Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፲—ክርስቶስ ጽድቃችን፡፡

    ‹‹በኃጢአታችን ብንናዘዝ እርሱ የታመነና ጻድቅ ነው ኃጢአታችነን ይቅር ይለን ዘንድ ከግፍም ሁሉ ያነጻን ዘንድ››፡፡ ፩ ዮሐ መልእክት ፩፣፱፡፡CCh 89.1

    እግዚአብሔር ኃጢአታችንን እንድንናዘዝና በፊቱ ልባችንን ዝቅ እናደርግ ዘንድ ይፈልገናል ነገር ግን በዚያኑ ጊዜ ርኅሩኅ አባት መሆኑንና በርሱ የሚታመኑትን የማይረሳ መሆኑን በርሱ ልናምን ይገባናል፡፡ ብዙዎቻችን በሓይማኖት ሳይሆን በማየት እንሔዳለን፡፡ የሚታዩትን ነገሮች እናምናለን ነገር ግን በአምላክ ቃል ውስጥ የተሰጡንን የተከበሩ (ተወዳጅ) ተስፋዎች ዋጋነታቸውን አንገምትም፣ ሆኖም የሚለውን ካለማመንና ጌታ ለኛ አሳቢ ይሆን ወይስ ያታልለን ይሆን እያልን ምንጠራጠርበት መሆናችንን ከማሳየታችን በቀር በይበልጥ ቁርጥ ሐሳብ አድርገን አምላክ ልናሳፍር ምንችልበት የለም፡፡CCh 89.2

    እግዚአብሔር በኃጢአታችን የተነሣ አይተወንም፡፡ ስሕተት አድርገን መንፈሱን እናሳዝን ይሆናል፣ ነገር ግን ንስሐ ስንገባና በተጸጸተው ልብ ወደርሱ ስንመጣ እርሱ አያስወግደንም፡፡ የሚወገዱልን እንቅፋቶች (ክልከላዎች) አሉ፡፡ የስህተት ስሜቶችን ወደናል ትዕቢት በራስ መብቃት አለመታገሥና ማጉረምረም ኑረውብናል፡፡ እነዚህ ሁሉ ከአምላክ ይለዩናል፡፡ ኃጢአታችንን መናዘዝ አለብን በልባችንም ውስጥ የጠለቀ የጸጋ ሥራ ሊኖርብን ይገባል፡፡ ደካሞችና ተስፋ የቆረጡ (የተስፈራሩ) መሆናቸው የሚሰማቸው ጠንካሮች የአምላክ ሰዎች ሊሆኑና ለጌታ የተከበረ ሥራ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ከፍ ባለው አቋም መሥራት አለባቸው ራስን ባለመውደድ ሐሳቦች የተነቃቁ መሆን አለባቸው፡፡CCh 89.3

    በክርስቶስ ትምህርት ቤት መማር አለብን፡፡ ከጽድቁ በቀር ከጸጋው ኪዳን በረከቶች አንዱን ሊያጎናጽፈን (ሊያበረክትልን) የሚችል ነገር የለም፡፡ እነዚህን በረከቶች ለማግኘት ለብዙ ጊዜ ተመኝተናቸዋል ሞክረናልም ነገር ግን አልተቀበልናቸውም ምክንያቱም ልናገኛቸው ራሳችንን ተገቢዎች እናደርግ ዘንድ አንዳች ነገር ለማድረግ የምንችል የመሆናችንን ሐሳብ ስለወደድን ነው፡፡ የሱስ ሕያው መድኅን መሆኑን እያመንን ከራሳች ራቅ ብለን አልተመለከትም፡፡ የገዛ ራሳችን ጸጋና ትሩፋቶች የሚያድኑን መሆናቸውን ማሰብ አይገባንም የክርስቶስ ጸጋ የደህንነት ተስፋችን እርሱ ብቻ ነው፡፡ በነቢዩ አማካይነት ጌታ ‹‹በደለኛ መንገዱነ ይተው ክፉ ሰውም ሐሳቡን፡፡ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ ይምረውማል ወዳምላካችንም ይቅርታው ብዙ ነውና›› ሲል ተስፋ ይሰጠናል፡፡ ኢሳይያስ 25፣7፡፡ ባዶውን ተስፋ ማመን ይገባናል ለሃይማኖትም ስሜትን መቀበል አይደለም፡፡ በአምላክ ፈጽመን ስንታመን ለኃጢአት ይቅርታ ሰጪ መድኅን መሆኑን በየሱስ ትሩፋቶች ላይ ስንታመን የምንፈልገውን እርዳታ ሁሉ እንቀበላለን፡፡CCh 89.4

    ራሳችንን ለማዳን ኃይል እንዳለን አድርገን ወደ ራስ እንመለከታለን ነገር ግን ይህን ለማድረግ ረዳተቢሶች ስለሆን የሱስ ሞተልን፡፡ ተስፋችን ጽድቃችን በርሱ ነው፡፡ ስለዚህ መድኀን እንደ ሌለን ወይም ምሕረት ሊያደርግልን ምንም ሐሳብ እንደ ሌለው አድርገነው ተስፋ መቁረጥና መፍራት አይገባነም፡፡ በዚሁ ጊዜ ለኛ ሲል ሥራውን በማካሔድ ላይ ነው በረዳተቢስነታችን ወደርሱ መጥተን እንድን ዘንድ ወደርሱ እንድንመጣ ያድመናል፡፡ እርሱ ባለማመናችን አናከብረውም፡፡ እጅግ ታላቅ ወዳጃችንን እንደምን የምንቀበለው መሆናችን ፈጽሞም ሊያድነን በሚችለውና ስለ ታላቅ ፍቅሩ ማስረጃ ሁሉ በሰጠን ላይ እንደምን በትንሹ እምነት ማድረጋችን የሚደንቅ ነው፡፡CCh 90.1

    ወንድሞቼ ኃሉ የሚያድን መሆኑን ከማመናችሁ በፊት ከኃጢአት ነጻ መሆን እንዳለባችሁ ትሩፋታችሁ ለአምላክ ሞገሥ የሚያበቃችሁ እንደሆነ ተስፋ ታደርጋላችሁን? በሐሳባችሁ ውስጥ ሚደረገው ጥረት ይህ ከሆነ ምንም ኃይል የማታገኙና በመጨረሻም ተስፋ የምትቆርጡ መሆናችሁን እፈራለሁ፡፡CCh 90.2

    በምድረ በዳ ጌታ መርዛሞቹ እባቦች ዓመፀኞችን እንዲነድፉ በፈቀደ ጊዜ ሙሴ የነሐስ እባብ እንዲሰቅልና የቆሰሉ ሁሉ ተመልክተው እንዲድኑ እንዲያዛቸው ተነገረው፡፡ ነገር ግን ብዙዎች በዚህ ከሰማይ በተላከላቸው መድኅንነት እርዳታ እዳለ አላዩም፡፡ የሞቱትና ሚሞቱት ሁላቸውም በአካባቢያቸው ነበሩ እነሱም አለመለኮታዊ እርዳታ ፍዳቸው (ጥፋታቸው) የተረጋገጠ መሆኑን አወቁ ነገር ግን በመቁሰላቸው፣ በሕመማችው፣በእርግጥም ስለ መሞታቸው ያለቅሱ ነበር ይኸውም ኃይላቸው እስኪዳከምና ዓይኖቻቸውን አተኩረው ተመልክተው ወዲያው ፈውስን እስኪያገኙ ድረስ፡፡CCh 90.3

    ‹‹ሙሴም እባብ እንደ ሰቀለ በምድረ በዳ እንዲሁ ይገባዋል የሰው ልጅ ይሰቀል ዘንድ፡፡ በርሱ የሚያምን ሁሉ እንዳይጠፋ የዘለዓለም ሕይወት ትሆንለት ዘንድ እንጂ››፡፡CCh 90.4

    ኃጢአት ማድረግህን ብታውቅ በዚሁ ላይ እየተዋዠቅህ በማልቀስ ኃይልህን ሁሉ ፈጽመህ አትስጥ፣ ነገር ግን ተመልከትና ዳን፡፡ መድኃኒታችን የሱስ ብቻ ነው፡፡ ሊፈወሱ የሚያስፈልጋቸው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የተሰጣቸውን ምሕረት ችላ ቢሉ እንኳ ማንም በትሩፋቶቹ የሚታመነውን እንዲጠፋ የሚተወው አይደለም፡፡ ያለ ክርስቶስ ረዳተቢስ መሆናችንን ስንገነዘብ ሳለን ተስፋ መቁረጥ አይገባንም በተሰቀለውና በተነሳው መድኀናችን መታመን አለብን ምስኪኑ ኃጢአት ያጠቃው ተስፋ የቆረጠው (የተስፈራራው) ነፍስ ተመልከትና ዳን፡፡ የሱስ ቃሉን ዋስትና ሰጥቶአል፣ ወደርሱ የሚመጡትን ሁሉ እርሱ ያድናል፡፡CCh 90.5

    ወደ የሱስ ና፤ ዕረፍትንና ሰላምንም ተቀበል፡፡ አሁንም እንኳ በረከትን ልታገን ትችላለህ፡፡ ሰይጣን ረዳተቢስ እንደሆንክና ራስህን ልትባርክ የማትችል እንደ ሆንህ ሳስባል፡፡ እውነት ነው ረዳተቢስ ነህ ነገር ግን የሱስን እፊቱ ሰቅለህ ‹‹የተነሣ መድኅን አለኝ፣ በእርሱም አምናለሁ አርሱም እንዲደናገረኝ ከቶ አይተወኝም፣ በእርሱም ስም አሸንፋለሁ፣ እርሱ ጽድቄና የደስታ አክሊሌ ነው›› በል እዚህ ማንም የእርሱ ነገር ተስፋቢስ እንደሆነ አይሰማው ተስፋቢስ አይ ደለምና፡፡ ኃጢአተኛና ጎስቋላ መሆንህን ታይ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ስለዚህ ነው መድኅን የሚያስፈልግህ፡፡ የምትናዘዝ ኃጢአት ካለህ ጊዜህን አታጥፋ፡፡ እነዚህ ጊዜያቶች ወርቃዊ ናቸው፡፡ ‹‹በኃጢአታችን ብንናዘዝ እርሱ የታመነና ጻድቅ ነው፡፡ ኃጢአታችንን ይቅር ይለን ዘንድ ከግፍም ሁሉ ያነጻን ዘንድ፡፡›› ፩ ዮሐ፣ መል ፩፣፱፡፡ የሱስ ተስፋ ሰጥቶናልና ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ይጸግባሉ፡፡ ክቡር የሱስ! ክንዶቹ ሊቀበሉን የተዘረጉ ናቸው ታላቁም የፍቅር ልቡ ሊባርከን ይጠባበቀናል፡፡CCh 90.6

    አንዳንዶች በረከቱን ለመለመን ከመቻላቸው በፊት በምርመራ (በመፈተን) ላይ መሆን እንዳለባቸውና ቅኖች እንደሆኑ ለጌታ ማስረዳት ሚገባቸው መሆኑን የሚሰማቸው ይመስላል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ተወዳጆች ነፍሳት አሁን እንኳ በረከቱን ሊለምኑ ይችላሉ፡፡ ድክመታቸውን ለመረዳት ጸጋውን የክርስቶስን መንፈስ ማግኘት አለባቸው አለበለዚያ ክርስቲያናዊ ጠባይ ሊያበጁ አይቻላቸውም፡፡ የሱስ እንዲሁ እንዳለን ኃጢአተኞች ረዳተቢሶች ጥገኞ ሁነን ወደርሱ ንእድንመጣ ይወዳል፡፡CCh 91.1

    ንስሐ መግባት እንዲሁም ይቅርታ ማግኘት በክርስቶስ አማካይነት የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው፡፡ ስለ ኃጢአት የምንረዳ ይቅርታ የሚያስፈልገን መሆኑ የሚሰማን በመንፈስ ቅዱስ አነቃቂነት ነው፡፡ ስለ ኃጢአታቸው ተጸጸቱት ብቻ ይቅርታ ያገኛሉ ነገር ግን ልብን ንስሐ እንዲገባ የሚያደርገው የአምላክ ጸጋ ነው፡፡ እርሱ ድክመታችንና ጉድለታችንን ሁሉ ያውቃልና ይረዳናል፡፡ አንዳንዶች ንስሐ በመግባትና በመናዘዝ ወደ እግዚአብሄር የሚመጡና ለኃጢአታቸውም ይቅርታ እንዳገኙ የሚያምኑ እንኳ እንደሚገባ ያምላክን ተስፋዎች አይለምኑም፡፡ የሱስ ለዘለዓለም አብሮዋቸው የሚሆን መሆኑን አያዩም በልባቸውም የተጀመረውን የጸጋ ሥራ እንዲፈጽምላቸው እየታመኑበት ነፍሳቸውን እንዲጠብቀላቸው አደራ ለመስጠት ዝግጁዎች ኤደሉም፡፡ ራሳቸውን ለአምላክ አደራ የሚሰጡ መሆናቸውን ሲያስቡ ሳለ በጣም በራስ ላይ የሚታመኑ ናቸው፡፡ በከፊል በአምላክ የሚታመኑ በከፊልም በራሳቸው የሚታመኑና በሐሳባቸው የሚመሩ ነፍሳት አሉ፡፡ በኃይሉ እንዲጠበቁ ወደ አምላክ አይመለከቱም ነገር ግን በፈተና ላይ የሚተጉና እርሱ እንዲቀበላቸው የተለዩ ተግባሮች የሚያደርጉ በመሆናቸው ላይ ይታመናሉ፡፡ በእንደዚህ ያለ ሃይማኖት ድል መንሣት የለም፡፡ እንደዚህ ያ ሰዎች ለሚያደርጉት ጥረት ግብ ላቸውም ነፍሳቸውም ዘወትር በባርነት ቀንበር ውስጥ ነው፡፡ ሸክሞቻቸውን በየሱስ እግሮች ላይ እስኪጥሉ ድረስ ዕረፍት አያገኙም፡፡CCh 91.2

    ዘወትር መትጋትና ከልብ የሆነ የተወደደ ቅድስና ያስፈልገናል ነገር ግን እነዚህ በተፈጥሮ የሚመቱት ነፍስ በሃይማኖት በእግዚአብሔር ኃይል ሲጠበቅ ነው፡፡ እኛ ለአምላክ ሞገስ ተገቢዎች ለመሆናችን ለራሳችን ልንመሰክር በፍጹም ምንም ነገር ለማድረግ አንችልም፡፡ በራሳችን ወይም በመልካም ሥራችን ፈጽመን መታመን አይገባንም፡፡ ነገር ግን ተሳሳቾች ኃጢአተኞች ፍጡራን ሁነን ወደ ክርስቶስ ስንመጣ በፍቅሩ ዕረፍት ልናገን እንችላለን፡፡ በተሰቀለው መድኅን ትሩፋቶች በፍጹም የታመነ ወደርሱ የሚመጣውን ሁሉ እግዚአብሔር ይቀበል፡፡ ፍቅር በልቡ ውስጥ ይመነጫል፡፡ የስሜት ወረት አይሆንበትም ነገር ግን ጽኑ የሆነ ሰላማዊ እምነት ይኖረዋል፡፡ ሸክሙ ሁሉ ቀላል ነው ክርስቶስ የሚጭንበት ቀንበር ቀሊል ነውና፡፡ ተግባርም ደስታ ይሆነለታል መሥዋዕትነትም ፍስሐው በፊት በጨለማ የተከበበ መስሎ የታየው ጎዳና ከጽድቅ ጸሐይ በሚያሸበርቁት ጮራዎች የበራ ይሆናል፡፡ ይኸውም ክርስቶስ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ውስጥ መሔድ ነው፡፡ ፩12 TT 91— 95CCh 91.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents