Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    በቤተ ክርስቲያን፡ ቢሲፕሊን፡ ውስጥ የክርስቶስ ሥርዓት፡፡

    የእግዚአብሔር ሕዝብ ለተሳሳቱት የቤተ ክርስቲያን አባሎች በሚያደርጉት አድራጎት መድኃኒታችን በማቴዎስ አሥራ ስምንተኛ ምዕራፍ የሰጠንን ምክር በጥንቃቄ መከተል አለባቸው፡፡CCh 120.1

    ሰብዓዊ ፍጥረቶች የክርስቶስ ንብረት ወሰን በሌለው ዋጋ በርሱ የተገዙ እርሱና አባቱ ለነሱ በገለጹት ፍቅር ከርሱ ጋር የተቆራኙ ናቸው፡፡ እንግዲህ ለእርስበርሳች በምናደርገው እንደምን ጥንቁቆች መሆን አለብን ሰዎች በጓድ ሰዎች ላይ ክፉ ለማሰብ መብት የላቸውም፡፡ የቤተክርስቲያን አባሎች ለተሳሳቱት ጓድ አባሎች በሚያደርጉት የገዛ ሐሳቦቻቸውንና ዝንባሌዎቻቸውም፤ በእንዲህ ክፉ እርሾ ወይም ላለችው እህት ደስ የማያሰኝ ወሬ /ሪፖርት/ ካንዱ የቤተክርስቲያን አባሎች ወደ ሌላይኛው ይተላፋል፡፡ አንዳንዶች በበኩላቸው የጌታ የሱስን ምክሮች ለመቀበል ፈቃደኞች ስላልሆኑ ስሕተቶች ይደረጉና ግፍም ይሠራል፡፡CCh 120.2

    ‹ወንድምህ ቢበድልህ› ሲል ክርስቴስ ተናገረ፤ ‹አንተም ከርሱ ጋር ሁነህ ብቻውን ምከረው› ፤ ማቴ 08.05፡፡ ስለ በደሉ ለሌሎች አትናገር አንድ ሰው ይነገረዋል፤ ከዚያ በኋላ ሌላውም፤ ደግሞ ሌላው እይቀጠለም ወሬው እያደገ ይሔዳል፤ ክፉም ይጨማመርበታል፤ መላዋ ቤተክርስቲያን እስክትሠቃይ ድረስ፡፡ ነገሩን፤ ‹ባንተና በርሱ በኻከል ብቻ› አደላድለው፡፡ ይህ ያምላክ አቅድ ነው፡፡ ‹ለጽል ፈጥነኸ አትውጣ፡፡ ባልንጀራህ ባሳፈረህ ጊዜ ኋላ ደርሰኸ እንዳይነድኸ፡፡ ክርክርህን ከባልንጀራኸ ጋር ተከራከር የሌላ ሰውን ምስጢር ግን አትግለጥ› ምሳሌ ፭፡፰፡፱፡፡ በወንደምህ ኃጢአት እንዲያይልበት አታድርገው እንዲሁም ችግር ጨማምረህበት ግስጋሤውን እንደ በቀል እንዲመስል እያደረግህ አታግፍጠው፡፡CCh 120.3

    ቅያሜህን ወደ ክፋት አታባብሰው፡፡ ቁስሉ እንዲፈርጥና የሚሰሙትን ሐሳባቸውን በሚበክሉ መርዛሞች ቃላት እንዲፈነዳ እትፍቀድ፡፡ መሪር የሆኑ ሐሳቦች አእምሮህንና የርሱን አእምሮ እንዲሞሉ ይቀጥሉ ዘንድ አፍቀድ፡፡ ወደ ወንደምህ ሒድ፤ በትህትናና በቅንነት ስለ ነገሩ ከርሱ ጋር ተነጋገር፡፡CCh 120.4

    የበደሉ ዓይነት ምንም ይሁን ይህ አለመግባባትንና የግል ጉዳትን /በደልን/ የማደላደል አምላክ ያቀደውን ፕላን የሚለውጥ አይደለም፡፡ ብቻህን ሁነህ በክርስቶስ መንፈስ ለተሳሳተው ሰው መናገር ብዚ ጊዜ ችግርን ያስወግዳል፡፡ ወደ ተሳሳተው ሰው በክርስቶስ ፍቅርና ርህራኄ ሒደህ ነገሩን ለማቃናት እሻ በጽጥታና በጽሞና ነጋገረው፡ ከከናፍርህ የቁጣ ቅላት አያምልጥህ፡፡ ለተሻለው ፍርዱ ተማኅጽኖ በሚያደርግ መንገድ ተነጋገረው፡፡ ‹ኃጡአተኛን ከስህተት መንገድ የሚመልስ ነፍስን ከሞት የሚያድን እንደሆነ የኃጢአትንም ብዛት ይሠውራል› የሚሉትን ቃላት አስታውስ፡፡ ያዕቆብ ፭፡፳CCh 120.5

