Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    እግዚአብሔር ከገቢያችን አንድ አሥረኛውን (አሥራትን) ይጠይቃል፡፡

    አሥራትን የመክፈል ደንብ (ሲስተም) የወጣው ከሙሴ ጊዜያት ቀደም ብሎ ነው፡፡ ለሙሴ የተረጋገጠው ደንብ ከመውጣቱ በፊት መለስ ብሎ እስከ አዳም ጊዜያት እንኳ ስለ ነበረ ሰዎች ለኃይማኖታዊ ሐሳብ ለእግዚአብሔር ሥጦታዎችን መስጠት ያስፈልጋቸው ነበር፡፡ ከአምላክ ፍላጎቶች ጋር በመስማማታቸው ላደረገላቸው ምሕረትና ለሰጣቸው በረከቶች ማመስገናቸውን በሥጦታዎች መግለጽ ነበረባቸው፡፡ ይህም በተከታዮቹ ትውልዶች ዘንድ ቀጠለ ለመልከጼዴቅ ለልዑል ካህን አሥራትን በሰጠው አብርሃም የተካሔደ ሆነ፡፡ ያው ኘሪንሲኘል በኢዮብ ጊዜያት ነበር፡፡ ያዕቆብ በቤቴል ስደተኛና ምንም የሌለው ተቅበዝባዥ በሌሊት ተኝቶ ብቻውን ሳለ ለትራስ ቋጥኝ ተንተርሶ ነበር እዚያም “ከሰጠኸኝም ሁሉ ላንተ ካሥር አንድ እሰጥሃለሁ” ሲል ላምላክ ተስፋ ሰጠ፡፡ ዘፍጥረት ፳፪፡፳፰፡፡ እግዚአብሔር እንዲሰጡት ሰዎች አያስገድድም የሚሰጡት ሁሉ በፈቃዳቸው ሊሆን ይገባል፡፡ ሳይፈቅዱ በሚሰጡት ሥጦታዎች ግምጃ ቤቱ እንዲሞላ አይፈቅድም፡፡CCh 77.2

    ስለሚያስፈልገው የስጦታ ልክ እግዚአብሔር ከገቢው አንድ አሥረኛውን ወስኖአል፡፡ ይህም የሚያርፈው ይህን አሥራት በመክፈል ረገድ ገጻ ፍርድ (ሐሳብ) ባላቸው የሰዎች ሕሊናና ቸርነት ላይ ነው፡፡ በሕሊና ላይ ነጻ ሆኖ የሚያርፍ ሲሆን ለሁሉም የተወሰነ በቂ ኘላን ታቅዶአል፡፡ ግዳጅነት የሚያስፈልግ አይደለም፡፡CCh 77.3

    እግዚአብሔር በሙሴ ጊዜ ከገቢያቸው ሁሉ አሥረኛውን (አሥራትን) እንዲሰጡ ሰዎችን ጠየቃቸው፡፡ የዚህ ሕይወትን ነገሮች መክሊቶች እንዲሻሻሉና ለርሱ እንዲመልሱለት በእምነት አደራ ሰጣቸው አሥረኛውን ፈለገባቸው ይህንንም አነስተኛውን ሰው ለርሱ ሊመልስለት እንደሚገባው ይፈልግበታል፡፡ የኔ የሆነውን አንድ አሥረኛውን ስፈልግባችሁ ዘጠኝ አስረኛውን እሰጣችኋለሁ ይላል፡፡ ሰዎች አንድ አሥረኛውን ሲያስቀሩበት እግዚአብሔርን መቀማታቸው ነው፡፡ የኃጢአት መሥዋዕቶች የሰላም መሥዋዕቶችና የምስጋና መሥዋዕቶች ደግሞ ከገቢው አሥረኛ ከሆነው ጭምር ያስፈልጉ ነበር፡፡CCh 77.4

    እግዚአብሔር ከሚፈልገው ከገቢው አሥረኛውን ማስቀረት በሚያስቀሩት ላይ እንደ ቀማኛነት በሰማይ መጻሕፍት ውስጥ ይጻፍባቸዋል፡፡ እንዲህ ያሉ ፈጣሪያቸውን ያታልላሉ ይህ የቸልተንነታቸው ኃጢአት እፊታቸው ሲገለጥባቸው እርምጃቸውን ለውጠው ከዚያን ጊዜ አንስተው በቀናው ኘሪንሲኘል ይሠሩ ዘንድ መጀመር አይበቃቸውም፡፡ ለአበዳሪው እንዲመልሱ በእምነት አደራ የሰጣቸውን ንብረት በመቀማታቸው በሰማያዊ መዝገብ የተጻፈባቸውን አርአያዎች ይህ የሚያርም አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ያለመታመንን አድራጎት በመሥራታቸውና ስለ የወራዳነት ምሥጋና ቢስነታቸው ንስሐ መግባት ያስፈልጋቸዋል፡፡CCh 78.1

    የእግዚአብሔር ሕዝብ በማናቸውም ዘመነ ዓለም ሐሳቡን በደስታና በፈቃደኝነት ሲያካሒዱና ከፍላጎቶቹ ጋር በተስማሙ ቁጥር በገንዘባቸውም ሲያከብሩት ጎተሮቻቸው በብዙ ይሞሉላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን በአሥራትና በሥጦታ አምላክን ሲቀሙ እርሱን ብቻ መቀማታቸው ሳይሆን ራሳቸውንም የሚቀሙ መሆናቸውን ይገነዘቡ ነበር ለርሱ ስጦታቸውን በወሰኑበት መጠን እርሱም ለነሱ በረከቶቹን ይወስንባቸው ነበርና፡፡ ፲፫133T393-395;CCh 78.2

    የተቸገረ ሰው (ያልታደለ) በዕዳ ላይ ሆኖ ራሱን ቢያገኝ ለባልንጀሮቹ ዕዳውን ይከፍል ዘንድ የጌታን ድርሻ መውሰድ የለበትም በዚህ አድራጎት የሚፈተን መሆኑንና ለገዛ ጥቅሙ የጌታን ድርሻ በማስቀረቱ ሰጪውን የሚቀማ መሆኑን ማሰብ አለበት፡፡ ላለው ሁሉ ለአምላክ ባለዕዳ ነው ለጌታ የተቀመጠውን ገንዘብ ለሰብዓዊ ፍጥረት ዕዳ ለመክፈል ሲጠቀምበት በዕፅፍ ባለዕዳ ይሆናል፡፡ “ለእግዚአብሔር ያልታመነ” የሚል በስሙ ላይ በሰማይ መጻሕፍት ውስጥ ይጻፍበታል፡፡ ለገዛ ምቾቱ ያምላክን ገንዘብ ለራሱ በማድረጉ አምላክ የሚቆጣጠረው ሒሳብ አለው፡፡ የእግዚአብሔርን ገንዘብ ያለ አግባብ በመጠቀሙ ያሳየው የኘሪንሲኘል ጉድለት የሌላውም ጉዳዮች (ነገሮች) ነክ በሆነው አመራሩ ይገለጻል፡፡ ከገዛ ሥራው ጋር ግንኙነት ባሏቸው ጉዳዮች ሁሉ ይታያል፡፡ አምላክን የሚቀማ ሰው እላይ ወዳሉት ያምላክ ቤተሰብ ከመግባት የሚያግደውን የጠባይ ባህል ማፍራቱ ነው፡፡ ፲፬146T391;CCh 78.3