Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ፰—ስለ መጋቢነት የተሰጡ ምክሮች

    የልግሥና መንፈስ የሰማይ መንፈስ ነው፡፡ የክርስቶስ ራስን የመሠዋት ፍቅር በመስቀል ላይ ተገለጸ፡፡ ሰው እንዲድን ያለውን ሁሉ ሰጠ ከኪያ በኋላም ራሱን ሰጠ፡፡ የክርስቶስ መስቀል የብሩኩን የመድኃኒታችንን ተከታይ ሁሉ ለቸርነት ያማጽነዋል፡፡ እዚያ የተገለጸው ኘሪንሲኘል (ደንብ) መስጠት ስጥ ነው፡፡ ይህ በውነቱ ደግ በመሥራትና መልካም ሥራ በመስራት ሲካሔድ የክርስቲናዊ ሕይወት እውነተኛ ሕይወት ነው፡፡ የዓላማውያን ኘሪሲንኘል ማግኘት ማግኘት ነው ደስታን ሲያገኙ ተስፋ ያደርጋሉ ግን በይዞታው ሁሉ ፍሬው ጉስቁልናና ሞት ነው፡፡CCh 73.1

    ከክርስቶስ መስቀል የሚበራው የወንጌል ብርሃን ራስን መውደድ ይዘልፋል የልግሥናና የቸርነትንም ሥራ ማድረግን ያደፋፍራል፡፡ ለመስጠት በብዙ ጥሪዎች ስለሚቀርቡ የሚያጸጽት ነገር ሊሆን አይገባም፡፡ እግዚአብሔር በቸርነቱ ወደ ታላቅ ሥራ ይገቡ ዘንድ ከተወሰነው የተግባራቸው አካባቢ ሊያወጣቸው ሕዝቡን በመጥራት ላይ ነው የግብረገብነት (የሞራል) ጨለማ ዓለምን በሚሸፍንበት ጊዜ ያልተወሰነ ጥረት ይፈለጋል፡፡ ብዙዎቹ የእግዚአብሔር ልጆች በዓለማዊነትና በስስት በመጠመዳቸው በሚያሠጋ ላይ ናቸው፡፡ ለገንዘባቸው (ለመረጃ) ጥያቄዎችን የሚያበዛ ምሕረቱ ነው፡፡ ቸርነትን ከምግባር ላይ እንዲያወሉ የሚፈልጉባቸው ነገሮች እፊታቸው ሊኖሩ ይገባል አለበለዚያ የታላቁን የአምላክ ምሳሌ ጠባይ ሊከተሉ አይችሉም፡፡CCh 73.2

    ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን ሲልክ ‹‹ወደ ዓለም ሁሉ ሒዱ ወንጌልንም ስበኩ ለፍጥረትም ሁሉ›› ሲል በተናገራቸው ጊዜ የጸጋውን ዕውቀት የማስፋፋት ሥራ ለሰዎች መመደቡ ነው፡፡ ግን አንዳንዶች ለመስበክ ሲሔዱ ሳለ በምድር ያለውን ጉዳዩን የሚደግፉባቸውን ሥጦታዎች ይሰጡ ዘንድ ለፍላጎቶቹ መልስ እንዲሰጡ ሌሎችንም ይጠራል፡፡ ባልንጀሮቻችንን በማዳን ረገድ ለኛ የተሰጠውን ሥራ እንድናደርግ መለኮታዊ ሥጦታዎቹ በሰብዓዊ መስኖች አማካይነት እንዲፈስ ገንዘብ (መረጃን) በሰዎች እጆች ውስጥ አድርጎአል፡፡ ይህ ሰዎችን ከፍ ለማድረግ ከእግዚአብሔር መንገዶች አንዱ ነው፡፡ ለሰው የሚያስፈልገው ሥራ ይህ ነው እጅግ ታላቅ የሆነ የልብን ርህራኄ ያነሳና እጅግ ከፍ ያለውንም የአእምሮ ችሎታዎች እንዲሰራባቸው ያደርጋልና፡፡ ፩19T254, 255;CCh 73.3

    በቀና የተደረገው የደግነት ሥራ በሰዎች የአእምሮና የግብረገብነት (የሞራል) ኃይሎች ላይ ያመራና ችጋረኞችን ለመባረክና የእግዚአብሔርን ጉዳይ ለማስፋፋት እጅግ የሚያስደስት ሥራ እንዲያደርጉ ያነቃቃቸዋል፡፡ ፪23T401;CCh 73.4

    የተቸገረውን ወንድም ለመርዳት ወይም እውነትን በመዘርጋት ረገድ የእግዚአብሔርን ጉዳይ ለማገዝ ያለህ ምቹ ጊዜ ሁሉ አስቀድመህ ልከህ በደህና እንዲጠበቅ በሰማይ ባንክ ልታስቀምጥ የምትችል ዕንቁ ነው፡፡ ፫33T349;CCh 73.5