Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የቅድስና አስረጅዎች ፡፡

    መድኃኒታችን የዓለም ብርሃን ነበር፤ ዓለም ግን አላወቀውም፡፡ እርሱ በሁሉ ጎዳና ላይ ብርሃን እያሰራጨ ዘወትር የምሕረት ሥራ ያደርግ ነበር፡፡ ሆኖም ወደር የሌለውን በጎ ሥራውን፤ ራስን መካዱን ራስን መሠዋቱንና ቸርነቱን ይመለከቱ ዘንድ የተቀላቀላቸውን አላደማቸውም (አልጠራቸውም)፡፡ አይሁዶች እንዲህ ያለውን ሕይወት አላደነቁለትም፡፡ ሃይማኖቱ ከሃይማኖታቸው ደረጃ ጋር ያልተስማማ ስለሆነ የርሱ ሃይማኖት እርባናቢስ እንደሆነ አሰቡ፡፡ ሃይማኖታቸው በገሃድ በሕዝብ ፊት መጸለይ የምጽዋትን ሥራ ማድረግን የሚጠቀልል ነበር፡፡CCh 95.1

    እጅግ ክቡር የሆነው የቅድስና ፍሬ የገርነት ጸጋ ነው፡፡ ይህ ጸጋ በነፍስ ውስጥ ሲኖር የምሳሌነቱ ባሕርይ ይታነጻል፡፡ ዘወትር ጸንቶ አምላክን መጠባበቅና ፈቃድን ለርሱ ማስገዛት ይሆናል፡፡CCh 95.2

    ራስን መካድ፤ ራስን መሠዋት፤ ደግነት፤ ቸርነት፤ ፍቅር፤ ትዕግሥት፤ ጽናትና ክርስቲያናዊ እምነት ከአምላክ ጋር በእውነቱ ግንኙነት የሚያደርጉ የሚያፈሩ ዕለታዊ ፍሬዎች ናቸው፡፡ አድራጊታቸው ለዓለም በይፋ አይገለጽም ይሆናል፡፡ ነገር ግን እነሱ ራሳቸው ከክፉ ጋር ዕለት ዕለት የሚታገሉና በፈተናና በስህተት ላይ የተከበረ ድል እድራጊነትን የሚያገኙ ናቸው፡፡ ከልብ በተጸለየው ጸሎትና ዘወትር በዚሁ ላይ በመትጋት በተገኘው ኃይል አማካይት ጥብቅ የሆኑ ተስፋዎች ይታደሱላቸዋል፤ ይጠበቃሉም፡፡ ብርቱና ትጉህ የሆነ ሰው እንኳ የእነዚህን የጸጥተኞች ሰራተኞች ትግል አያስተውልም፤ ነገር ግን የልብን ምስጢሮች የሚያይ አምላክ በትህትና በገርነት ያደረጉትን ጥረታቸውን ሁሉ እየመሰከረላቸቸው ልብ የሚያደርግና የሚመለከት ነው፡፡ በጠባይ ውስጥ ንጹህ የሆነውን የፍቅርና የሃይማኖት ወርቅ ለመግለጽ የፈተና ጊዜ ያስፈልገዋል፡፡ ፈተናዎችና ብስጭቶች በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ሲደርስ፤ በዚህን ጊዜ የክርስቶስ እውነተኞች ተከታዮች ጽኑ የሆነ ቅናትና የጋለ ፍቅር ይገለጹባቸዋል፡፡CCh 95.3

    ራሱ (እውነተኛ የሆነ ሃይማኖታዊ ሰው) ምንም የማያውቅ ሆኖ ሳለ፤ ወደ አርአያው አካባቢነት የሚመጡ ሁሉ የኖረውን ክርስቲያናዊ ሕይወቱን ውበትና መዓዛ ያያሉ፤ ከዓመሉና ከዝንባሌዎቹ ጋር የሚስማማ ነውና፡፡ እርሱ ለመለኮታዊ ብርሃን የጸልያል፤ በዚያም ብርሃን ውስጥ ለመሔድ ይወዳል፡፡ የሰማያዊ አባቱን ፈቃድ ያደርግ ዘንድ ምግቡና መጠጡ ነው፡፡ ሕይወቱ በእግዚአብሔር በክርስቶስ ውስጥ የተሰወረ ነው፤ ሆኖም እርሱ ስለዚህ ጉራውን አይነዛም፤ እንዲያውም ስለዚሁ የሚያውቅ አይመስልም፡፡ በጌታ እርምጃዎች ቀርበው የሚከተሉትን ትሁታንና ዝቅተኞችን በፈገግታ ይመለከታቸዋል፡፡ መላእክት ወደነሱ ይሳባሉ፡፡ በመንገዳቸውም ላይ ለመቆየት ይወዳሉ፡፡ ከፍተኛ ግብ ላይ ነን በሚሉት ዘንድና መልካም ሥራዎችቸውን ከፍ ለማድረግ በሚደሰቱት ዘንድ ያልተገቡ ሆነው ይታለፉ ይሆናል፤ ነገር ግን ሰማያዊ መላእክት በነሱ ላይ ተጎንብሰው በአካባቢያቸው እንደ እሳት ግንብ ናቸው፡፡ ፯7SL l l— 15;CCh 95.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents