Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምክሯን ለማይቀበሉ የቤተ ክርስቲያን ተግባር፡፡

    በክርስቶስ የተሰጠንን ምክር በታማኝነት እስኪከተሉ ድረስ የስህተት አድራጊውን (የበደለኛው) ስም ከቤተ ክርስቲያን መጽሐፎች ይፍቅ ዘንድ ማነም የቤተ ክርስቲያን አለቃ መምከር ማንኛውም ኮሚቴ መወሰን የለበትም፡፡ ይህን አድርጋለች ክፉው ያን ጊዜ እንዲሁ እንዳለ መገለጽ ይገባዋል፤ በይበልጥ የተስፋፋ እንዳይሆን ሊወገድም ይገባዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጤንነትና ንጽሕና ሊጠበቅ ይገባል፤ በእግዚአብሔር ፊት ያልረከሰችና የክርስቶስ ጽድቅ ልብሶች የተጐናጸፈች ሆና ትቆም ዘንድ፡፡CCh 121.7

    የተሳሳተው ንስሐ ቢገባና ለክርስቶስ ዲሲፕሊን ቢገዛ ሌላ ሙከራ ሊሰጠው አለበት፡፡ ንስሐ ባይገባም እንኳ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ቢቆምም ያም ልሱት ዘንድ አጥብቀው መሻት አለባቸው፡፡ ያደረገው በደል ምንም የከፋ ቢሆን፤ ለመንፈስ ቅዱስ ጥረት ቢገዛና /እሺ ቢልና/ በመናዘዝና ኃጢአቱን በመተው ንስሐ መግባቱን ማስረጃ ቢሰጥ ይቅርታ ተደርጎለት እንደገና ወደ መንጋ መቀበል ነው፡፡ ወንድሞቹ በቀና መንገድ እርሱን ማደፋፈርና ስለ ራሳቸውም እያሰቡ እነሱም ደግሞ እንዳይፈተኑ፤ በርሱ ሥፍራ ቢሆኑ ኑሮ ሊደረግላቸው እንደሚፈልጉ ለርሱም ማድረግ ይገባቸዋል፡፡CCh 122.1

    ‹እውነት እላችኋለሁ›፤ሲል ክርስቶስ ንግግሩን ቀጠለ፤በምድር ያሠራችሁት ሁሉ በሰማይ የታሠረ ይሆናል፡፡ በምድርም የፊታችሁም በሰማይ የተፈታ ይሆናል›፡፡ቁ ፲፰CCh 122.2

    ይህ ንግግር በዘመኖቹ ሁሉ የጸና ሆኖ ይኖራል፡፡ በክርስቶስ ፈንታ ሆና ትሰራ ዘንድ ለቤተ ክርስቲያን ኃይል /ሥልጣን/ ተሰጥቶዋታል፡፡ በሕዝቡ መኻከል ሥርዓትንና ዲሲፕሊንን ለመጠበቅ ያምላክ መሣሪያ ናት፡፡ ስለ ልማተዋ ስለ ንጽሕናዋና ሥርዓትዋ የሆኑት ጥያቄዎችን ሁሉ ለመወሰን (ለማደላደል) ኃይልን አጐናጽፎዋታል፡፡ ያልተገቡትን የክርስቶስን ጠባይ ባልመሰለው ጠባያቸው በቤተ ክርስቲያን ላይ ውርደትን (ኃፍረትን) የሚያመጡትን ከማኅበርዋ ተስወግድ ዘንድ በርስዋ ላይ ኃላፊነት አርፎባታል፡፡ በአምላክ ቃል ውስጥ በተሰጡት ምክሮች መሠረት ቤተ ክርስቲያኒቱ የምታደርገው ሁሉ በሰማይ የጸና ይሆናል፡፡CCh 122.3

    የባሰ ትልቅ ጉዳይ ሲሆን፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንድትወስን ይቀርብላታል፡፡ ያምላክ ሰባኮች የሕዝቡ መሪዎች ሆነው በርሱ የተሾሙ ፈንታቸውን ካደረጉ በኋላ መላውን ጉዳይ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ማቅረብ አለባቸው፤ በሚደረገው ውሳኔ ኀብረት ይኖራቸው ዘንድ፡፡CCh 122.4

    ጌታ ለእርስበርሳቸው በሚያደርጉት አድራጎት ትልቅ ጥንቃቄ ይኖራቸው ዘንድ ተከታዮቹን ይፈልጋል፡፡ወደ ላይ ማንሳት፤ መመለስ፤ መፈወስ አለባቸው፡፡ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተገቢ /ትክክለኛ/ ዲሲፕሊንን ችላ ማለት የለበትም፡፡ አባሎችዋ በትምህርት ቤት እንዳሉት ተማሮች ከፍ ላለው መጠራታቸው የተገቡትን ጠባያት ያበጁ ዘንድ የሚማሩ መሆናቸውን ራሳቸውን መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ እዚህ በታች ባለችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ የእግዚአብሔር ትላቁ ኅብረት መዘጋጀት አለባቸው፡፡ እዚህ ከክርስቶስ ጋር በመስማማት የሚኖሩ መጨረሻ የሌለውን የዳኑትን የቤተሰብ ሕይወት (አኗኗር)ወደ ፊት ሊመለከቱ ይችላሉ፡፡፭57T262-264;CCh 122.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents