Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፲፱—ክርስቲያኖች ያምላክን አርአያ ማሳየት አለባቸው፡፡

    በሕዝቡ አማካይነት የመንግሥቱን ፕሪንሲፕል (ሥርዓት) ለመግለጽ ያምላክ ሐሳብ ነው፡፡ ይህንኑ ፕሪንስፕል በሕይወታቸውና በጠባያቸው ይገለጹ ዘንድ ከዓለም ልማዶች፤ ባህሎችና ዓመሎች ሊለያቸው ይፈልጋል፡፡ ፈቃዱንም ያስታውቃቸው ዘንድ ወደራሱ ሊያቀርባቸው ይሻል፡፡CCh 138.1

    ዛሬ እግዚአብሔር በሕዝቡ አማካይነት ሊፈጽም የሚፈልገው ሐሳብ ፤ ከምድረ ግብፅ እሥራኤልን ባወጣ ጊዜ በእሥራኤል አማካይነት ሊፈጽም በፈለገበት በዚያው ሐሳብ ነው፡፡CCh 138.2

    በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የተገለጸውን ያምላክን ቸርነት ፤ ምሕረት ፤ ጽድቅና ፍቅር በመመልከት ዓለም የጠባዩ አርአያ ሊያገኝ አለበት፡፡ ያምላክ ሕግ፤ በእንዲህ በሕይወት የተሰተፈው አርአያ ያለበት ሲሆን፤ ዓለም እንኳ በምድር ካሉት ሌላው ሕዝብ ሁሉ በላይ አምላክን የሚያፈቅሩትን የሚፈሩትንና የሚያገለግሉትን ብልጫነታቸውን ይገነዘባል፡፡CCh 138.3

    ጌታ ዓይኑ በሕዝቡ ሁሉ ላይ ነው፤ ለእያንዳንዱም የራሱ እቅዶች አሉት፡፡ የተቀደሱትን ትእዛዞቹን የሚጠብቁ የተለየ ሕዝብ እንዲሆኑ ሐሳቡ ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አነቃቂነት በሙሴ የተጻፉት ቃላት ለጥንታዊ እሥራኤልም ሆነ ለዛሬ ያምላክ ልጆች የሚሆኑ ናቸው፡፡ «አንተ ለእግዚአብሔር ላምላክኸ የተቀደሰ ሕዝብ ነኸና፡፡ አንተንም መረጠ እግዚአብሔር አምላክኸ የተወደደ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ በምድር ፊት ከሚኖሩ ከአሕዛብ ሁሉ መኻከል»፡፡ ዘዳግ ፯ ፡ ፮፡፡ ፩16T912;CCh 138.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents