Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    እርስ፣ በርሳችሁ ትዋደዱ፡ ዘንድ ፡ እኔ እንደ ወደድኋችሁ፡፡

    እግዚአብሔር ለሰዎች ደህንነት ከሥራው ፈንታውን አድርጎአል አሁንም ለቤተ ክርስቲያኑ ትብብር የሚጠራ ነው፡፡ ባንድ በኩል የክርስቶስ ደም የእውነት ቃል መንፈስ ቅዱስ አሉ፤ በሌላው በኩል የሚጠፉ ነፍሳት አሉ፡፡ የክርስቶስ ተከታይ ሁሉ ሰማይ ያሰናዳለትን በረከቶች ሰዎች እንዲቀበሉ ሊያመጣላቸው የሚያደርገው ፈንታ አለው፡፡ እንግዲህ ራሳችንን አጥብቀን እንመርምርና ይህን ስራ አድርገን እንደሆን እንይ ሐሳባችንንና የሕይወታችንን አድራጎት ሁሉ እንጠያይቅ፡፡CCh 119.1

    በአእምሮዋችን አዳራሾች ውስጥ የተሰቀሉ ደስ የማያሰኙ ብዙዎች ስዕሎች ያሉ አይደሉምንአ የየሱስን ይቅርታ ብዚ ጊዜ አስፈልጎሃል፡፡ በርሱ ርሀራኄና ፍቅር ዘወትር የምታመን ኑርሃል፡፡ ሆኖም ከርስቶስ ያከባከበህን መንፈስ ለሌሎች ሳትገልጽ አልቀረህምንአ በተከለከሉት መንገዶች ውስጥ ደፍሮ ሲሔድ ላየኸው ሸክም ተሰምቶሃልንተ በቸርነት መክረኸዋልንመ ለርሰ አልቀሰህ ከርሱም ጋር ለርሱም ጸልየሃልንጸ እንደምትወደውና ልታድነው፤ እንደምትፈልግ በርህራኄ ቃላትና በቸርነት አድራጎት አሳይተሃልንአCCh 119.2

    በገዛ ጠባያቸው ድክመትና የስህተት ልምዳቸው ሸክም ሥር ሲናቀፉና ሱንገደገዱ ከነበሩት ጋር ሳለህ እርዳታ ልትሰጣቸው ስትችል ጦርነቱን ብቻቸውን እንዲዋጉ ትተሃቸዋልንት ዓለም ሲራራላቸውና ወደ ሰይጣን ወጥመዶች /መርበቦች/ ሊስባቸው ዝግጁ ሆኖ ሳለ እነዚህን በኃይል የተፈተኑትን ሰዎች በሌላ ወገን አልፈሃቸዋል አልሔድህምንአ እንደ ቃየል፤ ‹እኔ የወንድሜ ጠባቂውን ነኝ› ለማለት ዝግጁ አልነበርህምንአ እንደ ቃየል፤‹ እኔ የወንደሜ ጠባቂውን ነኝ› ለማለት ዝግጁ አልነበርህምንአ ዘፍጥረት ፬፡፬፡፡CCh 119.3

    ታላቁ የቤተ ክርስቲያን ራስ የሕይወትህን ሥራ እንደምን ሊመለከት አለበት ነፍስ ሁሉ ለርሱ ክቡር የደሙ ግዢ የሆነው ከቀና መንገድ የሚርቁትን ችላ ማለትህን እንደምን ይምለከትብህ ይሆንይ እነሱን እንደምትተዋቸው አንተንም እንደሚተውህ አትፈራምን; ያምላክ ቤት እውነተኛ ጠባቂ የሆነው ችላባይነትህን ሁሉ እንዳመለከተብህ እርግጠኛ ሁን፡፡CCh 119.4

    ያለፈውን ችላ ባይነትህን በማቃናት ጊዜው ገና በጣም አላለፈም፡፡ የመጀመሪያው ፍቅር፤ የመጀመሪያው ግለት መነቃቃት ..(ሪቫይቫል)ይሁንልህ ያራቅሃቸውን ፈልጋቸው፤ የቆሰልኸውንም ቁስሎች በኑዛዜ እሠረው፡፡ ወደ ታላቁ የሚራራ የፍቅር ልብ ቀረብ በል፤ ያ የአምላክ ርህራኄ ምንጭ ወደ ልብህ ፈስሶ፤ ካንተም ወደ ሌሎች ይፍሰስ፡፡ የሱስ በገዛ ክቡር ሕይወቱ የገለጸው ርህራኄና ምሕረት በጓድ ፍጡሮች በተለይም በክርስቶስ ወንድሞቻችን ለሆኑት በምናደርግላቸው አኳኋን ምሳሌ ይሁንልን፡፡ አንድ የቸርነት የደስታና የማደፋፈሪያ ቃል ለማሸነፍ የበረታታቸው የነበሩት በታላቁ የሕይወት ተጋድሎ ብዙዎች ዝለው ተስፋ ቆርጠዋል፡፡ እንግዲህ የተስፋራራህ፤ የቀዘቀዝህ የማትራራና ነቃፊ ከቶ አትሁን፡፡ ለማደፋፈር ተስፋንም ለማነቃቃት አንዲት ቃል ለመናገር ምቹ ጊዜ አትጣ፡፡ በርህራኄ የምንናገራቸው ቃላት አንዳች ሸክም ለማቅለል የምናደርጋቸው የክርስቶስን መሳይ ጥረቶቻችን እንደምን በጣም የሚስፋፉ መሆናቸው ልንናገር አንችልም፡፡ በቸርነት በገራምነትና በርህራኄ ፍቅር በቀር የተሳሳተው በምንም ሌላ መንገድ ሊመለስ አይቻልም፡፡35T 610-618;.CCh 119.5