Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መ ግ ቢ ያ ፡፡

    በዚህ ቮሊዩም ስልሣ ስድስት ምዕራፎች ውስጥ በሚገባ ተጠራቅመው የተውጣጡት ጽሑፎች በሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ዋና መሥሪያ ቤት በዋሽንግቶን ዲ ሲ በዲቪሺኑ ውስጥ ለሚስስ ኋይት ጽሑፎች ለመጠንቀቅ ኃላፊ በሆነው ትልቅ ኮሚቴና የዔሌን ጂ ኋይትን ጽሑፎች አሳትሞ ለማውጣት አደራ በተሰጠው ጉባዔ (ትራስቲስ) አማካይነት የሚካሔደው ሥራ ነው፡፡CCh iv.1

    ከ ኢ ጂ ኋይት መጽሐፎች ዋና ዋናዎቹን የተውታጡ ጽሑፎች በአንድ ቮሊዩም ለማጠራቀም ለማደራጀት፣ ለመተርጎምና አሳትሞ ለማውጣት ካሁን ቀደም ትልቅ ድካምና ጥረት ተደርጎበታል፡፡ ሥፍራ የማይበቃ ስለሆነ ስለ ዋና ዋናዎቹ ሐሳቦች የተሰጡት በጣም አስፈላጊ የሆኑ ምክሮች ብቻ ተጽፈዋል፡፡ ይህም እንኳ ሰፋ ያሉ አርእስት ነገሮችን የሚያቀርብ ነው፡፡ ባንዳንድ ነገሮች የተውታጣው ጽሑፍ ከልዩ ልዩ ምንጮች በየጊዜያቱ በተጠራቀሙት በጥቂቶች አንቀጾች መሠረት የተወሰነ ነው፡፡ ጽሑፎቹ ከተጠናቀሩበት መጽሐፎች የተጠቀሱት ጥቅሶች በእያንዳንዱ ምዕራፍ መጨረሻ ላይ በአሕጽሮት ተጽፈው ይገኛሉ፡፡ የተዛነፉትን ክፍለ አንቀጾቹን ወይም አረፍተ ነገሮችን ለማመልከት ምንም ሙከራ አልተደረገበትም፡፡CCh iv.2

    በፗ፱፻፶፭ ዓ፣ም እ.ኤ.አ በፑና በሰሚናሪ ኤክስተንሺን ትምህርት ቤት ከዲቪሺኑ ልዩ ልዩ ክፍሎች የተሰበሰቡት ብዙዎች ሰራተኞች ባቀረቡት ልመና መሠረት፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተቋቋመችበት ጊዜ አንስቶ፤ ኤሌን ጂ ኋይት ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር ግንኙነት ካደረገችበት ጊዜ ጀምሮ በፗ፱፻፶፭ ዓ.ም እ.ኤ.አ በሞት እስክታርፍ ድረስ ትንቢታዊ ሥጦታ እንደነበራት አንባቢውን ከዔሌን ጂ ኋይትና ከትንቢታዊ ሥጦታ ሥራዋ ጋር የሚያስተዋውቅ ማሳሰቢያ በዚህ ቮሊዩም ተዘጋጅቶለታል፡፡ ይህ የቮሊዩሙ ክፍል እርስዋ ስለ ጻፈችው ምክር ብቻ ከሚያቀርበውና ምዕራፎቹ በቁጥር ከተመለከቱለት የመጽሐፉ ክፍል ጋር መዘበራረቅ የለበትም፡፡CCh iv.3

    ይህ ቮሊዩም እንዲወጣላቸው ለብዙ ጊዜ ሲጠባበቁ ለነበሩት አሁን ጠቃሚ እንዲሆንላቸው ስናቀርብ በጣም ደስ ይለናል፡፡ በነዚህም ገጾች ውስጥ ያለው ተወዳጅ ምክርና ትምህርት ስለ ዳግመኛ ምጽዓት የሚያመለክተውን የመልእክቱን እውነት አንባቢው በሰፊው እንዲረዳ እንዲያደርገው፤ ክርስቲያናዊ ልምምዱንም እንዲያስፋፋለትና፤ በመጨረሻ ቀን ጌታ ሲመለስ ድል የማድረግ ተስፋውን ከፍ እንዲያደርግለት የደበቡባዊ አሲያ ዲቪሺን አለቆችና የዔሌን ጂ ኋይት ጽሑፎች አሳታሚ የሆነው የትራስቲስ ቦርድ ከልብ የሆነ ጸሎታቸው ነው፡፡CCh iv.4

    የዔሌን ጂ ኋይት መጽሐፎች ኣሳታሚ የትራስቲስ ቦርድCCh iv.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents