Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ክርስቶስ ካገር ወገኘ ጋር (ከተወላጅ ጋር) የነበረው ግንኙነት፡፡

    ክርስቶስ የወገን የማዕረግ ወይም የሃይማኖትን ልዩነት አልተቀበለም፡፡ ጸሐፎችና ፈሪሳውያን በዓለም ውስጥ ያለውን የተቀረውን ያምላክ ቤተሰብ አስወግደው የሰማይን ሥጦታዎች ሁሉ ያንድ ክፍለ አገርና ብሔራዊ ጥቅማቸው ለማድረግ ፈልገው ነበር፡፡ ክርስቶስ ግን የልዩነትን ግድግዳ ለማፍረስ መጣ፡፡ የምሕረቱና የፍቅሩ ሥጦታ እንደ አየር እንደ ብርሃን ወይም ምድርን እንደሚያረኩ (እንደሚያለመልሙ) የዝናቡ ጎርፎች ያልተወሰነ መሆኑን ለማሳየት መጣ፡፡CCh 131.1

    የክርስቶስ ሕይወት የዘር ልዩነት የሌለበትን ሃይማኖት አቋቋመ ይኸውም ሃይማኖት አይሁድና አሕዛብ ነፃ የሆነውም አገልጋይም በአምላክ ፊት እኩል ሆነው በተለመደው ወንድማማችነት የሚቆራኙበት ነው፡፡ የሥነ ሥርዓት (የፖሊሲ) ጥያቄ እንቅስቃሴውን አላናጋበትም፡፡ በጎረቤቶችና እንግዶች በወዳጆችና ጠላቶች መኻከል ምንም ልዩነት አላደረገም፡፡ ለልቡ የተማፀነው ለሕይወት ውሃ የተጠማ ነፍስ ነበር፡፡CCh 131.2

    ሰብዓዊ ፍጥረት እርባና ቢስ ነው በማለት አላለፈውም ነገር ግን ለነፍስ ሁሉ የሚፈውስ መድኃኒት ሊያደርግለት ፈለገ፡፡ ራሱን ባገኘበት ሕብረተሰብ ለጊዜውና ለሁኔታው (ለነገሩ) ትክክለኛ የሆነውን ትምህርት አቀረበ፡፡ ሰዎች በጓድ ሰዎቻቸው ላይ ያሳዩት ችላ ባይነትና ስድብ የመለኮትነቱን ሰብዓዊ ርህራኄ የሚያስፈልጋቸው መሆኑነ በይበልጥ እንዲያውቅ ብቻ አደረገው፡፡ ነውር የሌላቸውና የማይጎዱ እንዲሆኑና የእግዚአብሄር ልጆች የሚያደርጋቸውን ጠባይ እንዲያገኙ ማረጋገጫ እፊታቸው እያቀረበ እጅግ ጨምጋጎች የሆኑትንና ተስፋ የሌላቸውን በተስፋ ሊያነቃቃ ፈለገ፡፡ 29T190; 191;CCh 131.3

    የእግዚአብሔር ልጆች በክርስቶስ አንድ ስለሆኑ ለቀለም ልዩነት ለዘር፣ ለማዕረግ፣ ለሐብት፣ ለውልደት ወይም ለከፍተና ማዕረግ ብሎ የሱስ የዘርን ልዩነት፣ የማሕበርን ልዩነት፣ ሰው ጓዱ ከሆነው ሰው መለያየትን እንደምን ሊመለከት ይችላል( የኅብረት ምሥጢር ምዕመናን በክርስቶስ እኩል በመሆናቸው ይገኛል፡፡3RH 22 I 1891 CCh 131.4