Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    የግል ፍርድ ከፍ ያለ እንደሆነ የመገመት አሥጊነት፡፡

    የግል ፍርዳቸወ ከፍ ያለ እንደሆነ ለመገመት የሚያዘነብሉ እጅግ በሚያሠጋ ሁናቴ ላይ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ሥራውን በምድር ላይ ለመገን ባትና ለማስፋፋት ከሠራባቸው የብርሃን መገናኛዎች ከሆኑት እነዚህን ለማለያየት የሰይጣን የተጠና ጥረቱ ነው፡፡ እውነትን የማስፋፋት ነክ የሆነውን የመሪነት ኃላፊነት ይይዙ ዘንድ እግዚአብሔር የሾማቸውን ችላ ማለት ወይም መናቅ እርሱ (አምላክ) ለመረጃ ለማደፋፈሪያና ለሕዝቡ ጥንካሬ ያዘዘውን ዘዴ ችላ ማለት ነው፡፡ ማንኛውም ሰራተና በጌታ ጉዳይ ረገድ እነዚህን አልፎ በርሃኑ በሌላ መገናኛ (ጎዳና) አማካነት ሳይሆን በቀጥታ ከእግዚአብሔር መምት የሚገባ ነው ብሎ ማሰብ በጠላት ለመታለልና ለመሸነፍ ከሚበገርበት ሁኔታ ላይ ራስን ማስቀመጡ ነው፡፡8AA164; CCh 109.5

    ጌታ በጥበቡ ምዕመናን ሁሉ ሊኖራቸው በሚገባቸው በተቀራረበው ግንኙነት አማካይነት ክርስቲያን ከክርስቲያኑ ጋር ቤተ ክርስቲያንም ከቤተ ክርስቲያን ጋር እንዲተባበሩ አደላድሎአል፡፡ በእንዲህ ሰብዓዊ መሣሪያ የሆነ ከመለኮታዊው ጋር ተባብሮ ለመሥራት ይችላል፡፡ ወኪሉ (ሠራተኛው) የሆነ ሁሉ ለመንፈስ ቅዱስ ተገዥ ይሆናል ምዕመናንም ሁሉ በተደራጀና ደኅና ሁኖ በሚመራው ጥረት ስለ እግዘአብሔር ጸጋ የደስታ ምሥራች ያበሥሩ ዘንድ ይተባበራሉ፡፡9’TT443;CCh 110.1

    የሰብዓዊ ሲስተም (ሰውነት) ልዩ ልዩ ብልቶች ሁሉ ሙሉ አካል ለመሆን እንደሚተባበሩና ሁሉን ለሚያስተዳድረው አእምሮ በመታዘዝ እያንዳንዱ ሥራውን እንደሚሠራ እንደዚሁም የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አባሎች አንድ ሙሉ አካል ለመሆን መተባበርና ለሁሉ ለሚቆመው ለተቀደሰ አእምሮ መገዛት አለባቸው፡፡(CCh 110.2