Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ከአምላክ ጋር አብሮ ሠራተኛ የመሆን እድል (መብት)

    እግዚአብሔር ለጉዳዩ መደገፊያ በሰው ላይ የሚታመን አይደለም፡፡ ይህ ለሰው የሚሻል መሆኑን በቸርነቱ አይቶት ቢሆን ኑሮ ግምጃ ቤቱን ይደግፍ ዘንድ በቀጥታ ከሰማይ ገንዘብ ሊልክ ይችል ነበር፡፡ ያለ ሰዎች ውክልና (ጣልቃ ገቢነት) እውነቱን ለዓለም ይሰብኩ ዘንድ መላእክት የሚላኩበትን ጐዳና ሊያቅድ በቻለ ነበር፡፡ እውነቱን በሰማዮች ላይ ጽፎ በሕያው (ንቁ በሆነው) ባሕርይ ለዓለም የሚናገር ባደረገ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በማናቸውም የሰው ወርቅ ወይም ብር ላይ የሚታመን አይደለም፡፡ ‹‹የምድረ በዳው አራዊት ሁሉ የኔ ናቸውና በሽህ ተራሮችም ያሉት እንስሶች››፡፡ ‹‹ብራብም ላንተ አልነግርኸም ዓለም ከምላትዋ ጋራ ሁሉ የኔ ነውና›› ይላል፡፡ መዝሙር ፶፣፲-፲፪ በሚያስፈልገው ሁሉ ያምላክን ጉዳይ በማስፋፋት ረገድ ለራሳችን የሚሆን ችሎታ አለን እርሱ ለጥቅማችን አስቦ አደራጅቷል፡፡ እኛን ከርሱ ጋር አብሮ ሠራተኞች በማድረጉ አክብሮናል፡፡ የቸርነት ሥራ በመሥራት ይጸኑ ዘንድ ለሰዎች የትብብር ተፈላጊነት ሊሆን እንደሚገባ አዞዋል፡፡CCh 76.2

    የግብረገብ (የሞራል) ሕግ የሰንበትን አጠባበቅ ያጸና ነበር ይኸውም ያ ሕግ ሲጣስ በቀር ሸክም አልነበረም ይህነንም በመጣስ መቀጮ ያገኛቸው ነበር፡፡ ከሐሳቡ ላልራቁት አሥራትን የመክፈል ደንብ ሸክም አልነበረም፡፡ በዕብራውያን ላይ ይጸና የነበረውን ደንብ ባወጣው አምላክ የተሻረ ወይም የተደመሰሰ አይደለም፡፡ አሁንም የማይጸና በመሆን ፈንታ በክርስቶስ ብቻ የሚገኘው ደህንነት በክርስቲያናዊ ዘመን የበለጠውን በምላት በብርሃን ይገለጥ ዘንድ በበለጠው እንዲካሔድና በበለጠው እንዲስፋፋ ነው፡፡CCh 76.3

    ወንጌል ሲዘረጋና ሲስፋፋ ከክርስቶስ ሞት በኋላ ጦርነቱን (ተጋድሎውን) ለመመከት ትልቅ ዘዴ አስፈለገው ይኸውም ከዕብራውያን መንግሥት መሪነት ይልቅ ምጽዋትን የመስጠት ሕግ ይበልጥ በጥብቅ እንዲያስፈልግ አደረገው፡፡ አሁንም ከዚያ ያነሰ ሳይሆን ከማናለቸውም ሌላ የዓለም ጊዜያት ይልቅ እግዚአብሔር ትልቅ ሥጦታ ይፈልጋል፡፡ ክርስቶስ የመሠረተው ኘሪንሲኘል ሥጦታዎቹ በብርሃኑና በበረከቶቹ መጠን ሊሆን የሚገባ መሆኑን ነው፡፡ እርሱ እጅግም የተሠጠው እጅግ የሹበታል” ሲል ተናገረ፡፡ ሉቃስ ፲፪ ፡ ፵፰፡፡ ፲፩113T390-392;CCh 76.4

    ከእግዚአብሔር ቃል የብርሃን ጐርፍ እየበራ ነው እንግዲህ ችላ ለተባሉት ምቹ ጊዜያቶች መነቃቃት ሊሆን ይገባል፡፡ በአሥራትና በሥጦታ የርሱ የሆነውን ላምላክ መልሶ በመስጠት ሁሉም ታማኞች ሲሆኑ ለዚህ ጊዜ የሚሆነውን መልእክት እንዲሰማ ለዓለም መንገዱ ይከፈታል፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ልባቸው በክርስቶስ ፍቅር የተመላ ቢሆን ኑሮ የቤተ ክርስቲያንም አባል ሁሉ ራስን በመሰዋት መንፈስ በፍጹም ቢቀባ ኑሮ ሁሉም ፍጹም የሆነ ቅንነት ቢገልጽ ኑሮ ለቤት ወይም ለውጭ አገር ሚሲዮኖች (ወንጌላዊ ሥራዎች) የገንዘብ ጐድለት አይሆንባቸውም ነበር፡፡ ገቢያችን ይበዛ ነበር በሺህ የሚቆጠሩ የጠቃሚነት በሮች ይከፈቱ ነበር እኛም ልንገባባቸው እንታደም ነበር፡፡ የምሕረትን መልእክት ለዓለም በመስጠት ሕዝቡ ያምላክን ሐሳብ አካሔዶ ቢሆን ኑሮ ክርስቶስ ከዚህ በፊት ወደ ምድር በመጣ ነበር ጻድቃንም ወደ እግዚአብሔር ከተማ መልካም አቀባበል በተቀበሉ ነበር፡፡ ፲፪126T449, 450;CCh 77.1