በእምነት መዝራት
ቁጥር ስፍር የሌለው ትምህርት በተለያዩ የእድገት ሂደቶች የሚሰጥ ሲሆን እጅግ ድንቅ ከሆኑት ውስጥ ጥቂቶቹ ደግሞ መድህን በምሳሌነት ካቀረበው ስለዘር እድገት የተናገረው ይገኝበታል፡፡ ለአረጋዊያንና ለወጣቶች የሚሆን ትምህርት አለው፡፡ ሌሊትና ቀን ይተኛልም ይነሳልም እርሱም እንዴት እንደሆነ ሳያውቅ ዘሩ ይበቅላል ያድጋልም፡፡ ምድሪቱም አውቃ በመጀመሪያ ቡቃያ በኋላም ዛላ ኋላም በዛላው ላይ ፍፁም ሰብል ታፈራለች፡፡» ማር 4፡26-28EDA 112.4
ዘሩ ራሱ በውስጡ የአበቃቀል ሕግ አለው፡፡ እግዚአብሔር ራሱ በውስጡ ያበቀለው ሕግ ነው፡፡ ነገር ግን ዘሯ በራሷ እንድታድግ ቢተዋት ኖሮ ከመሬት ለመነሳት የራሷ ኃይል ባልኖራትም፡፡ ፍሬዋ እንድታድግ በማድረግ በኩል ሰውየው የራሱ የሆነ የሥራ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ ነገር ግን ሠርቶ ሠርቶ አንድ ነጥብ ላይ ሲደርስ ከዚያ በኋላ ምንም ሊያደርግላት የማይችልበት ደረጃ አለ፡፡ ይኸውም የዘሩን ሥራ ከፍሬ አሰባሰቡ ሥራ ጋር በሚያገናኘው አስደናቂና ዘለዓለማዊ በሆነው ኃይሉ ግሩም የአያያዝ ዘዴ ባለቤት በሆነው አንድ አምላክ ላይ መተማመን አለበት፡፡EDA 113.1
በዘሯ ውስጥ ሕይወት በአፈሩም ውስጥ አንድ ኃይል አለ፡፡ ነገር ግን ወሰን የሌለበት ኃይል ቀንና ሌሊት ካልታከለበት በስተቀር ዘሩ ፍሬአልባ ይሆናል፡፡ ዝናብ የተጠሙ ሜዳዎችን ማርካት አለበት ፀሐይም ሙቀት መስጠት አለባት፡፡ አፈር የለበሰችው ዘርፍ ኤሌክትሪካዊ የሆነ አንድ ኃይል ማግኘት አለባት፡፡ ፈጣሪ በውስጧ የዘራውን ሕይወት እንዲያድግ ሊያደርግ የሚችለው እሱ ብቻ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ኃይል እያንዳንዱ ዘር ያድጋል፡፡ እያንዳንዱ አትክልትም ይለመልማል፡፡ «ዘሩም የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡» «ምድር ቡቃያዋን እንደምታወጣ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ምስጋናን በሕዝብ ፊት ሁሉ ያበቅላል፡፡» ኢሣ 61፡11 በተፈጥሮ ውስጥ እንደሆነው ሁሉ በመንፈሳዊው ዘርፍ ሕይወት ሊዘራ የሚችለው ብቸኛው ኃይል የእግዚአብሔር ነው፡፡EDA 113.2
ዘሩም የሚዘራው ገበሬ ሥራ የእምነት ሥራ ነው፡፡ ዘሩ እንዴት እንደሚበቅልና የአስተዳደጉን ሚስጢር ሊያውቅ አይችልም፡፡ ነገር ግን ገበሬው እግዚአብሔር አትክልቶቹን እንዲያፋፋ በሚያደርጉ አካላት ላይ እምነት አለው፡፡ በመሆኑም በመከር ስብሰባ ወቅት በእጥፍና ከዚየም በላይ በብዙው እንደሚያገኝበት ተስፋ በማድረግ ዘሩን ይበትናል፡፡ እንደዚሁ ደግሞ ወላጆችና መምህራን ከዘሩት ዘር ውጤት በመጠበቅ እንዲሠሩ ያስፈልጋል፡፡EDA 113.3
ለጊዜው ጥሩው ዘር በደንብ ሳይታይ መሬት ውስጥ ወድቆ ተሸፍኖ ይሆናል፡፡ ሥር መስደዱም ላይታወቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን ወደኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ በነፍሷ ላይ እስትንፋስ እፍ ባለባት ጊዜ የተደበቀችው ዘር ተዘረጋግታ ትነሳለች፡፡ በመጨረሻም ፍሬ ትሰጣለች፡፡ በሕይወት ሥራችንም የትኛው ዓይነት ሥራ እንደሚያበለጽገን አናውቅም፡፡ ይኸኛው ይሁን ወይም ያኛው፡፡ እኛ ይኸንን ጥያቄ ለመፍታት አንችልም፡፡ «በማለዳ ዘርህን ዝራ በማታም እጅህን አትተው፡፡» መክ. 11፡6 በእግዚአብሔር ታላቅ ቃልኪዳን መሠረት «በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም፡፡» ዘፍ 8፡22 በዚያ የተስፋ ቃል በመተማመን ሰው ያደርሳል ይዘራል፡፡ መንፈሳዊ ሕይወታችንም አሠራሩ ከዚህ የሚለይ አይደለም፡፡ መዝራትና በእርሱ ማረጋገጫ መተማመን ብቻ ነው፡፡ «ከአፌ የሚወጣው ቃሌ እንዲሁ ይሆናል የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጅ ወደኔ በከንቱ አይመለስም፡፡» «በለቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይለቅማሉ፡፡ በሄዱ ጊዜ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ፡፡» ኢሳ 55፡11 መዝ 126፡6EDA 114.1
የዘሩ መብቀል በመንፈሳዊ ሕይወት መጀመር ይመሰላል፡፡ የአትክልቱ መፋፋትና ማደግ ደግሞ የባህሪን ማደግ የሚያመለክት ይሆናል፡፡ ያለእድገት ሕይወት ሕይወት አይሆንም፡፡ አትክልቱ ማደግ ወይም መሞት አለበት፡፡ እድገቱ ደግሞ በፀጥታና ሳይታወቅ ግን ያለማቋረጥ እንደሚሆን ሁሉ የባህሪ እድገትም እንደዚሁ ነው፡፡ በእያንዳንዱ የእድገት ደረጃ ላይ ሕይወታችን ፍፁም ወደ መሆን እያደገ ይሄዳል፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ያሰበው ዓላማ ከተሟላ ደግሞ በማያቋርጥ እድገት እንረማመዳለን፡፡EDA 114.2
አትክልቷ እግዚአብሔር በሕይወት እንድትቀጥል አድርጐ የሚያሟላላትን ስጦታ በመቀበል ታድጋለች፡፡ መንፈሳዊ እድገትም እንደዚሁ ሊደርስበት የሚቻለው ከመለኮታዊ አካላት ጋር በመተባበር ነው፡፡ አትክልቷ በአፈሩ ውስጥ ሥሯን እንደምትሰድ እኛም በክርስቶስ ሥሮቻችን በመዘርጋት እናድጋለን፡፡ አትክልት ፀሐይ ጤዛና ዝናብ እንደምታገኝ ሁሉ እኛም መንፈስ ቅዱስን መቀበል አለብን፡፡ ልባችን በክርስቶስ ከቆየ እርሱ ወደእኛ ይመጣል፡፡ «እንደዝናብ ምድርን እንደሚያጠጣ እንደመጨረሻ ዝናብ ይመጣል፡፡» እንደጽድቅ ፀሐይ በእኛ ላይ ይወጣል፡፡ «ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፡፡» እንደአበባም እያደግን «እናብባለን» «ከእህሉም የተነሳ ይጠግባሉ፡፡ እንደ ወይን አረግም ያብባሉ፡፡» ሆሴ 6፡3 ሚልከ 4፡2 ሆሴ 14፡5-7 EDA 115.1
ስንዴውም አደገ፡፡ «በመጀመሪያ ቡቃያ በኋላም በዛላዋ ፍፁም ሰብል ታፈራለች» ማር 4፡28 እህሉን በመዝራትና ተንከባክቦ በማሳደግ በኩል ዘር የሚዘራው የማሳው ባለቤት ዓላማው ለረሀብ ጊዜ ዳቦ ለማግኘትና ለወደፊቱ የከርሞ ዘር የሚሆን በቂ ምርት ማግኘት ነው፡፡ እንደዚሁም መለኮታዊው የእርሻ ባለቤት ምርት ይጠብቃል፡፡ በእነርሱ አማካይነት ወደ ሌሎች ሰዎች ልቦናና ሕይወት ውስጥ ገብቶ መራባት ይችል ዘንድ ራሱን በተከታዮቹ ልቦናና ሕይወት ውስጥ ማራባት ይፈልጋል፡፡EDA 115.2
አትክልቷ ከዘር ጀምራ የምታሳየው የቀስ በቀስ ዕድገት ልጅን ለማሰልጠን የሚጠቅም ተጨባጭ ትምህርት ነው፡፡ ልክ «መጀመሪያ ቡቃያው ከዚያ በኋላ ጆሮው ከዚያም ሙሉ ሰብሉ» ማር 4፡28 እንደሚገኝ ሁሉ ይኸንን ምሳሌአዊ ትምህርት የሰጠው ጌታ ትንሿን ዘር ፈጠረ፡፡ ዋናውን ባህሪም ሰጣት፡፡ ዕድገቷን የሚገዙ ሕጐችን ቀባ ወይም ባረከ፡፡ በዚህ ምሳሌ አማካይነት የተሰጡ የእውነት ትምህርቶች በራሱ ሕይወት ውስጥ በኑሮው በትክክል ተገልፀዋል፡፡ ያ የሰማዩ ግርማዊ ንጉሥ የክብር ንጉሥ በቤተልሃም እንደ ሕፃን ተወለደ፡፡ ለጊዜው ያለ እናቱ በስተቀር ሌላ የሚንከባከበው ሰው በሌለው ሕፃን ተመሰለ፡፡ በልጅነቱም ወላጆቹን በማክበር የሚፈልጉትን በመርዳት በኩል እንደልጅ ይናገርና ይሠራም ነበር፡፡ ነገር ግን ከመጀመሪያዋ የእውቀት ዕለት ጀምሮ ያለማቋረጥ በፀጋና በእውነት እውቀት ያድግ ነበር፡፡EDA 115.3
ወላጆችና መምህራንም እንደዚሁ እንደጓሮ አትክልቶች ተፈጥሮን በመግለጽ ወጣቱ በሕይወት ደረጃዎች የሚኖረው ዝንባሌ ለወቅቱ ተስማሚ የሚሆነውን ውበት እንደያዘ አድርገው ለማሳደግ ዓላማ ሊኖራቸው ይገባል፡፡EDA 116.1
ትንንሽ ልጆች ደግሞ እንደትንሽ ልጅ የዋህ ሆነው እንዲያድጉ ማስተማር ያስፈልጋል፡፡ ለዚያ እድሜአቸው ሊኖረው የሚገባውን ትንንሽ ሥራዎችን ማገዝ፣ የደስታና በኑሮአቸው ቁም ነገር የመጨበጥ ልምድ እንዲኖራቸው ተደርጐ መሰልጠን ይገባቸዋል፡፡ ልጅነት በቡቃያው ይመሰላል፡፡ ቡቃያው ደግሞ የራሱ የሆነ ልዩ ውበት አለው፡፡ ሕፃናት ያለእድሜአቸው ደርሰው እንደትልቅ ሰው ልዩ ችሎታ የሚያሳዩ እንዲሆኑ መገደድ የለባቸውም፡፡ ነገር ግን በተቻለ መጠን የጧት ዕድሜአቸውን ትኩስነትና ፀጋ እንደያዙ መሆን አለባቸው፡፡ የልጁ ሕይወት ፀጥታ ያለበት የተረጋጋና ቀላል በሆነ መጠን፣ ከሰው ሠራሽ መዝናኛዎች ነፃ በሆነ መጠን፣ ከተፈጥሮ ጋር በቀረበና በተዋሀደ መጠን፣ ለአካላዊና ለአእምሮ ኃይል መዳበርና ለመንፈሳዊ ጥንካሬው የበለጠ የሚስማማው ይሆናል፡፡ EDA 116.2
መድኃኔአለም አምስት ሺውን ሲመግብ ባሳየው ተዐምር ምርትን በማበርከት ረገድ የእግዚአብሔር ኃይል የሚሠራው ነገር ተገልጦለታል፡፡ የሱስ ከተፈጥሮ ዓለም ላይ መጋረጃውን አነሳና ለእኛ ደህንነት ያለማቋረጥ የሚሠራውን ፈጣሪ ኃይል አሳየ፡፡ በእርሻ ላይ የተዘራውን ፍሬ በማራባት ያ ዳቦዎቹን ያበረከተው ኃይል በየቀኑ ተዐምር በመሥራት ላይ ነው፡፡ ከዐለም የሰብል ማሳዎች ላይ ሰብስቦ በሚሊዬን የሚቆየሩትን የሚመግበው በእርሱ ተዐምር ነው፡፡ ሰብሉን በመንከባከብና ዳቦውን በማዘጋጀት ሰዎች እንዲተባበሩ ተጋብዘዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ግን መለኮታዊውን አካል ማየት አልቻሉም፡፡ የርሱ ኃይል የሚሠራውን እንደተፈጥሮአዊ ምክንያቶች ወይንም እንደሰብዓዊ መሣሪያነት ተደርገው ታስበዋል፡፡ የርሱ ስጦታዎች ደግሞ ብዙ ጊዜ አለአግባብ ለራስ ግላዊ ጥቅም በመዋላቸው በረከት በመሆን ፋንታ እርግማን ሆነዋል፡፡ እግዚአብሔር ይኸን ሁሉ መለወጥ ይፈልጋል፡፡ የደነዘዙት ስሜቶቻችን ተነቃቅተው ምህረት የተሞላበትን ችሮታዎቹን ለይተው እንዲገነዘቡና እርሱ ለእኛ የሚሰጠን ስጦታዎች ሁሉ እርሱ ባሰበልን በረከት ይሆኑ ዘንድ ፍላጐቱ ነው፡፡EDA 117.1
የእግዚአብሔር ቃልና የርሱ ሕይወት ክፋይ አካል ነው፡፡ ለዚያች ዘር ሕይወት የሚሰጣት እሱ ነው፡፡ እኛም ፍሬዋን በመመገብ የዚያን ሕይወት ክፋይ እናገኛለን፡፡ ይኸንን ለይተን እንድናውቅ እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ የዕለት ምግባችን በመቀበልም ረገድ እንኳ የእርሱን የአሠራር ሁኔታ መገንዘብና ወደርሱ ወዳጅነት የበለጠ መቅረብ ያስፈልገናል፡፡EDA 117.2
በተፈጥሮ ውስጥ ባሉ በእግዚአብሔር ሕጐች ባልተለያየ እርግጠኛ ሁኔታ ውጤት ምክንያት ሲከተል ኖሯል፡፡ የተዘራው ሰብል ለፍሬ መድረስ የአዘራሩን ትክክለኛነት ያስረዳል፡፡ እዚህ ላይ ምንም ዓይነት የማስመሰል ተግባርን በትዕግሥት ማለፍ አይቻልም፡፡ ሰዎች መሰል ሰዎቻቸውን ማታለል ይችሉ ይሆናል፡፡ በዚህም ላልደከሙበት ሥራ ምስጋናና ዋጋ ሊያገኙበት ይችሉ ይሆናል፡፡ በተፈጥሮ ውስጥ ግን ማታለል አይሠራም፣ ማለፍ የሚቻል ነገርም አይደለም፡፡ ታማኝ ባልሆነው ባለእርሻ ላይ ሰብሉ ራሱ ባለቤቱን ይኮንነዋል፡፡ ያወግዘዋል፡፡ ይህ ደግሞ በመንፈሳዊው መንገድም በትክክል የሚመስለው ይኸንኑ ነው፡፡ በክፉው መንገድ የሚሳካልን ነገር ቢኖር በገጽታው ሊመሳሰል ይችላል፡፡ ነገር ግን እውነት አይደለም፡፡ ያለምክንያት ከት/ቤት ወጥቶ የሚጫወት ልጅ ትምህርቱን ለማጥናት የሚሰንፍ ሐኬተኛ ወጣት በሚሰጠው አገልግሎት የቀጣሪ አለቃውን ፍላጐት የማያሟላ ወስላታ ፀሐፊ ወይም የእጅ ባለሙያ ወይም በማንኛውም ሥራ እና የሙያ መስክ ያለበትን ትክክለኛ ኃላፊነት በእውነት የማይወጣ ሰው፣ ጥፋቱ እስከ ተደበቀለት ድረስ ጥቅም በማግኘቱ ተደስቶ ሊፈነድቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን ልክ አይደለም፣ ምክንያቱም ራሱን ማሞኘቱ ነውና፡፡ የሕይወት አዝመራ ባህሪ ነው፡፡ የመጨረሻ ግባችን የሚወስነውም ይኸው የባህሪአችን ዓይነት ነው፡፡ በአሁኑና ለሚመጣው ሕይወትም ጭምር፡፡EDA 117.3
አዝመራ የተዘራው ዘር ብዜት ነው፡፡ እያንዳንዱ ዘር የራሱ ዓይነት ፍሬ ያፈራል፡፡ እኛ የምንወደው ያው የባህሪአችንን ዝርያ ነው፡፡ ራስን መውደድ የራስ ፍቅር የራስ ክብር በራስ ፍላጐት ብዙ ማጥፋት እንዲህ ዓይነት ተግባራት ራሳቸውን ያበራክታሉ፡፡ መጨረሻውም ሥቃይና የተበላሸ ጥፋት ነው፡፡ «በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና በመንፈስ ግን የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና በመንፈስ ግን የሚዘራ ከመንፈስ የዘላለም ሕይወትን ያጭዳል፡፡» ገላት 6፡8 ፍቅር አዛኝ ሩህሩህነት እና ደግነት የበረከትን ፍሬ ያፈራሉ፡፡ የማያልቅና የማይጠፋ አዝመራ፡፡EDA 118.1
ዘሩ በአዝመራ ወቅት ተበራክቶ ይገኛል፡፡ አንዲት ፍሬ ስንዴ ተደጋግማ በምትዘራበት ጊዜ ትጨምራለች፡፡ ወርቃማ በሆነው ዛላዋ ማሳውን በሙሉ ታለብሳለች፡፡ የአንድ ሰው ሕይወትም፣ እንዲያውም አንዷ ሥራው እንኳ በስፋት ብዙዎችን የምትስብ ትሆናለች፡፡EDA 118.2
ከከበረ ድንጋይ የተሠራው ሳጥን ተሰብሮ ክርስቶስ በክብር ይቀባሉ ዘንድ የተደረገው አንዷ ድርጊት በረዥም ምዕተ ዓመታት ውስጥ ምን ዓይነት የፍቅር ትዝታ ተግባር ነው የሚያስታውሰን፡፡ ያ አስተዋጽአ በአንዲት ስሟ ባልተጠቀሰ ድሃ መበልት የተበረከተው በዚያ ሁሉ ቁጥር ስፍር ከሌለው የተበረከተ ስጦታ «ድሀዋ የሰጠችው ሁለት ናስ አንድ ሳንቲም የሚያክሉ» ማር 12፡42 ለመድኒተዓለም ሥራ ምንኛ ከሁሉ የበለጠ አስተዋጽኦ እንዳበረከተች የሚያሳይ ነው፡፡EDA 119.1