Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 10—እግዚአብሔር በተፈጥሮ ውስጥ

  «ክብሩ ሰማይን ሞላ፣
  ምድርም በምስጋናው ተሸፈነች፡፡»
  EDA 106.1

  በሁሉም የፍጥረት ነገሮች ሁሉ ላይ የመለኮት አሻራ ይታያል፡፡ ተፈጥሮ ስለ እግዚአብሔር ትመሰክራለች፡፡ ተጠራጣሪ አእምሮ የዩኒቬርስን ሚስጥር ሲመለከት ወሰን የሌለበትን ኃይል ከመገንዘብ በስተቀር ሌላ ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ይች ዓለም በረከቷን ሁሉ የምታፈራውና ከዓመት ዓመት ያለማቋረጥ በፀሐይ ዙሪያ የምተንቀሳቀሰው በራሷ ውስጥ ባለ ኃይል አይደለም፡፡ አንድ ማይታይ እጅ ፕላኔቶች በሰማይ ውስጥ በራሳቸው ምህዋር እንዲሽከረከሩ ያደርጋል፡፡ ተፈጥሮ ሁሉ ሚስጥራዊ በሆነ ሕይወት ውስጥ ይኖራል፡፡ ልክ በሌለው እጅግ ሰፊ በሆነው በሕዋው ውስጥ ያሉ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ዓለማት ሁሉ ከዘመን ዘመን እየተሸጋገሩ የሚኖሩበት ሕይወት፤ በመኸር ወቅት በሚታዩት ትንኞች ውስጥ ያሉ ነፍሳት፣ ለሚጮኹ ጫጩቶቿ ምግብ የምታመጣዋ ወፍ የምትበርበትን ክንፍ፣ ቀምበጡን እንዲያድግ አባውንም ፍሬ እንዲሰጥ ከሚያደርግ ሚስጥራዊ ኃይል አለ፡፡EDA 106.2

  ያ ተፈጥሮን ቀጥ አድርጐ የያዘው ኃይል በሰው ውስጥም እየሠራ ነው፡፡ ከዋክብትንና አተሞችን አንድ ላይ የሚመራው ታላቅ ሕግ የሰውን ልጅ ሕይወትም ይቆጣጠራል፡፡ የልብን ተግባር የሚገዙ ሕጐች የሕይወተ ፈሳሽ ወደአካል የመዳረሱን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠሩ፣ በነፍስ ላይ የመፍረድ ሥልጣን ያለው የታላቁ ኃያል ሕጐች ናቸው፡፡ ሕይወት ሁሉ ከርሱ ይወጣል፡፡ እውነተኛው የተግባር እንቅስቃሴ ከርሱ ጋር በመዋሐድ ብቻ የሚገኝ ነው፡፡ ለፈጠራቸው ነገሮች ሁሉ ሁኔታው ያው ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ሕይወት በመቀበል የምትኖር ሕይወት ከፈጣሪ ፍላጐት ጋር በመዋሐድ የምትሠራ ስትሆን ብቻ ነው፡፡ በአካል፣ በህሊናና በሞራል ሕጉን መተላለፍ ራስን ከዩኒቨርስ ውጭ ለማድረግና ሕገወጥ ስርአት አልበኝነትንና ጥፋትን ለማስተዋወቅ የሚደረግ ተግባር ነው፡፡EDA 106.3

  ስለዚህም ትምህርቶቹን ለመተርጐም የሚሞክር ወይም የሚማር ሰው ተፈጥሮ ሁሉ ብሩህ ይሆንለታል፡፡ ዓለም የትምህርት መጽሐፍ ሕይወትም ትምህርት ቤት ትሆንለታለች፡፡ ሰው ከተፈጥሮና ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረው አንድነት፤ የሕግም ዓለምአቀፋዊ የበላይነት ሲኖር ሕግን የመተላለፍ ውጤቶች አእምሮን ሊስቡና ባህሪንም ሊቀርፁ አይችሉም፡፡EDA 107.1

  ልጆቻችን ሊማሯቸው የሚገባ ትምህርቶች እነዚህ ናቸው፡፡ ለትንሹ ልጅ የታተሙ ገጾችን አገላብጦ ትምህርት ለመውሰድ ለማይችለው ሕፃን ወይም ገና ወደትምህርት ቤት ገብቶ አንዳንድ ነገሮችን መለማመድ ለጀመረ ልጅ ተፈጥሮ ከዋናው ምንጭ ትምህርትና ደስታን ትሰጠዋለች፡፡ ከክፋት ጋር በመገናኘት ልቡ የደነደነ ባለመሆኑ የተፈጠሩ ነገሮችን ሁሉ እንዲስፋፋ የሚያደርግ ኃይል መኖሩን በፍጥነት ይገነዘባል፡፡ ጆሮው በዓለም አደንቋሪ ጩኸት ገና ያልተጐዳ በመሆኑ በተፈጥሮ በኩል የሚናገረውን ድምጽ ለመስማት ቀልጣፋ ነው፡፡ በእድሜአቸው ገፋ ላሉት ደግሞ ፀጥ ያለ አስታዋሽነቷን ያለማቋረጥ መንፈሳዊና ዘለዓለማዊውን ለሚፈልጉ ተፈጥሮ የምተሰጠው ትምህርት ቀላል ግምት የማይሰጠው የመመሪያ (የትምህርት) ምንጭ ይሆናል፡፡ በኤደን ይኖሩ የነበሩ ከተፈጥሮ ገጾች እንደተማሩ ሁሉ ሙሴ የእግዚአብሔርን የእጅ ጽሁፍ በአረቢያ ሜዳዎችና ተራራዎች ለይቶ እንዳስተዋለና እንደተገነዘበ ሁሉ ሕፃኑ የሱስም እንዲሁ በናዝሬት ኮረብቶች አካባቢ፣ እንደዚሁም ሁሉ የዛሬ ልጆች ከርሱ ሊማሩ ይገባቸዋል፡፡ የማይታየው በሚታየው አካል ውስጥ ይገልፃል፡፡ በምድር ባለ ነገር ሁሉ ላይ በጫካ ውስጥ ካለው ግዙፍ ዛፍ ጀምሮ በቋጥኝ ላይ እስከምትጣበቀው አቃቅማ ድረስ፤ መጠን ከሌለው ውቅያኖስ ጀምሮ በዳርቻው እስከምትገኘው እጅግ ትንሻE ቀንድ አውጣ ድረስ በእግዚአብሔር ምሳሌና በላዩ ላይ በትልቁ በተፃፈው የእጅ ሥራው ውስጥ ናቸው፡፡EDA 107.2

  በተቻለ መጠን ልጃችሁ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ይህ አስገራሚ የትምህርት መጽሐፍ ሊገለጥለት በሚችል ትምህርት ቤት ውስጥ ይግባ፡፡ በታላቁ ባለጥበብ ጌታ የተሠራውን ሰማይን የሸፈነውን ግርማ ሞገስ የተላበሰ ስዕል ይመልከት፡፡ በምድርና በባህር ውስጥ ካሉት ድንቅ ነገሮች ጋርም ይተዋወቅ፡፡ የሚለዋወጡትን የወቅቶች ሚስጥር ግልጽነት በጥንቃቄ ይመልከት፡፡ በእርሱ ሥራዎች ውስጥ ሁሉ ስለ ፈጣሪ ይማር፡፡EDA 108.1

  የእውነተኛ ትምህርት መሠረት በምንም ዓይነት በሌላ ጥብቅ የማይናወጥና እርግጠኛ መሠረት ላይ ሊጣል ከቶ አይቻልም፡፡ ሕፃኑ ከተፈጥሮ ጋር በተገናኘ ቁጥር ግራ የሚያጋቡ ምክንያቶች ሊመለከት ይችላል፡፡ ነገር ግን ሁለት ተፃራሪ ነገሮች መኖራቸውን ብቻ ከመረዳት በስተቀር ሌላ ሊያደርግ የሚችለው ነገር የለም ተፈጥሮ ተርጓሚ የምትፈልገው እዚያ ላይ ነው፡፡ በክፋት መግለጫዎች ላይ በመመልከት ፍጡር በሆነው ግሀድ ዓለም ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት ተመሳሳይነት ያለው ያው አሳዛኝ ነገር ነው፡፡EDA 108.2

  ከመስቀሉ ሥፍራ የሚወጣው ብርሃን ብቻ ነው የተፈጥሮ ትምህርት በትክክል ሊነበብ የሚችለው፡፡ በቤተልሄም ታሪክና ክፉን ማሸነፍ ምን ያክል መልካም እንደሆነ እንዲሁም ለእኛ የሚመጣልን እያንዳንዱ በረከት የደህንነት ስጦታ መሆኑን መስቀሉ አሳይቷል፡፡EDA 108.3

  የሚበክልና የሚያበላሽ፣ ሕይወትን የሚያጠፋ ክፋት በእሾህ በአሜኬላ በአጋምና በአቃቅማ ተመስሎ ተወክሏል፡፡ ፈዋሽና አዳሽ የሆነው ፍቅር ደግሞ በምትዘምር ወፍ በሚፈኩ እምቡጦች በዝናብና በፀሐይ ብርሃን በመኸር ለስላሳ ነፋስ በርጋታ በሚወርድ ጤዛ በተፈጥሮ ውስጥ ባሉ በአሥር ሽህ ነገሮች፣ ከጫካው ወርካ በሥሯ እስከምትፈካው ቫዬሌት ድረስ ታይቷል፡፡ ተፈጥሮ እስከአሁንም ድረስ የእግዚአብሔርን ቸርነት ትናገራለች፡፡EDA 109.1

  «ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ ፍፃሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ፡፡ የሰላም አሳብ ነው እንጅ የክፉ ነገር አይደለም፡፡» ኤር 29፡11 ከመስቀሉ በሚወጣው ብርሃን አማካይነት በተፈጥሮ ሁሉ ላይ መነበብ ያለበት መልዕክት ይኸው ነው፡፡ ሰማያት የርሱን ክብር ይናገራሉ ምድርም በርሱ ሀብት ሞልታለች፡፡EDA 109.2

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents