Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  በፍቅር የተሰጠ ትምህርት

  የሱስ ደቀ መዛሙርቱን ደጋግሞ አረጋገጠላቸው፤ አስጠነቀቃቸው ለየት ያለ ትኩረትና ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን አስረዳ ነገር ግን ዮሐንስና ጴጥሮስ ከእርሱ አለሸሹም፡፡ እነሱ ግን ማሳሰቢያውን ከምንም ሳይቆጥሩ ከየሱስ ጋር ለመቆየት መረጡ፡፡ መድኃኔአለምም ስህተት አለባቸው ብሎ አልተለያቸውም፡፡ ሰዎችን ባሉበት ደረጃ ከነስህተታቸው ከነድክመታቸው እንዳሉ ነው የሚቀበላቸው፡፡ ከዚያ በኋላ ለርሱ አገልግሎት እነሱም የሚፈቅዱ ከሆነ በርሱ ይገራል ሥርዓት ይይዛሉ ይማራሉም፡፡EDA 99.4

  ነገር ግን ካሥራ ሁለቱ መካከል ለአንዱ ሥራውን እስከሚጨርስ ድረስ አንድም ቃል በቀጥታ ያላነጋገረው ሰው ነበር፡፡EDA 100.1

  በይሁዳ ምክንያት በደቀ መዛሙርቱ መካከል የቅራኔ ነገር ተነስቶ ነበር፡፡ ራሱን ከየሱስ ጋር በማገናኘት በክርስቶስ ባህሪና ሕይወት መሳቡን አሳይቷል፡፡ በሕይወቱ ውስጥ ታላቅ ለውጥ እንዲታይ ፈልጓል፡፡ ይኸንንም ከየሱስ ጋር አንድነት በመፍጠር በኑሮው ላይ እንደሚታይለተ ተስፋ አድርጓል፡፡ ነገር ግን ይህ ምኞት በሕይወቱ ውስጥ ብጐ በጸዕኖ ላያሳድር አልቻለም፡፡ ለካስ አዕምሮውን የገዛው ተስፋ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ መንግሥት ቢያቋቁም በዚያ መንግሥት ውስጥ ሊያገኝ የሚችለውን ዓለማዊ የግል ጥቅም ነበር የሚያስበው፡፡ የክርስቶስን ፍቅር መለኮታዊነት ቢያውቅም የበላይነቱን አምኖ ራሱን አላስገዛም ነበር፡፡ የራሱን ግምትና ሀሳብ ብቻ በመውደድ ለመተቸትና ለማውገዝ ፈንጠር ማለትን ፈለገ፡፡ የክርስቶስ ፍላጐቶችና እንቅስቃሴዎች ዘወትር ከእሱ ማስተዋል በላይ ነበሩ፡፡በጥርጣሬና ውድቅ በሚሆን ሀሳብ መደንገጥና የራሱ ጥያቄዎችና ምኞቶች ለደቀመዛሙርቱ በዘዴ የቅሬታ መንገድ ከፈተ፡፡ ለስልጣን ሽሚያ በሆዳቹው ካመቋቸው ሐሳቦች አብዛኞቹ በክርስቶስ የአሠራር ዘዴዎች ላይ ከነበሯቸው ቅሬታዎች ብዙዎቹ ከይሁዳ የመነጩ ነበሩ፡፡EDA 100.2

  የሱስ ይኸንን የቅራኔ ሽኩቻ አይቶ መነካካት ማለት ማባባስ ስለሚሆን እንዳላየ ተቆጠበ፡፡ እየጠበበ የመጣውን የይሁዳ ራስወዳድነት ሕይወት ራሱን ቤዛ በሚያደርገው ፍቅሩ ሊፈውሰው ፈለገ፡፡ በሚያስተመረው ትምህርት ውስጥ የደቀ መዛሙርቱን የራስወዳድነት ምኞት ከሥሩ የሚነካ መሠረታዊ ሀሳብን ገለጠ፡፡ ካንዱ ትምህርት ቀጥሎ ሌላ ትምህርት ተሰጠ፡፡ እናም ይሁዳ የሱ ጠባይ ስዕልና ሀጢአቱ በግልጽ እየታወቀ መምጣቱን ተገነዘበ፡፡ ነገር ግን አልተመለሰም፡፡EDA 100.3

  የክፋት ግፊት መጨረሻ ካልደረሰ በስተቀር የምህረትን ቃል ሊያሰማው አልቻለም፡፡ ይሁዳ በተሰጠው ተግሳጽ ተቆጥቶና አኩርፎ የምኞት ሕልሙን ግልጽ አወጣው፡፡ ነፍሱ ለገንዘብ በመቋመጥ ባዕድ አምልኮ ተንሰፍስፎ ጌታውን ለመሸዋ ወሰነ፡፡ ከዚያ የጌታ ራት ማዕድ ክርስቶስ በተገኘበት፤ የማይሞት የተስፋ ብርሃን ካለበት ቦታ ተነስቶ ወደክፉ ሥራው ሄደ ወደ ከባድ ጨለማ ተስፋ ወደሌለበት፡፡EDA 101.1

  «እየሱስም የሚያምኑት እነማን እንደሆኑ አሳልፎ የሚሰጠው ማን እንደሆነ ከመጀመሪያ ያውቅ ነበርና፡፡» ዮሐ 6፡64 ሁሉንም እያወቀ አንዳችም የምህረት ወይም የፍቅር ስጦታ አልከለከለም ወይም አልቆጠበም፡፡EDA 101.2

  የይሁዳን አደገኛነት እያየ ወደራሱ አስጠጋው፡፡ ለራሱ ከተመረጡት ታማኝ ደቀመዛሙርት መካከል አስገባው፡፡ በርሱ ልብ ላይ የሚወድቀው ሸክም ከቀን ወደ ቀን እየከበደ ሲሄድ ከዚያ ክፉ ተጠራጣሪና የመሠሪነት የተንኮል ሐሳብ የሚያሰላስል መንፈስ ከነበረው ሰው ጋር እየቆሰለ፤ በነበረው ያላቋረጠ ግንኙት ያንን ተከታታይ ሚስጥራዊና ሪቂቅ የተንኮል ቅራኔ በደቀ መዛሙርቱ ፊት ግልጽ አውጥቶ አፍረጥርጦታል፡፡ ይህ ሁሉ ለዚያች በአደጋ ለተከበበች ነፍስ አዳኝ ከሆነ ስበት ሁሉ አንዱም እንዳያመልጣት ለማድረግ ነበር፡፡EDA 101.3

  «ብዙ ውሃ የፍቅርን ያክል አይስተካከላትም፡፡
  ጐርፍም ሊያሰጥማት አይችልም፡፡
  ፍቅር የሞትን ያክል ብርቱ ናት፡፡» መኃልየ መኃሌይ 8፡76
  EDA 101.4

  እንግዲህ ይሁዳን ራሱን በተመለከተ የክርስቶስ የፍቅር ሥራ ያለጥቅም ዋለ፡፡ ነገር ግን ይህ ደቀ መዛሙርቱን የሚመለከት አልነበረም፡፡ ለእነሱ የእድሜ ልክ የሚስብ ትምህርት ነበር፡፡ የፍቅርና ብዙ ስቃይን የመታገስ ምሳሌነቱ ከሚፈተኑና ከሚሳሳቱ ሰዎች ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት ለዘላለም እንዲቀርጽላቸው ነበር፡፡ ሌላም ትምህርት ነበረው፡፡ አሥራ ሁለቱ ተመርጠው እንደታጩ ደቀ መዛሙርቱ ይሁዳ ከርሱ እንደአንዱ እንዲሆን ትልቅ ምኞት ነበራቸው፡፡ የእሱ እድገትም ለሀዋሪያት ቡድን አንድ ትልቅ ተስፋ እንደሚሆን ቆጥረውት ነበር፡፡ እርሱ ግን ግንኙነቱን ወደእነሱ ከማድረግ ይልቅ ይበልጥ ወደዓለም አዘነበለ፡፡ ከሰዎች ጋር ሲገናኝ የትልቅ ሰው አቀራረብ ነበረው፡፡ ለየት ማለትና የአፈፃፀም ችሎታ የነበረው ሲሆን የራሱን ብቃት ከፍ አድርጐ በመገመት ደቀ መዛሙርቱም በዚያ መልክ እንዲያዩት እምነት አሳድሮባቸዋል፡፡ ነገር ግን ወደክርስቶስ ሥራ ውስጥ አስገብቶ ሊያስተዋውቅ የፈለጋቸው ዘዴዎች በዓለማዊ መሠረተ ሀሳቦች ላይ የተመሠረቱና በዓለማዊ ፖሊሲዎች ሥር የሆኑ ነበሩ፡፡ ዓለማዊ ዕውቅናና ክብርን የሚያስጠብቁ፣ በዚህ ዓለም ለሚኖር መንግሥት የሚሰጡ ዓይነቶች ነበሩ፡፡ በይሁዳ ሕይወት ውስጥ የታዩት የእነኝህ ፍላጐቶች ተግባራዊ እንቅስቃሴ፣ ደቀመዛሙርቱ ለራስ ሀብት በማጋበስ መርሆዎችና በመንፈሳዊ ግዛት ውስጥ የሚኖር የክርስቶስ ሰብዓዊ የሆነና ራስን ለመስዋዕትነት በሚዘጋጀው መርህ መካከል ያለውን ቅራኔ እንዲያስተውሉ ረድቷቸዋል፡፡ በይሁዳ እጣ ራስን ብቻ ማገልገል መጨረሻው ወደምን እንደሚያደርስ አዩ፡፡EDA 101.5

  ለእነኝህ ደቀመዛሙርት የክርስቶስ አጠቃላይ የተልዕኮው ዓላማ ተፈፀመ፡፡ ትንሽ በትንሽ የርሱ ምሳሌዎችና የርሱ ራስን መስዋዕት በማድረግ ትምህርት ጠባያቸውን አርቀው፡፡ የእርሱ ሞት እነሱ ያሰቡት የነበረውን ዓለማዊ ታላቅነት ተስፋ አስቆረጣቸው፡፡ የጴጥሮስ ውድቀትና የይሁዳ አመጽ፤ እነሱ ራሳቸው ክርስቶስ በከባድ ፈተናና መከራ ላይ በሆነ ጊዜ ጥለው መጥፋት በራስ የመተማመንን ስሜት አጠፋባቸው፡፡ የራሳቸውን ድክመት ተመለከቱ፡፡ የተጣለባቸው ኃላፊነት ምን ያክል ትልቅ እንደሆነ ተገነዘቡ፡፡ በእያንዳንዱ እርምጃቸውም የጌታቸው እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተሰማቸው፡፡EDA 102.1

  ከእንግዲህ እርሱ በአካል አጠገባቸው እንደማይገኝ አወቁ፡፡ ከዚህ በፊት ያልተገነዘቡት አንድ ነገር አሁን አስተዋሉ፡፡ እሱም ከእግዚአብሔር ልዑክ ጋር መነጋገር አብሮ መጓዝ እጅግ ታላቅ እድል እንደነበረ መገንዘባቸው ነው፡፡ እርሱ ከሰጣቸው ትምህርቶች አብዛኞቹ እርሱ በሚያስተምርበት ሰዓት ያላደነቋቸው ወይም ከነጭራሹ ያላስተዋሉአቸው አሁን ወደኋላ ተመልሰው ሊያስታውሷቸው ወይም ቃሉን እንደገና ለመስማት ናፈቁ፡፡ አሁን የርሱን ማረጋገጫ ቢያገኙና ቢመጣላቸው ምን ያክል በተደሰቱ ነበር፡፡EDA 103.1

  «እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል፡፡ እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ፡፡» «ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቃችኋለሁ፡፡» «አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል፡፡ እኔም የነገርኳችሁን ሁሉ ያስታውሳችኋል፡፡» ዮሐ 16፡7 ምዕ 15፡15 ምዕ 14፡26EDA 103.2

  «ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፡፡» «የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፡፡ አሁን ልትሸከሙት አትችሉም ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፡፡ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል፡፡» ዮሐ 16፡15 1314EDA 103.3

  ደቀ መዛሙርቱ ክርስቶስ በኦሌቭ ተራራ ላይ ከመካከላቸው ተነስቶ ወደላይ ሲያርግ ተመለከቱ፡፡ ሰማይም እርሱን እንደተቀበለችው እርሱ ሲለያቸው በገባላቸው ቃል መሠረት ወዲያውኑ «እነሆም እኔ እስከዓለም ፍፃሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋራ ነኝ፡፡» አላቸው፡፡ ማቴ 28፡20EDA 103.4

  የርሱ ርህራሄና ሀዘኔታ አሁንም ከእነርሱ ጋር እንደሆነ አወቁ፡፡ በእግዚአብሔር ዙፋን አጠገብ አንድ ተወካይ ጠበቃ እንዳላቸው አወቁ፡፡ በየሱስ ስም እርሱ የተናገረውን ቃል በመድገም ልመናቸውን አቀረቡ፡፡ «እውነት እላችኋለሁ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል፡፡» ዮሐ 16፡23EDA 104.1

  የእምነት እጆቻቸውን እጅግ ከባድ በሆነ ሙግት ወደላይ ከፍ ከፍ አደረጉ፡፡ «የሞተው፤ ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለኛ የሚማለደው ክርስቶስ የሱስ ነው፡፡« ሮሜ 8፡34EDA 104.2

  ቃሉን አክባሪ የሆነው፣ መለኮታዊ የሆነው፣ በሰማይ አደባባዮች ከፍ ያለው፣ በምድር ላሉ ተከታዮቹ ከምላቱ አካፈላቸው፡፡ ከእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ መቀመጡ መንፈስ ቅዱስን ለደቀ መዛሙርቱ ወዲያውኑ በማውረዱ ታወቀ፡፡EDA 104.3

  በክርስቶስ ሥራ እነኝህ ደቀ መዛሙርት የመንፈስ ቅዱስ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተረድተዋል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ትምህርት አማካይነት ደግሞ ለእድሜ ልክ ሥራ የሚጠቅማቸውን የመጨረሻ ዝግጅት አደረጉ፡፡EDA 104.4

  ከዚያ በኋላ ያልሰለጠነ መሐይም ሆነው አልቀሩም፡፡ ከዚያ በኋላ እንደፈለጉ በየግላቸው ቡድን የሚፈጥሩ ወይም በሻከረ የጭቅጭቅ ግንኙነት የሚጣሉ ሰዎች በመሆን አልቀጠሉም፡፡ ከዚያ በኋላ ተስፋዎቻቸው ሁሉ በዓለማዊ ታላቅነት ላይ የተመሠረቱ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ «በአንድነት ተስማሙ፡፡» በአንድ አእምሮና በአንድ ነፍስ ሆኑ፡፡ ክርስቶስ ሀሳባቸውን ሞላላቸው፡፡ ዓለማቸው ሁሉ የርሱን ግዛት በማስፋፋት ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር፡፡ በአእምሮና በባህሪ የጌታቸውን አምሳል ይዘው ነበር፡፡ ሰዎችም «እነዚህ ከክርስቶስ ጋር እንደነበሩ ተገነዘቡ፡፡» የሐዋ ሥራ 4፡13EDA 104.5

  ከዚያ በኋላ ሟች በሆነ ፍጡር ሰው ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የክርስቶስ ክብር ተገለጠ፡፡ ከዚያ በፊት ስሙን ይጠሉና አጥብቀው በመቃወም ኃይሉንም ይንቁ የነበሩ ብዙ ሰዎች የተሰቀለው ጌታ ተከታዮች መሆናቸውን ተናዘዙ፡፡ በመለኮታዊ መንፈስ ትብብር የእነኝህ ክርስቶስ የመረጣቸው ትሁት ሰዎች ሥራ ዓለምን ገለባበጠው፡፡ በአንድ ትውልድ ጊዜ ውስጥ ከሰማይ በታች ላለ እያንዳንዱ ሕዝብ በሙሉ ተዳረሰ፡፡EDA 105.1

  በርሱ ምትክ ለረዳት ተባባሪ ሠራተኞቹ መመሪያ እንዲሰጣቸው የተላከው ክርስቶስ ለዛሬዎቹ ተባባሪ ሠራተኞቹም ያስተምራቸው ዘንድ መንፈስ ቅዱስን ሰየመላቸው፡፡ «እኔ እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡» ነው የሚለው የገባው የተስፋ ቃል፡፡EDA 105.2

  በዛሬው የትምህርት ሥራም የዚሁ መሪ በቦታው መገኘት ያንኑ የጥንቱን ዓይነት ውጤት ያስገኛል፡፡ እውነተኛ ትምህርት መጨረሻ ላይ የሚያዘነብለው ወደዚሁ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንዲከናወን የሚፈልገው የሥራ ዓይነትም ይኸው ነው፡፡EDA 105.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents