ከጥሩ ከልጣፋነት ባሕሪይ ሁሉ እጅግ የሚያምረው ይኸኛው ነው፡፡ ለእያንዳንዱ እውነት ለሆነ የሕይወት ሥራ ሁሉ እጅግ ዋና አስኳል የሆነ የብቃት መሠረት ነው፡፡EDA 265.2

    ልጆች አድናቆትን በህራሄንና በመረታታትን ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ከመጠን በላይ መወደስን ማፍቀር እንዳይለምዱ መደነቃቸውን እንዲያውቁት ማድረግ ጥሩ አይደለም፡፡ ወይም የተናገሩትን የብልጠት ንግግር እፊታቸው ላይ በአድናቆት መልሶ መናገር አያስፈልግም፡፡ እውነተኛው የባሕሪይ ከፍተኛ ግምትና ስለሚኖሩ እድሎች እንዲሁም ሊደረስባቸው ስለሚገባ ክንዋኔዎች ሐሳብ ያለው ወላጅ ወይም መምህር ለራሴ ይበቃኛል የሚለውን አስተሳሰብ ሊወደደ ወይም ሊያበረታ አይችልም፡፡ ወጣቱ ችሎታው ወይም ብቃቱ እንዲታወቅለት የሚፈልግ እዩኝ እዩኝ የሚል ፍላጐት እንዲያድርበት አያበረታታም፡፡ ከራሱ በላይ የላቀውን የሚመለከት ሰው ትሁት ይሆናል፡፡ ስለሆነም በውጫዊ እይታ ወይም በሰብአዊ ታላቅነት በብስጭት ግራ የመጋባት ስሜት ውርደት የሚያሳፍር ስህተት የሌለበት የተከበረ ሰው ይህናል፡፡EDA 265.3

    የባሕሪይን ፀጋ የሚያዳብረው ኃይልን የሚጠቀም የቅጣት ሕግ ወይም ደንብ አይደለም፡፡ ንፁህ፣ ክቡርና እውነት የሆነ ድቫቫ /አትሞስፌር/ ሁኔታን በውስጡ በማሣደር እንጂ፡፡ የልብ ንጽህናና የባሕሪይ ትልቅነት ባለበት ሁሉ በንጽህናና ክቡር ቀና በሆነ አሠራርና ንግግር ይገለጣል፡፡EDA 265.4

    «የልብን ንጽህና የሚወደድና ሞገስ በከንፈሩ ያለች ንጉሥ ወዳጃ ይሆናል፡፡» ምሳ 22-11EDA 266.1

    እንደ ንግግርም ሁሉ በሌላው ጥናትም ውስጥ ባሕሪይን ሊገነባና ሊያበረታታ የሚችል ነገር ሁሉ በክትትል አመራር ሊሰጥበት ይገባዋል፡፡EDA 266.2

    ይህ በአመዛኙ ከሌላው ሁሉ በበለጠ በታሪክ ጥናት ላይ እውነትነቱ ይታያል፡፡ ከለኮታዊ አስተሳሰብ አንፃር ተመዛዝኖ ይታሰብ፡፡EDA 266.3

    ብዙ ጊዜ ታሪክ፤ ከነገሥታት አነሳስና ውድቀት የአባባይ የሸንጐ ምስጢራዊ ተንካሎች የሠራዊት ድል አድራጊነት ወይም ሽንፈት፣ ትልቅ ምኞት የማጋበስ ስግበግብነት፣ የማታለል፣ የጭካኔና ደም ማፍሰስ ዘገባ ከመሆን ሌላ እምዛም እንደማያልፍ ደተርጐ ይታሰባል፡፡ ይኸንን ማስተማር ውጤቱ ከአደጋ በስተቀር ሌላ እርባና የለውም፡፡ የልብ ሕመም የሚሆን የወንጀል ድግግሞሽና የሕዝብ እልቂት፤ በደል የጭካኔዎች ስዕል መጨረሻቸው የክፋት ፍሬ ማጨድ የሚሆን የአትክልት ዘሮችን በብዙዎች ሕይወት ውስጥ ማብቀል ነው፡፡EDA 266.4

    መንግሥታት ሊወድቁና ሊነሱ የሚችሉበት መነሻ ምክንያቶቹን የሚቆጣጠረው ቃል ብርሃንነት መማር የበለጠ ጠቃሚ ነው፡፡ ወጣቶች እነዚህን ዘገባዎች ያጥኑ፡፡ እናም የሕዝቦች እውነተኛ ብልጽግና የመለኮትን መርሆዎች ከመቀበል ጋር ምን ያክል የተያያዘ እንደሆነ ይመልከቱ ታላቁን የተሃድሶ እንቅስቃሴ ታሪክ ያጥና እናም እነዚህ መሠረታዊ ሀሳቦች ምንም ምንኳ ቢዘለሉና ቢጠሉም ደጋፊዎቻቸው ዘወትር ወደጭለማ ምድር ቤት ሲጣሉና ወደመሰቀያው እንጨት ቢቀርቡም በእነዚህ መስዋዕትነቶች አማካይነት እንዴት ድል እንዳደረጉ ይመልከቱ፡፡EDA 266.5

    እንዲህ ዓይነት ጥናት ስለ ሕይወት ሰፊና አጠቃላይ አመለካከት ይሰጣል፡፡ ወጣቶች ከነገሮቹ ግንኙነትና አንዱ በሌላው ላይ ስማመመስረቱም አንድ ነገር እንዲያስተውሉ ይረዳቸዋል፡፡ በታላቁ የወንድማማችነት ኅብረተሰብና ሕዝቦች ውስጥ ሁላችን እንዴት በሚያስገርም ሁኔታ በአንድ ላይ እንደተሳሰርን የአንድ አባል መጨቆን ወይም መዋረድ ለሌላው ሁሉ ምን ያክል ታላቅ ጥፋትና የሚያጐድል መሆኑን እንዲያስተውሉ ይረዳቸዋል፡፡EDA 267.1

    ሂሳብ በሚያጠኑበት ጊዜ ጥናቱ ተግባራዊ ይሁን፡፡ እያንዳንዱ ወጣትና ልጅ ሐሳባዊ የሆኑትን ቁጥሮች ማስላት ብቻ ሣይሆን የራሱን የግል ገቢና ወጪ በትክክል መዝግቦ መያዝን መማር አለበት፡፡ የገንዘብን ትክክለኛ ጥቅም በተግባር እየተጠቀመበት ይማር፡፡ ከላጆቻቸው የተሰጣቸውም ሆነ ራሳቸው ባገኙት ገቢ ወንዶችና ሴት ልጆች ልብሶቻቸውን መጽሐፎቻቸውንና ሌሎች የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ሁሉ ራሳቸው መርጠው መግዛትን ይማሩ፡፡ የራሳቸውን ወጪም መዝግበው በመያዝ በሌላ በምንም መንገድ ሊማሩ የማይችሉትን የገንዘብን ፋይዳና ምንነት ይማራሉ፡፡ ይህ ይልጠና በአንድ በኩል እውነተኛውን የኢኮኖሚ አያያዝ ከቆጥቋጣነት በሌላ በኩል ደግሞ አባካኝነትንም ምን እንደሆነ ለይተው እንዲያውቁ ይረዳቸዋል፡፡ በትክክል ከተመሩ ትሁትና ጠቃሚ የመሆንን ልምዳቸውን ያበረታታላቸዋል፡፡ ወጣቶች መስጠትን እንዲማሩ ጊዜያዊ ፍላጐታቸው በሥርዓት መለገስን እንዲማሩ ይረዳቸዋል፡፡EDA 267.2

    በዚህ ዓይነት መንገድ እያንዳንዱ ጥናት ከሁሉም በበለጠ ትልቅ ችግር ላይ የሚረዳ የልጆች ስልጠና በሕይወት ለሚገጥሙ ኃላፊነቶች ሁሉ የሚመጥኑ የሚያደርጋቸው ይሆናል፡፡EDA 268.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents