Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ራስን የመካድና የመሥዋዕት መንፈስ

    የደህንነት ሐሳብ ወሰን በሌለው የእግዚአብሔር ልጅ መሥዋትነት ታቀደ፡፡ ከየሱስ ክርስቶስ መስቀል የሚበራው የወንጌል ብርሃን ራስን ወዳድነትን ይዘልፋል በልግሥናና ቸርነት ያደፋፍራል፡፡ ለመስጠት ተጨማሪዎች ጥሪዎች መኖራቸው የሚጸጸቱበት (የሚለቀስለት) ነገር መሆን የለበትም ታላላቅ ሥራዎች ይጀምሩ ዘንድ እግዚአብሔር በቸርነቱ ከተወሰነው የተግባር አካባቢ ሕዝቡን እየጠራ ነው፡፡ በዚህን ጊዜ ዓለምን ጨለማ በሚሸፍንበት ጊዜ ያልተወሰነ ጥረት ያስፈልጋል፡፡ ዓለማዊነትና ስስት የእግዚአብሔርን ሕዝብ ቁምነገራምነት እየደመሰሰባቸው ነው፡፡ ለገንዘባቸው ጥየቃዎች የሚያበዛ ምሕረቱ መሆኑን ማስተዋል አለባቸው፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ በጸሎት አጠገብ የቸርነት አድራጎት ያኖራል፡፡ ለቆርኔሌዎስ “ጸሎትህ ምጽዋትህም በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰብ ወጣ” አለ፡፡ የሐዋ ፲፡፬ ፡፡ ፳፮263T405;CCh 83.5

    በቤቶቻችሁ መቆጠብን ልመዱ፡፡ በብዙዎቹ ጣዖታት የሚወደዱና የሚመለኩ ናቸው፡፡ ጣዖቶቻችሁን አስወግዱ፡፡ ራስን የመውደድ ተድላዎቻችሁን ተው፡፡ ቤቶቻችሁን በማጌጥ ገንዘባችሁን አትጨርሱ እያልሁ እለምናችኋለሁ የእግዚአብሔር ገንዘብ ነውና እንደገና ከናንተ ይፈልግባችኋል፡፡ ወላጆች ስለ ክርስቶስ ብላችሁ ልጆቻችሁን በማሽሞንሞን ልታስደስቷቸው ያምላክን ገንዘብ አትጠቀሙ፡፡ በዓለም ዘንድ እውቂያ ያገኙ ዘንድ መቀማጠልንና መጀነንን እንዲሹ አታስተምሩዋቸው፡፡ ይህ ክርስቶስ የሞተላቸውን ነፍሳት ለማዳን የሚያዘነብላቸው ነውን? የለም ቅናት፣ መመቅኘትንና ክፉውን ሐሳብ የሚፈጥር ነው፡፡ ልጆቻችሁ በዓለም ጅነናና (ታይታ) መንፈላሰስ ይወዳደሩ ዘንድ ለጤና ወይም ለደስታ ጠቃሚም ላልሆነው ነገር የጌታን ገንዘብ ያባክኑ ዘንድ ይመራሉ፡፡CCh 84.1

    እናንተ ለልጆቻችሁ ያላችሁ ፍቅር በትዕቢታቸው በመንፈላሰሳቸውና በመጀነን ፍቅራቸው በመሳተፋቸው የምትወዷቸው መሆኑን እንዲያስቡ ልጆቻችሁን አታስተምሩ፡፡ ገንዘብን በመጠቀም ረገድ መንገዶችን ለመፈልሰም አሁን ጊዜ የለም፡፡ ቁጠባ ለማድረግ በመሻት በብልሃት ችሎታዎቻችሁን ተጠቀሙበት፡፡ ራስን የመውደድ ዝንባሌ ከማከባከብ የአእምሮንም ችሎታዎች ለሚያጠፉ ነገሮች ገንዘብን በማባከን ፈንታ በአዳዲስ ጣቢያዎች የእውነትን ደረጃ ከፍ በማድረግ (በማንሳት) አንዳች የምታጠራቅሙ ነገር እንዲኖራችሁ ራሳችሁን እንደምን እንደምትክዱ አጥኑ አእምሮ መክሊት ነው ለነፍሳት ማዳኛ ገንዘባችሁን በተሻለው እንደምን እንደምትጠቀሙበት በማጥናት ተጠቀሙበት፡፡ ፳፯276T450, 451;CCh 84.2

    ለሌሎች መልካም ያደርጉ ዘንድ ራስን የሚክዱና ራሳቸውንና ያለውን ሁሉ ለክርስቶስ አገልግሎት ቀድሰው የሚሰጡ ራስን ወዳድ ሰው በከንቱ የሚሻውን ደስታ ይገነዘባሉ፡፡ መድኃኒታችን “እንደዚሁም ከላንት ሁላችሁ ከብቱን ሁሉ ያልተወ አይችልም ለኔ ደቀመዝሙር ይሆን ዘንድ” አለ ሉቃስ 14፡33፡፡ በክርስቶስ ሕይወት የነበረው ያ ራስን አለመውደድ የፍቅርና የቸርነት (የልግስና) ፍሬ ይኸው ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሕግ በልባችን ውስጥ ጥቅሞቻችንን ከፍ ላለውና ለዘላለማዊ አሳቢነት ወደ መገዛት ያመጣቸዋል፡፡ ፳፰283T397CCh 84.3