Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    «ባለፈው ሌሊት እኔ በዚያ ስብሰባ ነበርሁ» አለ፡፡

    «ባለፈው ሌሊት ነውን?» ስትል ሲስተር ኋይት ተናገረች፤ «ያውም ባለፈው ሌሊት ነውን? በራእይ ታይቶኝ በነበረ ጊዜ ስብሰባው ከብዙ ወራት በፊት የሆነ መስሎኝ ነበር፡፡»CCh 27.6

    «እኔ ባለፈው ሌሊት በዚያው ስብሰባ ውስጥ ነበርሁ» አለ ፤ «በወረቀቱ ውስጥ ስላለው አርቲክልስ እያመለከትሁ እራሴ ላይ ይዤ የነበርሁ እኔው ነኝ፡፡ በሥህተት ጐዳና ላይ ነበርሁ በማለቴ አዝናለሁ ፤ ግን ራሴን በቀና ጐዳና አስቀምጥ ዘንድ ይህን ምቹ ጊዜ እወስዳለሁ»፡፡ ከዚያ በኋላ ተቀመጠ፡፡CCh 27.7

    ሌላው ሰው ሊናገር ብድግ አለ፡፡ እርሱም የረሊጅየስ ሊበርቲ አሶሲየሺን ፕሬዚዳንት ነበር፡፡ ያለውን ቃላት እስቲ ልብ በለው ፤ «እኔ ባለፈው ሌሊት በዚያ ስብሰባ ውስጥ ነበርሁ ፤ ኮንፈረንሱ (ስብሰባው) ካበቃ በኋላ ጥቂቶቻችን በክፍሌ ውስጥ በሬቪው ቢሮ ተገናኘንና እዚያ ከውስጥ ዝግት አድርገን ነገሩን አንስተን በዚህ ጧት የቀረቡልንን ጥያቄዎች ጉዳይ ተከራከርንበት (ተነጋገርንበት)፡፡ በዚያው ክፍል ውስጥ በዚህ ጧት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ቆየን፡፡ ስለሆነው ነገርና በክፍሉ ስላሉት ግላዊ አስተያየት ማስረጃ ለመስጠት መጀመር የሚገባኝ ብሆን ልክ በሲስተር ኋይት እንደተሰጠው አድርጌ አስተካክዬ ልሰጥ አይቻለኝም ነበር፡፡ አሁን በሥህተት ላይ እንደነበርሁና የወሰድሁትም እርምጃ ልክ አለመሆኑን አያለሁ፡፡ በዚህ ጧት ከተሰጠው ብርሃን ጋር ሳስተያይ በስህተት ላይ መሆኔን አውቃለሁ»፡፡CCh 27.8

    ሌሎችም በዚያን ቀን ተናገሩ፡፡ ባለፈው ሌሊት በስብሰባው የነበረ ሰው ሁሉ ብድግ አለና መስክርነቱን ሰጠ፤ ዔሌን ኋይት ስለ ስብሰባውና በክፍሉ ውስጥ ስለነበሩትም አስተያየት በትክክል እንዳመለከተች ተናገረ፡፡ ይህም ስብሰባ በዚያው የእሁድ ጧት ከመዘጋቱ (ከማብቃቱ) በፊት የረሊጅየስ ሊበርቲ ሰዎች ጓድ ባንድነት ተጠሩና ከአምስት ሰዓታት በፊት ብቻ የወሰኑትን ውሳኔ ሻሩ፡፡CCh 28.1

    «ሚስስ ኋይት ባትታገድና (ባትከለከልና) ራእዩን በሰንበት በቀትር በላይ ተናግራ ብትሆን ኑሮ ስብሰባው ገና አልተደረገም ነበርና መልእክቷ እግዚአብሔር ላሰበው ሐሳብ ባልጠቀመ ነበር፡፡CCh 28.2

    የሆነ ሆኖ ሰዎቹ በሰንበት ከቀትር በላይ የተሰጠውን ጠቅላላ ምክር እንዲሁ መሆኑን አልተቀበሉትም ፡፡ የተሻለውን እናውቃለን ብለው አስበው ነበር፡፡ ዛሬ አንዳንዶች «ምናልባት ሲስተር ኋይት አላስተዋለችም» ፤ ወይም «አሁን በልዩ ቀናት ነው የምንኖር” ወይንም «ያ ምክር ከብዙ ዓመታት በፊት ለነበሩት የሚሆን ነው ፤ አሁን ግን የሚስማማ አይደለም” እያሉ እንደሚያስቡ ፤ እነሱም ምናልባት አስበው ይሆናል፡፡ በነዚህ ቀናት ሰይጣን የሚያሾከሽክብን ሐሳብ ያው በ፲፰፻፺፩ ዓ.ም ሰዎችን የፈተነበት ነው፡፡ አምላክ በየጊዜውና በገዛ ራሱ ጐዳና ሥራው እንደሆነ ገለጸ ፤ እርሱ ይመራ ይጠብቅም ነበር ፤ እጆቹንም በመንኰራኩሩ ላይ ያደረገው እርሱ ነበር፡፡ ዔሌን ኋይት «የርሱ ጣልቃ ገቢነት (ረዳትነት) ይታወቅ ዘንድ እግዚአብሔር ነገሮቹን ብዙ ጊዜ በመከራ ውስጥ እንዲሆኑ ፈቅዶአል ፤ እንግዲህ እርሱ አምላክ በእሥራኤል እንዳለ ገልጾአል” ፤ ስትል ትነግረናለች፡፡CCh 28.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents