ኅብረትን ለማስገኘት የተሰጠ መግለጫ፡፡
ከብዙ ዓመታት በፊት በተሎ በሚመጣው የክርስቶስ መምጫ የሚያምኑ ጓድ ምዕመናን በጣም ጥቂቶች በነበሩበት ወቅት በቶፕስሐም ሜይን የነበሩ ሰንበት ጠባቂዎች በወንድም ስቶክብሪጅ ሆውላንድ ቤት በትልቅ ማዕድ ቤት ውስጥ ለጸሎት ተገናኙ፡፡ አንድ ጊዜ በሰንበት ጧት ወንድም ሆውላንድ አልነበሩም፡፡ እርሳቸው ሁልጊዜ በጊዜ የሚገኙ ስለ ነበሩ በዚህ ተገረምን፡፡ ወዲያው ገባ አሉ እፊታቸው የሸበረቀ ሁኖ በአምላክ ክብር በርቶ ነበር፡፡ ‹‹ወንድሞቼ›› አሉ ‹‹እኔ አግኝቸዋለሁ ያምላክ ቃል ዋስትና ሁኖ የተሰጠን ‹‹ከቶ አትወድቁም›› በሚለው ረገድ የምግባር እርምጃ መሆኑን አግኝቻለሁ ስለርሱም ልነግራችሁ ነኝ››፡፡CCh 131.5
ከዚያም በኋላ አንድ ወንድም ድሃ አሣ አጽማጅ እንደሚገባ ከፍ ያለ ከበሬታ እንዳልተሰጠውና ወንድም ሆውላንድና ሌሎች ራሳቸው ከርሱ በላይ እንደሆኑ እንዳሰቡ ይሰማው የነበረ መሆኑን ልብ እንዳደረጉ ነገሩን፡፡ ነገር ግን ይህ እውነት አልነበረም ዳሩ ግን ለርሱ እውነት መስሎት ነበር ለአያሌ ሳምንታትም ወደ ጸሎት ስብሰባዎች አልሔደም ነበር፡፡ ስለዚህ ወንድም ሆውላንድ ወደ ቤቱ ሔዱና በፊቱ ተንበርክከው ‹‹ወንድሜ ይቅር በለኝ›› አሉት ምንስ አድርጌአለሁ ሰውዬው ክንዳቸውን ይዞ ብድግ ሊያደርጋቸው ሞከረ፡፡ ‹‹የለም›› አሉ ወንድም ሆውላንድ በኔ ላይ ምን ቅያሜ አለህ››( ‹‹ምንም ቅያሜ በርስዎ ላይ የለኝም›› አለ፡፡ ‹‹ነገር ግን ይኖርሃል›› አሉ ወንድም ሆውላንድ አንድ ጊዜ እርስበርሳችን ልንነጋገር እንችል ነበር አሁን ግን ጨርሶ አትነጋገረኝም ነገሩ ምን እንደሆነ ላውቅ እፈልጋለሁ››፡፡CCh 131.6
‹‹ብድግ ይበሉ ወንድም ሆውላንድ›› አለ፡፡ ‹‹የለም›› አሉ ወንድም ሆውላንድ ‹‹ብድግ አልልም›› ‹‹እንግዲውያ እኔ ዝቅ ማለት አለብኝ›› አለ እርሱም በጉልበቱ ተንበርክኮ እንደምን የልጅነት ሥራ እንዳደረገና እንዴት ያለ ብዙ ክፉ ሐሳቦች እንደ ወደደ ተናዘዘ እንግዲህ አለ አሁን ‹‹አስወግዳቸዋለሁ››፡፡CCh 132.1
ወንድም ሆውላንድ ይህን ታሪክ ሲነግሩዋቸው ፊታቸው በአምላክ ክብር በርቶ ነበር፡፡ ነግግራቸውንም እንደፈጸሙ አሣ አጽማጁና ቤተሰቡ መጡ እጅግም ጥሩ የሆነ ስብሰባ ነበረን፡፡CCh 132.2
ወንድም ሆውላንድ የተከተሉትን እርምጃ አንዳንዶቻችን እንከተል ይሆናል፡፡ ወንድሞቻችን ክፉ ቢያስቡብን ወደነሱ ሔደን ‹‹ልጎዳችሁ ማናቸውንም ነገር አድርጌ እንደሆን ይቅር በሉኝ›› ብንላቸው የሰይጣንን ተንኮል ሰብረን ወንሞቻችንን ከፈተናዎቻቸው ነጻ እናወጣቸዋለን፡፡ ባንተና በወንድሞችህ መኻከል ማንኛውም ነገር ጣልቃ እንዲገባ አትፍቀድ፡፡ የጥርጣሬን ጥራጊ (ቆሻሻ) በመሥዋዕት ለማጣራት የምትችል ማናቸውም ነገር እንዳለ አድርገው፡፡ እግዚአብሔር እርስበርሳችን በወንድማማችነት እንድንዋደድ ይፈልገናል፡፡ የምንተዛዘንና ትሑታን እንድንሆን ይፈልገናል፡፡ ወንድሞቻችን እንደሚወዱን ክርስቶስም እንደሚወደን እናምን ዘንድ ራሳችንን እንድናሰለጥን ይፈልገናል፡፡ ፍቅር ፍቅርን ይወልዳል፡፡CCh 132.3
ወንድሞቻችንን በሰማይ ልንገናኛቸው ተስፋ እናደርጋለንን( እዚህ ከነሱ ጋር በሰላምና በስምምነት ለመኖር የምንችል ከሆን እዚያም ከነሱ ገር ለመኖር እንችላለን፡፡ ግን እዚህ ከነሱ ጋር ዘወትር ሳንጣላና ፀብ ሳይኖረን ለመኖር ባንችል በሰማይ እንደምን ከነሱ ጋር ለመኖር እንችላለን( ከወንድሞቻቸው ለይቶአቸው ወደ ፀብና መለያየት የሚያደርሳቸውን የአድራጎት እርምጃ የሚከተሉ በፍጹም መመለስ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ልባችን በክርስቶስ ፍቅር መቅለትና መገዛት አለበት፡፡ በቀራንዮ መስቀል ላይ ለኛ በመሞቱ ያሳየንን ፍቅር መውደድ አለብን፡፡ ወደ መድኃኒታችን እየተቃረብን መሳብ ያስፈልገናል፡፡ ብዙ ጸሎት ማድረግና ሃይማኖትን ከምግባር ላይ ለማዋል መማር አለብን፡፡ ልበ ርህሩሆች አዛኞችና ትሑታን መሆን አለብን፡፡ በዚህ ዓለም እናልፋለን ግን አንድ ጊዜ ነው፡፡ እንግዲህ አብረናቸው ለምንሆነ የክርስቶስን ጠባይ ልናሳትፍላቸው አንጣጣርምን(CCh 132.4
የደነደነው ልባችን መሰበር ያስፈልገዋል፡፡ ፍጹም በሆነው ኅብረት ባንድነት መሰብሰብ ያስፈልገናል፡፡ የናዝሬቱ የየሱስ ክርስቶስ ደም ግዥ መሆናችን ንም መገንዘብ ያስፈልገናል፡፡ እንግዲህ እያንዳንዳችን እንዲህ እንብ ‹‹እርሱ ሕይወቱን ለኔ ሰጠ በዚህም ዓለም ስሔድ እራሱን ለኔ በመስጠቱ የገለጸውን ፍቅር እንድገልጽ ይፈልግልኛል››፡፡ ክርስቶስ አምላክ ጻድቅ እንደሆነና በርሱ የሚያምኑትን የሚያጸድቅ መሆኑን ለመግለጽ በመስቀል ላይ ኃጢአታችንን በራሱ አካል ላይ ተሸከመ፡፡ ለክርስቶስ የሚገዛ ሁሉ ሕይወት ዘላለማዊ ሕይወት አለው፡፡ CCh 132.5