    የጥላቻን (የፀብን) በሽታ የሚፈውሰውን መድኃኒት ለወንድምህ ወሰድለት ትረዳው ዘንድ ፈንታህን አድርግለት፡፡ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሰላምና ኅብረት ብለህ ይህን ለማድረግ ተግባርህ እንደ መሆኑ መብትህም /መታደልህም/ እንደሆነ ይሰማህ፡፡ ቢሰማህ፣ ወዳጅ አድርገኸው አተርፍኸው፡፡CCh 121.1

    ሰማይ ሁሉ በተጐዳውና በተሳሳተው መኻከል በተደረገው ጭውውት ይደሰታል፡፡ የተሳሳተው በክርስቶስ ፍቅር የቀረበለትን ግሣጼ ሲቀበልና ስህተቱን አውቆ ከአምላክና ከወንድሙ ይቅርታ ስለምን የሰማይ የጸሐይ ብርሃን በልቡ ይመላል፡፡ ፀቡ ተፈጸመ፤ ወዳጅነትና መተማመን ይመለስላቸዋል፡የፍቅር ዘይት በስህተት የቆሰለውን ቁስል ያሸራል፡፡ ያምላክ መንፈስ ልብን ከልብ ጋር ያቆራኛል፤ ስላገኙትም ኅብረት በሰማይ ሙዚቃ ይዘመራል፡፡CCh 121.2

    እንዲሁም በክርስቲያናዊ አንድነት የተባበሩት ለአምክ ጸሎት ሊያቀርቡና የቀናውን ለማድረግ ምሕረትን ለመውደድና ከአምላክ ጋር በትህትና ይሔዱ ዘንድ ራሳቸውን ሲሰጡ ታላቅ በረከት ይወርድላቸዋል፡፡ ሌሎችን በድለው እንደሆን የንስሐ የኑዛዜና የማቃናት ሥራ መቀጠል፤ ለእርስበርሳቸውም መልካም ለማድረግ በምሉ መታጠቅ አለባቸው፡፡ ይህ የክርስቶስ ሕግ አፈጻጸም ነው፡፡CCh 121.3

    ‹ባይሰማህም ደግመህ ካንተ ጋር አንድ ወይም ሁለት ውሰድ፡፡ በሁለትና በሶስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ ትጸና ዘንድ› ማቴዎስ 08.06፡፡ አእምሮዋቸው በመንፈስ የጐመሱትን ካንተ ጋር ውሰድ ከተሳሳተው ጋር ስለ ስህተቱ (በደሉ) ተነጋገሩ፡፡ ወንድሞች ተባብረው ስለ ለመኑት ተማኅጽኖ እሺ ይል ይሆናል፡፡ በነገሩ መስማማታቸውን ሲያይ ሐሳቡ ይብራራለት ይሆናል፡፡CCh 121.4

    ‹አርሳቸውንም ባይሰማ› እንግዲያውስ ምን ይደረጋልይ የተሳሳተውን ከማኅበርነት ለማሰናበት በቦርድ ስብሰባ ጥቂቶች ሰዎች በራሳቸው ላይ ኃላፊነት ይውሰዱንይ ‹እርሳቸውንም ባይሰማ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት› ቁጥር ፲፯ ቤተክርስቲያኒቱ ስለ አባሎችዋ ውሳኔ ታድርግ፡፡CCh 121.5

    ‹ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ሳይሰማት ካረማዊና ካጣሪ ቁጠረው ቁጥ. ፲፯ ፡ የቤተክርስትያንን ድምፅ ባይሰማ ሊመልሱትም የተደረጉለትን ጥረቶች ሁሉ ባይቀበል፤ ከማኅበርነት ትለየው ዘንድ ኃላፊነቱ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ያርፋል› በዚያን ጊዜ ስሙ ከመጻሕፍት ይፋቃል፡፡ ፬47T290-262;CCh 121.6