Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሰራተኞቹ የቤተ ክርስቲያንን አባሎች ማሰልጠን፡፡

    የተሰበኩት ስብከቶች ሁሉ ብዙዎችን ራሳቸውን የሚክዱ ሰራተኞች ያላፈሩ መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ እጅግ ጥብቅ የሆኑ ውጤቶች ያሉበት መሆኑን ሊታሰብበት አለበት፡፡ ለዘለዓለም ኑሮዋችን የወደፊት ሁናቴያችን ከሚያሠጋን ላይ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናት ብርሃንን በማሠርጨት ረገድ መክሊቶቻቸውን ሳይጠቀሙበት ስለቀሩ እየጠወለጉ ናቸው፡፡ ሁሉም ብር ሃናቸውን በሥሪ ያውሉ ዘንድ ከጌታ ትምህርቶች የሚሆናቸው የተጠናቀቀ ምክር ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ የቤተክርስቲያናት ተጠባባቂዎች የሆኑ ችሎታ ያላቸውን አባሎት መርጠው ኃላፊነት ሊሰጧቸው ይገባል በዚያኑ ጊዜም እንደምን ደህና አድርገው ሌሎችን ሊያገለግሉና ሊባርኩ እንደሚችሉ ለነሱ ክብር መስጠት ነው፡፡ ፲፬146T431; CCh 66.3

    ሜካኒክ፤ ጠበቆች ነጋዴዎች የንግድና የሥራ ሁሉ ሰዎች የሥራቸው ጌቶች እንዲሆኑ ራሳቸውን ያሠለጥናሉ፡፡ የክርስቶስ ተከተዮች ከነሱ ያነሱ አስተዋዮች ሆነው በአገልግሎቱ ተቀጥረው ሳሉ የተቀጠሩበትን ጐዳናዎችና ዘዴዎች የሚያጡበት /የማያውቁት/ መሆን ይገባቸዋልንይ የዘላለምን ሕይወት የማግኘት ጉዳይ ከምድራዊ ግምት ሁሉ በላይ ነው፡፡ ነፍሳችን ወደ የሱስ ለመግኘት ጉዳይ ከምድራዋ ግምት ሁሉ በላይ ነው፡፡ ነፍሳትን ወደ የሱስ ለመምራት የሰብዓዊ ጠባይን ማወቅና የሰብዓዊ ሐሳብንም ማጥናት የሚገባ ነው፡፡ ታላቁን የእውነት ጉዳይ ይዞ ወደ ወንዶችና ሴቶች እንደምን እንደሚቀረበው ለማወቅ ብዙ የተጠናቀቀ ሐሳብና የጋለ ጸሎት ያስፈልጋል፡፡ ፲፭154T67;CCh 67.1

    ቤተ ክርስቲያኒቱ ወዲያው እንደ ተደራጀች፤ እንደተቋቋመች ሰባኪው (ቄሱ) አባሎችን በሥራ ላይ ያድርጋቸው፡፡ በክንውን እንደምን እንደሚሠሩ ሊማሩ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሰባኪው ከመስበክ ይልቅ የበለጠውን ለማስተማር ጊዜውን ቀድሶ ይስጥ፡፡ ያገኙትን ዕውቀት ለሌሎች እንደምን እንደሚሰጡ ሰዎችን ያስተምር፡፡ አዲሶቹ አማኞች በሥራው ልምምድ ካላቸው ምክር እንዲቀበሉ መማር የሚገባቸው ሱሆን ሰባኪውን በአምላክ ፈንታ እንዳያደርጉ ደግሞ መማር አለባቸው፡፡CCh 67.2

    ለሌሎች ሊሰጥ የሚቻል ታላቁ እርዳታ ለእግዚአብሔር እንዲሠሩና በሰባኪዎቹ ላይ ሳይሆን በርሱ እንዲታመኑ እነሱን ማስተማር ነው፡፡ ክርስቶስ እንደ ሰራ ይሠሩ ዘንድ ይማሩ፡፡ ከሠራተኞች ሠራዊቱ ጋር ሆነው ለርሱ የታመነ አገልግሎት ያድርጉ፡፡ ፲፮167T19, 20;CCh 67.3

    አስተማሮች በሕዝብ መኻከል በመሥራት መንገዱን ይምሩ ሌሎችም ከነሱ ጋር ተባብረው ምሳሌያቸውን ይማራሉ፡ ከብዙ ሕግጋቶች አንዱ ምሳሌ የሚጠቅም (ዋጋ ያለው) ነው፡፡ ፲፯17MH149;CCh 67.4

    በብተ ክርስቲያኒቱ ላይ የመንፈሳዊ ተጠባባቅነት ያላቸው በእግዚአብሔር ሥራ አንዳች ክፍል እንዲያደርግ ለአባል ሁሉ ምቹ ጊዜ የሚሰጥባቸው መንገዶችና ችሎታዎች ማቀድ አለባቸው፡፡ ይህ ባለፈው ሁልጊዜ አልተደረገም በቀለጠፈ አገልግሎት ሁሉም መክሊታቸውን የሚጠቀሙት ፕላን (እቅድ) በምሉ አልታቀላቸውም፡፡ ከዚሁ የተነሣ ምን ያህል እንደጠፋባቸው የሚገነዘቡት ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡CCh 67.5

    በቤተ ክርስቲያኑ መኪሊት አለ፤ ይኸውም የቀና ሥራ ዓይነት ቢሰራበት በዚህ ሥራ ታላክ እርዳታ እንዲሆን ሊያድግ ይቻላል ሠራተኞች ወደ ቤተ ክርስቲያኖቻችን ሁሉ ወደ ትላልቆችና ትናንሾቹ ሔደው ቤተ ክርስቲያኒቱን ደግሞ ምዕመናንን ለመገንባት እንደምን እንደሚሠራ አባሎቻችንን እንዲያስተምሩዋችው (እንዲመክሩዋቸው) ለመቅጠር ደህና ሆኖ የተደራጀ ፐላን ሊኖር ይገባል፡፡ የሚፈለገው ማሠልጠን፤ ዕውቀት ነው፡፡ ሁሉም በበለጠው የሚመቻቸውን እንዲያደርጉ ራሳቸውን እያሠለጠኑ ለዚህ ጊዜ ለሚሆን ሥራ አስተዋዮች ይሆኑ ዘንድ ልባቸውንና ሐሳባቸውን ይጣሉበት፡፡CCh 67.6

    አሁን ለቤተ ክርስቲያኖቻችን መገንቢያ የሚያሰፈልገው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለውን መክሊት፤ ይኸውም ለጌታ አገልግሎት ዕውቀት ሊያገኙበት የሚቻልበትን መክሊት ማስተዋልና ማግኘት ጥሩ የሆነ የጠቢባን ሰራተኞች ሥራ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናትን በመጐብኘት የሚሠሩ ወንጌላዊውን ሥራ ዓይነተኛ በሆነው ጐዳና እንዲሠሩ ለወንደሞቻችንና ለእህቶቻችን ምክር መስጠት ይገባቸዋል፡፡ እንደዚሁም ለወጣቶች ማሠልጠኛ ክፍል ይሁንላቸው ወጣቶች ወንዶችም ሴቶችም በቤት በጐረቤቶቻቸውና በቤተ ክርስቲያን ሠራተኞች እንዲሆኑ ዕውቀት (ሊማሩ) ሊያገኙ አለባቸው፡፡ ፲፰18.CCh 68.1

    ሰማያዊ መላእክት ሰብዓዊ ወኪሎችን ማለት የቤተ ክርሰቲያን አባሎችን በማሰራው ታላቁ ሥራ አብረዋቸው ለመሥራት ለብዙ ጊዜ ሲጠባበቁ ኑርዋል እየተጠባበቋችሁም ናቸው፡፡ የተቀደሰው ልብ ሁሉ የመለኮታዊ ኃይል መሣሪያ ሁኖ ወደ አገልግሎቱ ይጣደፍ ዘንድ እርሻው በጣም ሰፊ ነው፤ እቅዱም በጣም የሚታሰብበት ነው፡፡ ፲፱199T 46,47;CCh 68.2

    ክርስቲያኖች አንድ ሐሳብ ለመፈጸም በአንድ ኃይል መሪነት አንድ ሆነው ወደፊት በመገስገስ በኅብረት ቢሠሩ ኑሮ፤ ዓለምን ባንቀሳቀሱ ነበር፡፡ ፳209T221; CCh 68.3

    ‹በአውራ መንገዶች› ውስጥ የሚሰጠው ጥሪ በዓለም ሥራ ታላቅ ተከፋይነት ላላቸው ሁሉ ለሕዝበ አስተማሮችና መሪዎች ሊታወጅ (ሊነገር) አለበት ለሕዝባዊ ሕይወት ከባድ ኃላፊነቶች ያላቸው ሐኪሞችና አስተማሮች ጠበቆችና ዳኞች የሕዝብ ሹማምንትና ሰራተኞች ግልጽና ዕውቅ የሆነው መልእክት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ወይስ ምን ይሰጣል ሰው የነፍሱ ቤዛ ማርቆስ ፰፡፴፯፡፴፯CCh 68.4

    ችላ ስለ ተባሉት ድሆች ብዙ ጊዜ በብዙ እንነጋገራለን እንጽፋለንም ችላ ስለ ተባሉትም ባለጸጋዎች ደግሞ አንዳች ማሰብ አይገባንም ብዙዎች ይህን ክፍል ተስፋቢስ እንደሆነ ይመለከቱታል፡ በሰይጣን ኃይል ታውረውና ፈዘዝው ከሐሳባቸው ዘልዓለማዊነትን ፈጽመው ያስወገዱትን ዓይኖቻቸውን ለመክፈት በትንሹ ይሠሩላቸዋል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሐብታሞች ሰዎች ተስፋ የሌለባቸው ዜጋዎች እንደሆኑ መልካቸውን አይተው በመፍረድ የተነሣ አልፈዋቸው ሳይመከሩ ወደ መቃብራቸው ውስጥ ገብተዋል፡፡ ዳሩ ግን ቸልተኞች ሆነው ቢታዩም ከዚህ ከፍል አብዛኞቹ ነፍሳቸው የከበደባቸው እንደሆኑ ታየኝ፡፡ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ለመንፈሳዊ ምግብ የሚራቡ ሐብታሞች ሰዎች አሉ፡፡ ብዙዎች በሚኖሩት የማዕረግ ሕይወታቸው የሌላቸው አንዳች ነገር የሚያስፈልጋቸው እንደሆነ ይሰማቸዋል፡፡ ምንም ጥቅም እንደማያገኙ ይሰማቸዋልና ከመካከላቸው ጥቂቶች ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሔዳሉ፡፡ የሚሰሙት ትምህርት ነፍስን የሚነካ አይደለም፡፡ ለነሱ የግል ጥረት አናደርግላቸውምንአCCh 68.5

    አንዳንዶች፤ ‹በጽሑፎች ልንደርስባቸው አንችልምን› እያለ ይጠይቃሉ፡ በዚህ መንገድ ሊደረስባቸው የማይቻል ብዙዎች አሉ፡፡ የሚያስፈልጋቸው የግል ጥረት ነው፡፡ የተለየ ማስጠንቀቂያ (ምክር) ሳያገኙ ሊጠፉ ናቸውን? በጥንት ጊዜያት እንዲህ አልነበረም፤ የእግዚአብሔር አጋልጋዮች በጌታ የሱስ ክርስቶስ ብቻ ሰላምና ዕረፍትን ሊያገኙ እንዲችሉ ከፍ ባሉት ሥፍራዎች ላሉት ለመናገር ይላኩ ነበር፡፡CCh 68.6

    የሰማይ ግርማዊ አምላክ የጠውፋንና የወደቀውን ሰው ያድን ዘንድ ወደ ዓለማችን መጣ ጥረቶቹ ለተጣሉ ብቻ የሆነ አይደለም ከፍ ባለው ክብር ላሉትም ነው፡፡ አምላክን የማያውቁብንና ትእዛዛቱን የማይጠብቁትን በከፍተኞች ክፍሎች ያሉትን ነፍሳት ሊደርስባቸው በብልሃት ሠራ፡፡CCh 69.1

    ከክርስቶስም ዕርገት በኋላ ይኸው ሥራ ቀጠለ፡፡ ጌታ በቆርኔሌዎስ መደሰቱን የገለጸውን ሐሳብ ሳነብ፤ ልቤ በጣም ይነካል፡፡ ቆርኔሌዎስ በከፍተኛ ማዕረግ ላይ የነበረ ሰው በሮማውያን ጣር ሠራዊት ውስጥ አለቃ የነበረ ዳሩ ግን ከተቀበለው ብርሃን ሁሉ ጋር አጥብቆ በመስማማት ይሔድ ነበር ጌታ ከሰማይ የተለየ መልእክት ላከለት፤ እንዲጐበኘውና ብርሃንን እንዲሰጠው በሌላም መልእት ጴጥሮስን መራ፡፡ ይህ ብርሃንን ለሚሹትና ለብርሃን ለሚጸልዩት እግዚአብሔር ስለሚያደርግላቸው የርኅራኄው ፍቅር እናስብ ዘንድ በሥራችን ትልቅ ማደፋፈሪያ ሊሆን ይገባል፡፡CCh 69.2

    እግዚአብሔር ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር ሊያገናኛቸው የሚፈልጋቸው ሰዎች እንደ ቆርኔሌዎስ ሁነው የታዩኝ ብዙዎች አሉ፡፡ መድልዎአቸው (ሐሳባቸው) ወደ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ጠባቂ ሕዝብ የሚያመራ ነው፡፡ ነገር ግን ከዓለም ጋር የሚያስተሳስሯቸው ክሮች አጥበቀው ይይዙዋቸዋል፡፡ ከዝቅተኞቹ ጋር ሥፍራዎቻቸ ውን ለመያዝ የግብረገብነት /የሞራል/ ድፍረት የላቸውም፡፡ ስላለባቸው ኃላፊነቶችና ስለሚገጥሟቸው ፈተናዎች የተለየ ሥራ ለሚያስፈልጋቸው ለእነዚህ ነፍሳት የተለዩ ጥረቶች ልናደርግላቸው አለብን፡፡CCh 69.3

    ከተሰጠኝ ብርሃን፤ ‹‹እግዚአብሔር እንዲህ ይላል›› የሚለው ግልጽ ንግግር በዓለም ታዋቂነትና ሥልጣን ላላቸው ሰዎች አሁን ሊነገር የሚገባ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ እነሱ እግዚአብሔር ታላቅ እምነት የተጣለባቸው መጋቢዎች ናቸው፡፡ ጥሪውን ቢቀበሉ፤ እግዚአብሔር ለጉዳዩ ይጠቀምባቸዋል፡፡CCh 69.4

    ለከፍተኛዎች ክፍሎች ይሠሩ ዘንድ በተለይ ተስማሚዎች /ተገቢዎች/ የሆኑ አንዳንዶች አሉ፡፡ እነዚህ ዕለት ዕለት አምላክን መሻት ይገባቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች እንደምን እንደሚደረስባቸው ማጥናት አለባቸው፤ ከነሱ ጋር አጋጣሚ ዕውቂያ እንዲኖራቸው ብቻ አይደለም፤ በግላዊ ጥረትና በጋለ /በሕያው/ እምነት እነሱን ጨብጠው፤ለነፍሳቸው የጠለቀ ፍቅር እንዳላቸው እይገለጹ በአምላክ ቃል ውስጥ አንዳለው አድርገው የእውነትን እውነትን እውቀት ያገኙ ዘንድ በውነቱ ለነሱማሰብ ነው ፳፩216T 78 - 81CCh 69.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents